Friday, June 28, 2013

***ነጻነት የራስን መሰዋእትነት ይጠይቃል።***

***ነጻነት የራስን መሰዋእትነት ይጠይቃል።***

ተፈጥሮ የለገሰችንን ነፃነት ሰው መንጠቅ አይችልም።
ኧረ ማንም!!
ነጻነት እኛ ሰዎች በልደት ወደዚህ አለም ስንመጣ አብሮን የሚመጣ የተፈጥሮ ፀጋ ነዉ።
ደስ ሲል!
 ነጻነት ከሌሎች የምንጠብቀዉ ወይም ማንንም ስጠን ብለን የማንጠይቀዉ ፈጣሪ ለእያንዳንዳችን ያደለንን፤ በዚህ አለም ቆይታችን ለደቂቃም ቢሆን እንዲለየን መፍቀድ የሌለብን ኃብት ነዉ።
ደስ ሲል!
ነጻነታችን እጃችን ላይ ሲኖር በግለሰብ ደረጃ የምንደሰትበት፤ እንዳንቀማ በጋራ የምንጠብቀዉና እንደወያኔ አይነቱ ፀረ ህዝብ ኃይል ሲቀማን ደግሞ በጋራ ታግለን ማስመለስ የሚገባን የግልና የጋራ ኃብት ነዉ።
እውነት ነው።
 እኛ ኢትዮጵያዉያን በድህነትና በረሀብ የምንጠቃዉ፤ በዘረኝነት አለንጋ የምንገረፈዉ፤ የምንሰደደዉ፤ የምንታሰረዉና የምንገደለዉ  ይህንን ፈጣሪ ያደለንን ነጻነት የሚባል ኃብት ወያኔ አንድ፤ ሁለትና ሦስት እያለ ሲቀማን አፋችንን ዘግተንና እጃችንን አጥፈን ስለተመለከትን ነዉ።
እውነት ነው።
መፈናቀላችን፤ ስደታችን፤ ዉርደታችንና በገዛ አገራችን ሁለተኛ ዜጋ ሆኖ መኖራችን እንዲያበቃ ለማድረግ ያለን ብቸኛ አማራጭ ሌሎች መጥተዉ ነጻ ያወጡናል ከሚለዉ አመለካከት ተላቅቀን ነጻነታችንን ለማስመለስ  ስንታገልት ብቻ ነዉ።
እውነት ነው።
ወገን ሁሉ ለራሱ ነጻነት፣ ህልውና ሲል የለውጡ እንቅስቃሴ ታጋይ የመሆን ኢትዮጵያዊ ግዴታውን እንዲፈጽም ለራሱ ጥሪ ማቅረብ አለበት።
ቅስቀሳ አያስፈልግም!


የዘር በትር አለንጋ የሚደርስበት ግርፋት እንዲቆም
ስቃይ እንዲቆም
 ርሃብ እንዲቆም
 ስደት እንዲቆም
እንግልት እንዲቆም፣
የመናገርና የህትመት ውጤቶች መታፈን እንዲቆም፣
ፖለቲከኛው፣ጋዜጠኛው፣ማህበረሰቡን በአስተሳሰብ ምክንያት ማሰር ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው ነገሮች እንዲቆሙ።
ቅስቀሳ አያስፈልግም!


 ስለዚህ ህዝቡ ራሱ ለራሱ ነጻነት፣ በእምቢ አልገዛም ባይነት የሚነሳበት ጊዜው አሁን ነው።
ነጻነትን ከነጻ አውጭዎች በመጠበቅ እስከመቼ የአባገነኖች የጥይት ሰለባዎች እንሆናለን?
አለበለዚያ ላም አለኝ በሰማይ ወተትዋንም አላይ እንዳይሆን ያስፈልጋል።
 ግዜው ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በእኩልነትና በነጻነት የሚኖርባትን ሀገር ለመመስረት የሚደገውን የትግል ጉዞ እጅ ለእጅ ተያይዞ መቀጠል ያስፈልጋል

ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment