Sunday, June 2, 2013

ሕገ-መንግሥትን የማስከበር ትግል ከ“መደርመስ” ሲቆጠር!


- By Nasrudin Ousman 

በዛሬው ዕለት በሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ የተካሄደውን ሰላማዊ ሰልፍ ለወትሮው የህዝብን ድምጽ በማሰማት የማይታማው ኢቲቪ በዜና መልኩ ሰፋ አድርጎ ዘገበው፡፡ኢቲቪ እንዴት ሰልፉን ሊዘግበው ቻለ?” ለሚለው ጥያቄ ሳይንሳዊም ሆነ በአምክንዮ የተደገፈ ምላሽ ለመስጠት ያዳግታል፡፡ በደፈናው ሁለት መላምቶች እናስቀምጥ ካልን፣ በመጀመርያ ሰልፉአላየሁም፣ አልሰማሁምለማለት በማይመች መልኩ ኢቲቪ አፍንጫ ስር የተካሄደ በመሆኑ ነው ልንል እንችላለን፡፡ ምንም እንኳ ከይህ ቀደም [በኢድ አል አድሃ አረፋ] በቁጥር ከዛሬው የላቀ ህዝብ ደጃፉ ላይ ለበርካታ ደቂቃዎች ሰፍሮኢቲቪ ሌባ!” እያለ ሲጮህአላየሁም፣ አልሰማሁምቢልም፡፡ በሌላ በኩል፣ኢቲቪ ክንዋኔውን የዘገበው ሰልፉ ሕጋዊ እውቅና ባለው ፓርቲ የተጠራ በመሆኑ ነውብለን ልንገምት እንችላለን ቢያስኬድም ባያስኬድም፡፡

ዘገባው ሚዛናዊ ነበር ወይ?” 


የዚህ ጥያቄ መልስ ዘገባውን ለተመለከተ ሁሉ ግልፅ ይመስለኛል፡፡ ዘገባው ሚዛናዊ አልነበረም፡፡ ምንም እንኳ ሰልፈኛው በጋራ ካስተጋባቸው መፈክሮች የተወሰኑትን ቢያሰማንም፣ አንድን ሰልፈኛም ሆነ የሰልፉን አስተባባሪ ፓርቲ ተወካይ ቀረብ ብሎ በማናገር የሰልፉን ዓላማና የግለሰብ ሰልፈኞችን ውስጣዊ ስሜት ለማቅረብ አልፈለገም፡፡ [የድጋፍ ሰልፍ ቢሆን ኖሮ የስንት ወይዛዝርት፣ አዛውንትና የልምዓት ተጠቃሚዎችን አስተያየት እንሰማ እንደነበር አስቡት፡፡] ይህን ሆን ብሎ ገድፎ ሲያበቃ፣ ሰልፈኛው ሲያስተጋባቸው የነበሩ መፈክሮችን መነሻ በማድረግ፣ ‹‹በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተንፀባረቁት መልዕክቶችና መፈክሮች ሕገ መንግሥቱ በሃይማኖትና በፖለቲካ መካከል ያስቀመጠውን የልዩነት መሥመር የጣሱ ናቸው›› ብለው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች /ቤት ሚኒስትር ደኤታ አቶ ሺመልስ ከማል መናገራቸውን አስደምጦናል፡፡


እርሳቸውም በአካል ቀረቡና እንዲህ አሉ፡- 
“‘ፖለቲካ ከሃይማኖት መነጠል አለበት፤ ሃይማኖትም በፖለቲካ ጉዳይ ውስጥ መግባት የለበትም፤የሚል ግልፅ ሕገ መንግሥታዊ ትዕዛዝ አለ፡፡ ይህ ህገ መንግሥታዊ ትዕዛዝ በመንግሥት ብቻ ሳይሆን በሁሉም ወገኖች መከበር ያለበት ትዕዛዝ ነው፡፡ መንግሥትም ይህንን አጥብቆ የሚያከብረው ነው፡፡ […] ይህ ሆኖ ሳለ ግን በፖለቲካና በሃይማኖት መካከል ህገ መንግሥቱ ያሰመረው መስመር ሲደረመስ የሚታይበት ሁኔታ አለ፡፡” … 


በዚህ ንግግራቸው ክቡር ሚኒስትር ደኤታው ሕገ-መንግሥቱንየደረመሱበትን ሁኔታአስተዋላችሁን? ደረማመሱት እንጂ! ኧረ ጓድ ሺመልስ በሕግ አምላክ! … 

የአገሪቱ ሕገ መንግሥት በየትኛው አንቀጽ ነውፖለቲካ ከሃይማኖት መነጠል አለበት፤ ሃይማኖትም በፖለቲካ ጉዳይ ውስጥ መግባት የለበትም፤ብሎ የደነገገው? የሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 11 እኛ ሳንሰማ ተቀይሮ ነው ወይስ አቶ ሺመልስ በአየር ላይ ቀየሩት? የህገ መንግሥቱ አንቀጽ 11 “(1) መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው፤ (2) መንግሥታዊ ሃይማኖት አይኖርም፤ (3) መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፡፡ ሃይማኖትም በመንግሥት ጉዳይ ጣልቃ አይገባምእንደሚል ነው የምናውቀው፡፡ 

ከትናንቱ ሰላማዊ ሰልፍ ዐበይት መፈክሮች አንዱና ዋነኛውየሕዝበ ሙስሊሙ ጥያቄዎች በአግባቡ ይመለሱ!” የሚል ሲሆን፣ የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄዎች ደግሞ የሕገ መንግሥቱን አንቀጽ 27 እና አንቀፅ 11 መሠረት ያደረጉ ናቸው፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ ላለፉት 16 ወራት በሰላማዊ የተቃውሞ ትዕይንቶች መንግሥትን እየጠየቀ ያለው ሦስት ጥያቄዎችን ብቻ ሲኾን፣ ከሦስቱ ጥያቄዎቻችን አንደኛው፣በህዝበ ሙስሊሙ ሳይመረጡ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ላይ በሹመት የተቀመጡ አመራሮች ተወግደው፣ [በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 27 ንዑስ አንቀፅ 2 የተረጋገጠ መብታችንን በመጠቀም] የሃይማኖታዊ ተቋማችን አመራሮች በነፃና በዴሞክራሲያዊ መንገድ የመምረጥ መብታችን ይከበርየሚል ነው፡፡ 


ይህን ጥያቄ ያነሳነው በሁለት መሠረታዊ ምክንያቶች ነው፡፡ የመጀመርያው ምንክያት፣ 1987 አጋማሽ አንስቶ የኢህአዴግ መንግሥት በብቸኛው የጋራ ሃይማኖታዊ ተቋማችን ላይ ካድሬዎችን እና ታማኝ ሎሌዎቹን በመሾም ተቋማችንን በማሽመድመዱ፣ ተቋሙ ለሙስሊሙ ማኅበረሰብም ሆነ ለአገር የሚጠቅም አንዳችም ነገር አለማከናወኑን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ በሁለተኛና በዋነኝነት ግን፣ መንግሥት 2001 ወዲህ ይህንኑ በጉልበት የነጠቀንን ተቋም መሣሪያ በማድረግ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ አህባሽ የተባለ አዲስ አስተምህሮ ለመጫን በመንቀሳቀሱ ነው፡፡ ከሦስቱ መሠረታዊ ጥያቄዎቻችን ሁለተኛው የመነጨውም የሕገ መንግሥቱን አንቀጽ 11 ከሚጥሰው ከዚህ አስነዋሪ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ነው፡፡እምነትህን እኔ ልምረጥልህከማለት ወዲያ አስነዋሪ ነገር አለን?! አፄ ኃይለሥላሤም እንዲህ አላሉም! … ሦስተኛው ጥያቄያችን አወሊያ የተሰኘውን ተቋም የተመለከተ ሲኾን፣ የጥያቄው ምንጭ [መስፍን ነጋሽመንግጅሊስሲል ጥሩ ስም ያወጣለት መንግሥታዊው መጅሊስ] ይህንን ተቋም የአዲሱ አስተምህሮ ማስፋፊያ ማዕከል የማድረግ እቅድ የነበረው ከመሆኑ የመነጨ ነው፡፡ ይህ እቅድ በህዝበ ሙስሊሙ ጠንካራ ሰላማዊ ትግል ምክንያት ለጊዜው እንዲዘገይ የተደረገ ይመስላል፡፡ ነገር ግን ዛሬም ህገ መንግሥታዊ መብቶቻችን ተከብረው የጋራ የሃይማኖት ተቋማችንን መሪዎች መምረጥ አልቻልንም፡፡ አህባሽን በግድ የመጫን አጀንዳም አልቆመም፡፡ 20 እና 30 ዓመት የመስጂድ ኢማም (አሰጋጅ) ሆነው ያገለገሉ የሃይማኖት አባቶች እየተባረሩ በግድ የአህባሽ አሰጋጅ ተከትላችሁ ስገዱ እየተባልን ነው፡፡ መስጂዶች ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ እየተነጠቁ ለአህባሻዊው መጅሊስ እየተሰጡ ነው፡፡ ከዚያም አልፎ በሕገ መንግሥት የተረጋገጡ መብቶቻችን ከአህባሻዊው መጅሊስ መልካም ፈቃድ ሥር እንዲውሉ እየተደረገ ነው፡፡ በአጠቃላይ እንደዜጋ በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጡ መብቶቻችን በአህባሻዊ መጅሊስ አይረግጡ አረጋገጥ እየተረጋገጡ ነው፡፡ 

ጥያቄዎቻችንን ይዘው ከመንግሥት ጋር እንዲደራደሩልን በፊርማችን አፅድቀን የወከልናቸው የመፍትኄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች የህዝበ-ሙስሊሙ ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ ባለማግኘታቸው በሰላማዊ መንገድ ህገ መንግሥታዊ መብታችንን የማስከበር ትግላችንን በማስቀጠላቸው አሸባሪነትተከስሰውብናል፡፡ የኢህአዴግ መንግሥት ተወካዮቻችንን፣ የሃይማኖት አስተማሪዎቻችንን እና የህዝበ ሙስሊሙን ድምጽ ያስተጋቡ ጋዜጠኞችና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን ዘብጥያ ወርውሮ ሲያበቃ በመስከረም ወር 2005 ከብዙኃኑ ሙስሊም ኅብረተሰብ ፈቃድና ተሳትፎ ውጪ በቀበሌ አዳራሾች ራሱ ባደራጀው የምርጫ ጭምብል ያጠለቀ የሹመት ሂደት መልሶ የአህባሽ አጀንዳውን የሚያስፈፅሙ ታማኝ ሎሌዎቹን በተቋማችን ላይ አስቀመጠብን፡፡ እነዚህ ሎሌዎቹም በመላው አገሪቱ የሙስሊሙን ኅብረተሰብ ሰላማዊ ህይወት የማናጋት ተልዕኳቸውን በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎችና ልዩ ልዩ መዋቅሮች ድጋፍ እያስፈፀሙ ይገኛሉ፡፡ እኛም ሕገ መንግሥታዊ መብታችንንና ነፃነታችንን የማስከበር ሰላማዊ ትግላችንን ቀጥለናል፡፡ 

ላለፉት አሥራስድስት ወራት እያካሄድን ያለነው የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ በአጭሩ ለመንግሥትበህገ መንግሥቱ አንቀፅ 27/2 የተረጋገጠ መብታችንን መንግጅሊስን መሣሪያ በማድረግ አትግፈፈን፤ እንዲሁም አንቀጽ 11/1/ እና 11/3/ ተላልፈህ በሃይማኖታችን ጉዳይ በእጅ አዙር አትፈትፍት የሚል ነው፡፡ በዛሬው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በቃል ከተስተጋቡትና በሰልፈኞች ከፍ ተደርገው ከታዩ መፈክሮች መካከልመንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን ያቁም!”ህገ መንግሥቱ ይከበርየሚሉ ይገኙበታል፡፡ 

ሕገ መንግሥቱን የት ሄደን እናስከብረው?

የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 9 ንዑስ አንቀጽ 2ማንኛውም ዜጋ፣ የመንግሥት አካላት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሌሎች ማኅበራት እንዲሁም ባለሥልጣኖቻቸው ሕገ መንግሥቱን የማስከበርና ለሕገ መንግሥቱ ተገዢ የመሆን ኃላፊነት አለባቸውሲል ይደነግጋል፡፡ 
በዛሬው የኢቲቪ ዜና ላይም፣ ሚኒስትር ደኤታ ሺመልስ ከማልየፖለቲካ ፓርቲዎችና ወገኖች ይሄንን ሕገ መንግሥት የማክበር ብቻ ሳይሆን የማስከበርም ህገ መንግሥታዊ ግዴታም ጭምር ተጥሎባቸዋል፤ሲሉ ሰምተናል፡፡ ጥያቄ አለን ጓድ ሺመልስ! ታዲያ የእርስዎ መንግሥት እየደረማመሳቸው ያሉትን ከሃይማኖት ጉዳይ ጋር የተያያዙ የሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 11 እና 27 የት አባታችን ሄደን እናስከብራቸው?! 

ጓድ ሺመልስ፣ እርስዎ ዛሬ በኢቲቪ “‘ፖለቲካ ከሃይማኖት መነጠል አለበት፤ ሃይማኖትም በፖለቲካ ጉዳይ ውስጥ መግባት የለበትም፤ሲሉ በሕገ መንግሥቱ ውስጥ ያልተፃፈ ድንጋጌ አጣቀሱ፡፡ ይህንን ያልተጻፈ ድንጋጌ በማጣቀስም ሰማያዊ ፓርቲ በሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 9 የተጣለበትንሕገ መንግሥቱን የማስከበርኃላፊነቱን ለመወጣት ያደረገውን ጥረት ማድነቅ ሲገባዎ ኮነኑ፡፡ ታዲያ፣ እርስዎን የት ሄደንየሕገ መንግሥቱን አንቀጾች በአየር ላይ በመቀየር ወንጀልእንክሰስዎትና ሕገ መንግሥቱን የማስከበር ህገ መንግሥታዊ ግዴታችንን እንወጣ?! … ቸገረን እኮ! … “አለእኔ ጩሉሌ የለምባይነትዎ ለከት አጣብንኮ! … ምንድነው የሚሻለን?! …

No comments:

Post a Comment