Friday, June 14, 2013

**የአባይ ጉዳይ የሰሜት ጉዳይ አይደለም!!!**


ትልቅ ጉዳይ ነው።ግን ያለ ነፃነት ልማት ዋጋ የለውም!!!
የህዝቡ ጥያቄ በአሁን ሰዓት የነፃነት ፕሮጀክት ነው የሚፈልገው።
የውኃ ጥም የሚረካው ውኃ ፍሪጅ ውስጥ ስለተቀመጠ አይደለም፡፡ ሱቅ ውስጥም ስለተደረደረ አይደለም፡፡ ምንጮች ውኃ ስላላቸው አይደለም፡፡ የውኃ ማስታወቂያዎች ስለተሰሙ፣ ስለተነበቡና ስለታዩ አይደለም፡፡ በተጨባጭ የተጠማው ሰው ማግኘትና መጠጣት ሲችል ነው፡፡
ገዥው ፖርቲ እውነታውን ለህዝብ ከመነሻው ጀምሮ ማሳወቅ አለበት።ግብፆች ስለአባይ ጉዳይ እኮ ተቃዋሚውቹንም ጠርተው ስለ አገራቸው እንዲመክሩ ተደርጓል ታዲያ የገዥው መንግስት ተቃዋሚውን ለማማከር አይደለም እንደ ባህዳን አገር ሰው መቁጠሩን ተያይዞታል ይህ አካሄድ ምንም አያስኬድም ዋጋ ያስከፍላል እንጂ።እነ በረከትም  አገር ውስጥ ያሉትን ጋዜጠኞች ሰብስበው ስለ አባይ ጉዳይ ምንም መጥፎ ነገር እንዳይዘግቡ ማስፈራራት ተያይዘውታል።
አገራዊ ጉዳይ ብቻ እንዲያደርጉት እያሳሰቧቸው ነው።ከህዝብ ምንም ነገር ሊደበቅ አይችልም።ወያኔ/ኢህአዴግ የአባይን ጉዳይ ፕሮፓጋንዳ መንፊያ አድርገውታል።
የኢትዮጵያ መንግስት የአባይንጉዳይ የፖለቲካ መጠቀሚያ ማድረጉን እንዲያቆም ማድረግግድይላል።እውነቱ ግን ይህ ነው
ሁሉንም ነገር ለፖለቲካ ፍጆታ ለማዋል የቆረጠ ፓርቲ የሀገርን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ መጣሉ የማይቀር  
አባይ ከመገደቡ በፊት መፈፀም የሚገባው የዲፕሎማሲ ስራዎች አልተሰሩም፡፡

እውነታውን ይዘን መዄድ ካለብን “በአባይ ላይ ግድብ ከመሰራቱ በፊት ማለቅ የሚገባቸው የዲፕሎማሲ ስራዎችና ሌሎች ጉዳዮች በውል ታይተዋል ወይ የሚል ጥያቄ ማንሳት ተገቢ ነው፡፡ ከነዚህም ዋነኛው በቂ የዲፕሎማሲ ስራ ያለመሰራቱና ከአባይ ተጋሪ ሃገሮች ጋር በቂና አስተማማኝ ውይይት አድርጎ ስምምነት አለመድረስ በዚህ የተነሳ ሃገሪቱ የጦርነት ስጋት ቢገጥማት ለመቋቋም በቂ ዝግጅት ያለማድረግ ይገኙበታል፡፡”
የኢትዮጵያና የግብፅ መንግስት ከፀብ አጫሪ ድርጊትተቆጥበው በጠረጵዛ ዙሪያ ንግግሮች ላይ እንዲያተኩሩ መሆን አለበት።
  ሁለቱም ሀገሮችየአባይን ጉዳይ ለውስጥ ፓለቲካ ማብረጃ ከማድረጋቸው እንዲቆጠቡና የኢትዮጵያመንግስት ደግሞ ጉዳዩን ለፖለቲካ መጠቀሚያ ማድረጉን ማቆም አለበት፡፡

ገዥው ፓርቲና መንግስት በህዳሴው ግድብ ላይ ህዝቡን ባለቤት አላደረ ፡፡

“ችግሩ የሚመነጨው ገዥው ፓርቲ በአባይ ወንዝ ላይ ግድብ ለመስራት መነሳቱ ሳይሆን የአባይን ጉዳይ የኢሕአዴግ ጉዳይ ማድረጉ
የአባይን ጉዳይ የአንድ ግለሰብ ራዕይ ማድረጉና ከእለት ጉርሱ ቀንሶ ቦንድ እየገዛ ያለውን ህዝብ የግድቡ ባለቤት ማድረግ አለመቻሉ ነው፡፡
ግድቡ የኢትዮጵያ ህዝብ ግድብ ይሁን የኢሕአዴግ በዉል አልለዩትም፡፡
ኢትዮጵያዊነት በዘፈቀደ የመጣና በዘፈቀደ ሊደበዝዝ የሚችል አርእስተ-ጉዳይ አይደለም፡፡ አዲስና ቅኝ አገዛዝ ሰራሽም አይደለም፡፡ ለረጅም ዘመናት አብሮ በመኖር ከቁሳዊና ማህበራዊ ውህደት የመጣ ታሪካዊና ሕያው ህልውና ነው፡፡ ሉዓላዊነትም ነው፡፡ ትላንት የነበረ ዛሬም ያለ ለወደፊትም የሚኖር ው።
እውነታው ግን የአባይን መገደብ የሚቃወም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የለም ኢትዮጵያዊ ሀገሩን ሲነኩበት አይወድም እውነታው እንዲ ነው። ነገር ግን አባይ የሚገደበው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲጠቀም ከሆነ  ህዝብ ይከበር ነው የምንለው  ከአባይ በፊት፦
ነፃነት ይቅደም!
ዘረኝነት ይገደብ !
ህዝብን ማፈናቀል ይቁም !
ሰብዊነት ይቅደም !
በሃገራችን የአፓርታይድ ስርዐት ይወገድ !
የሃይማኖት ነጻነት ይከበር !
አባይን ለርካሽ ፖለቲካ መጠቀሚያ ማድረግ ይቁም !
በግፍ የታሰሩ ጋዜጠኞች ይፈቱ !
የሙስሊም ድምጽ ይሰማ !
ታሪካዊ ገዳማችን ዋልድባ ይከበር !
በህዝብ የተመረተ መንግስት ይምራን !
የህዝብ ድምጽ ይሰማ !
ነብሰ ገዳዮች ለፍርድ ይቅረቡ !
እና ሌሎችን ተያያዥነት ያላቸውን መሰረታዊ ጥያቄዎችን ነው የተጠየቀው 

  ኢህአዴግ/ወያኔ አባይን ለኢትዮጲያ ህዝብ አጀንዳ መስጠቱ ነው ህዝቡ በጣም ነቅቷል!
የህዝቡ በአሁን ሰዓት የነፃነት ፕሮጀክት ነው የሚፈልገው።
ድል ለነፃነት ለሚሻው ሰፊ ህዝብ!!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment