እንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በቅርቡ ‹‹የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻነት››በሚል አቢይ ርዕስ የህዝባዊ ንቅናቄ ጥሪ ለህዝብ ማስተላለፉ አይዘነጋም፡፡አንድነት በዚህ ህዝባዊ ንቅናቄ የአንድ ሚልዮን ዜጎችን ፊርማ በማሰባሰብ የዜጎችን የማሰብ፣ የመናገር ፣በነጻነት የመደራጀትና ሃሳብን የመግለጽ መብቶችን ጨምሮ ከህገ መንግስቱ ጋር ይጋጫል ያለውን የጸረ ሽብር ህግ እንዲሰረዝ ህጋዊ መስመርን በመከተል ጫና እንደሚያደርግ ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡ ይህንኑ መግለጫ ተከትሎ የዛሚዋ ሚሚ ስብሃቱ በምትመራው ‹‹የጋዜጠኞች የክብ ጠረጴዛ ››የውይይት መድረክ የአንድነትን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ከግብጽና ከግንቦት 7 ጋር በማቆራኘት ‹‹ፓርቲው ይህንን እንቅስቃሴ ያደረገው የህዳሴው ግድብ እንዳይሳካ ከሚፈልጉ ሀይሎች የገንዘብ ድጉማ ተደርጎላቸው ነው፡፡››በማለት የወረደና የተለመደ ፍረጃዋን አስደምጣለች፡፡
አንድነትን ለፍርፋሪ ያጩት እነ ሚሚ አልገባቸውም ወይም ሆን ብለው የሚሰማቸው ካለ ለማሳሳት አልያም አፍቅሮተ ኢህአዴግነታቸው ከኢህአዴግም በላይ ራሳቸውን እንዲያስቀምጡ አድርጓቸው ይሁን በተለየ መንተገድ የአንድነትን የሰላማዊ ትግል ጥያቄ አንድ ከረጢት ውስጥ በመክተት ፓርቲውን ለማስወንጀል ደንጊያ ለማቀበል ታትረዋል ግን አንድነት ለምን የጸረ ሽብር ህጉ እንዲሰረዝ ይታገላል; ኢትዮጵያስ የሽብር ህግ አያስፈልጋትም የሚል አመለካከት አንድነት አለውን; ይህ ምላሽ ሁለት ጆሮዎቿን በአብዮታዊ ዲሞክራሲ የደፈነችውንና በነጻ ሚዲያ ስም የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ያገኘችውን ሚሚንና ሁለቱን ደንገጡሮቿን አይመለከትም፡፡ 1)አንድነት በኢትዮጵያ ጥቅም ላይ ከኢህአዴግ ጋር በተቃራኒነት ስለተሰለፈ ብቻ ለማንም አሳልፎ አይሰጥም፣የአገሪቱን ጥቅም ከሚጎዳ የትኛውም ቡድን ጋርም የሚፈጽመው ምንም አይነት ስምምነት አይኖርም፡፡አንድነት በዚህ በኩል ጽኑ ኢትዮጵያዊ አቋም አለው፡፡እንዲህ አይነት ልምድና ታሪክ ያለው አሁን በገዢነት መንበር ላይ የተቀመጠው ኢህአዴግ እንጂ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የማያወላውል አቋም ያለው አንደነት አይደለም፡፡ለገዢው ፓርቲም የሚበጀው የተቃዋሚዎችን እንቅስቃሴ ከወቅታዊ ሁነቶች ጋር በግድ በማዛመድ ትርጉም መስጠት ሳይሆን ለመነጋገርና እውነታውን ለመቀበል መዘጋጀት ብቻ ነው፡፡ 2)አንድነትና ግንቦት 7 ማቆራኘት ሚሚየጀመረችው አይደለም፡፡የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በፓርላማ ጭምር ፍረጃቸውን ማስደመጣቸውን በሰላማዊ ትግል ዙሪያ ቁርጠኛ አቋም በመያዝ ለብዙዎች አርአያ የሆነውን አንዷለም አራጌን በሽበርተኝነት በመወንጀል እድሜ ልክ አስፈርደውበታል፡፡አንድነት በህዝብ ድምጽ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር ገዢው ፓርቲ በየእለቱ የሚደቅንበትን መሰናከል እየተሻገረ የሚታገል ብረትን የሚጠላ ሰላማዊ ፓርቲ ነው፡፡እነ ሚሚ የህዝቡ መነቃቃትና የትግል መንፈስ መነሳሳት ድንጋጤ ውስጥ ከቷቸው ይሉት ይጨብጡትን ስላጡ አንድነት በዚህ የተለመደ ፍረጃ በመደናገጥ አንድ ስንዝር ወደኋላ አይልም፡፡ 3)አንድነት የጸረ ሽብር ህጉ ይሰረዝ ያለው ሚሚ እንደምትለው ከግብጽ ወይም ከግንቦት ሰባት ትዕዛዝ ስለ ወረደለት ሳይሆን በሽብር ህጉ ህገ ወጥነት ዙሪያ ከበቂ በላይ መረጃዎችንና ማስረጃዎችን በመሰብሰቡ ነው፡፡የአገሪቱ ህገ መንግስት በአንቀጽ 9 በግልጽ ከህገ መንግስቱ ጋር የሚጋጭ የትኛውም አይነት ህግ ወይም መመሪያ ተቀባይነት እንደሌለው እያወጀ የጸረ ሽብር ህጉ 15 ያህል አንቀጾች ህገ መንግስቱን እየተጣረሱ ፣የዜጎች መብት እየተደፈጠጠና ገዢው ፓርቲ ህጉን በሽፋንነት እየተጠቀመ ጋዜጠኞች፣ፖለቲከኞች፣የሃይማኖት ተደራዳሪዎችና አክቲቪስቶችን እያሰረና እያሰበረገገ ባለበት ሁኔታ አንድነትና ፊርማቸውን በተዘጋጀው ሰነድ ላይ እያኖሩ ያሉ ዜጎች ያሰሙትን ተቃውሞ ከግብጽ ፍርፋሪ ጋር ማቆራኘት ‹‹አያ ጅቦ ሳታመሃኝ ብላኝ››የምትለውን ተረት እንድናስታውስ ያደርገናል፡፡ - See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=4717#sthash.Yq6HGFeM.dpuf

No comments:
Post a Comment