Thursday, July 25, 2013

እየገፉ እናውቅልሃለን

ራሳቸው ያወጡትን ህግ ራሳቸው እየጣሱ እናውቅልሃለን ..
በኑሮ ውድነት እያሰቃዩን እናውቅልሃለን
በፍትህ እጦት እያሸበሩን እናውቅልሃለን ..
በሃገሪት የሚካሄዱ እንቅስቃሴዎችን ሁሉ እየተቆጣጠሩ እኛ እናውቅልሃለን

ይብቃ እናውቅልሃለን!

የወያኔ መንግስት የአመለካከት ልዩነትን አያስተናግድም እናዉቃለን 
ተቃዋሚ ፓርቲ እንዳይኖር ይፈልጋሉ ነጻ እትመት እንዳይኖር ይፈልጋሉ ነጻ ሃሳብን ይዞ የሚጽፍ ሰው ጸረ- ሽብርተኛ ተብሎ እንደሚታሰር እናዉቃለን 
የሚተቸዉን ሰዉ ከቻሉ ማሰር ካልቻሉ እንዲሰደድ ማድረግ ተቀዳሚ ተግባራቸዉ ነዉ እናዉቃለን 


በወገናቸዉ ላይ ክህደት ይፈጽማሉ መግቢያ መዉጫ ያሳጣሉ ከእነሱ የተለየ አመለካከት የማስተናገድ ብቃትና ፍላጎት የመሪነት አቅም ያለዉ ሰዉ ማሰር የተካኑበት ሙያቸዉ ነዉ:: ዘርን ከዘር መለየት መርሀ- ግብራቸዉ ካደረኩትም ብዙ አመታን አሳለፉ አረ ምን ተባለነ >>>> በዚህም ኢትዮጵያን እየከፋፈሉ ናቸዉ ለግል ጥቅማቸዉ ብለዉ ኢትዮጵያን ይነካሉ ::

አሁን አሁንማ የሚገርም ደረጃ ላይ እየተደረሰ ነዉ የኢትዮጵያ ጠላቶች የሚባሉት ስለ ኢትዮጵያዊነት የሚቆረቆሩት ሰዎች በአንድነት በጋራ በመተሳሰብና እኩልነት የሚሰብኩ ሰዎች የማርያም ጠላት በመባል እያሳደዱ መግደላቸዉን ማሰራቸዉን የቀጠሉበት አረመኔዉ ዘመን መሆኑ ... 

ለሃይማኖቴ እያለ የሚታገለዉን፣ ለነጻነቱና ለሕዝቡ መብት እንዲጠበቅ የሚጽፈዉ ጸረ- ሽብርተኛ እያሉ እየከሰሱ እያሰሩ ወያኔ ከዚህ በላይ ምን ያድርግ ? ማን ይዳኘው !! 
ክቡር የሆነዉን የሰዉ ልጅ አበላልጦ በመግዛት የወያኔን ሎሌዎች የበላይ ሆነዉ እንዲኖሩበት ከማድረግ በላይ ምን ሌላ ነገር ይመጣልስ¬ ¬¬? ይህ አምባገነን መንግስት ከጭፍሮቹ ጋር የሴራ መዝሙር እየዘመሩ እስከመቼ እንተዋቸዉ ? ኢትዮጵያዊነት ስሜት እያጠፉ የሕዝብ ጠላት ሆነዉ እያየን ዝም ማለት እስከ መቼ
ይብቃ እናውቅልሃለን!
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment