Thursday, July 25, 2013

እስቲ እረጋ ብለን ደግሞ እንነጋገር… ”ጭርቁምፈምቶታ ኡመታ ኢትዮጵያ”

ከአቤ ቶክቻው

ወንድማችን
ጃዋር መሀመድ እኔን ጨምሮ በርካቶች የሚያደንቁት ወጣት ነው፡፡ ሀሳቦቹ አንጀት ላይ ጠብ የሚሉ ገዢ ሀሳቦች ናቸው፡፡ የሚገዙት ታድያ እንደ ገዢው ፓርቲ አስገድደው አይደለም፡፡ ጃዋር ወደው ፈቅደው የሚገዙላቸው

ሀሳቦች ባለቤት ነው፡፡ እኔ ከጃዋር ሀሳቦች ጋር በቅጡ የተዋወቅሁት የቱኒዚያ አብዮት የተቀሰቀሰ ሰሞን ነበር፡፡ ስለ ቱኒዚያ እና ግብፅ አብዮቶች መንስኤ፤ አስፈላጊነታቸው እና ውጤታማነታቸው ጃዋር ከፃፈው በተሸለ ገብቶኝ እና ተመችቶኝ ያነበብኩት መኖሩን እንጃ

ከዛም በኋላ ጃዋር የሚሰጣቸውን ትንታኔዎች ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ እሰማለሁ፡፡ ሰምቼም እስማማለሁ፡፡ ምን መስማማት ብቻ፤ የሆነ ቀን ጃዋር ምርጫ
ቢወዳደር ይምራኝ ብዬ የምመርጠው ሁሉ እስኪሆን ድረስ አክባሪው ሆኛለሁ…!
ከእለታት በአንዱ ቀን እኛበፌስ ቡክ አስተዳደር የኢህአዴግ ዋና የስራ ሂደት ባለቤትየምንለው ዳንኤል በርሄ በአሁኑ ሰዓት በአልጀዚራ የሚተላለፈውን እባክችሁ ቅዱልኝ ብሎ ተማፅኖ ሲያሰማእኔ እንደ እናንተ አይደለሁምበሚልሙድልቀዳለት ወደ አልጀዚራ ጎራ አልኩየማከብረው ጃዋር በአልጀዚራ ስቱዲዮ ጉብ ብሏል፡፡ እውነቱን ለመናገር ጃዋርን ባየሁት ጊዜ ኖራብዬ አባቴ የሚያከብረው ሰው ሲመጣ እንደሚያደርገው በአክብሮት ከመቀመጫዬ ተነስቻለሁ

እንግዲህ ይሄኔ ነው፡፡ ኦቦ ጃዋር እስከዛሬ ሲናገር ይስማሙኝ ከነበሩት በተቃራኒው የማይስማማኝን ነገር ሲናገር የሰማሁት፡፡ የተረገመቺቱ የአልጀዚራ ጋዜጠኛ አንድ የተረገመ ጥያቄ ጠየቀችውኦሮሞ ፈርስት ወይስ ኢትዮጵያ ፈርስትአለችውእርሱም ኦሮሞ ፈርስት አለ፡፡ ጃዋር ይሄንን የማለት መብት አለው፡፡ ኢትዮጵያዊነት በግድ የተጫነብኝ ነው ሲልም ተናገረ፡፡ ይሄንንም የማለት መብት አለው፡፡ እኔ ደግሞ መብቴን በመጠቀም፤ አንድ ውሳኔ ላይ ደረስኩጃዋር ምርጫ ቢወዳደር አልመርጠውም፡፡ እንኳንም ቀድሞ ተወዳድሮ ጉድ አላደረገኝ አልኩ… (አልጀዚራንም እረገምኩ እንድንከፋፈል አድርጎናልና፤ ዳንኤል በርሄንም ረገምኩ አልጀዚራን እንድመለከት አድርጎኛልና፤ ጃዋርንም አሽሟጠጥኩ ሀሳቡ አልረባልኝምና!)

ጃዋርን ያሰብኩት ለክልሉ አስተዳዳሪነት ሳይሆን ለሀገሪቷ መሪነት ነበር፡፡ ታድያ ለቤተዘመዶቹ ቅድሚያውን የሚሰጥ መሪ አማራሪ እንጂ ምኑን መሪ ሆነውለመሆኑስ የብሄርተኝነት ጥጉ የት ድረስ ነው…. ስልምሽሮሜዳ ደረስኩእናም የመጣው ምጣ ብዬ አሽሟጠጥኩ!

ይለይልህ ብለው የጃዋርን ሌላ ንግግር ሰዎች ካለበት ፈልፍለው አሳዩኝይሄኛው ደግሞ የባሰበት ነው፡፡ ጃዋር ባደገበት አካባቢ ዘጠና ዘጠኝ በመቶው ሙስሊም ነው፡፡ ስለዚህ አንድ ሙስሊም ያልሆነ ኦሮሞ ቀና ቢልበሜንጫ ነው አንገቱን የምንለውአለን፡፡ ልብ አድርጉልኝ ጃዋርኦሮሞ ፈርስትብሎ አላቆመም ደግሞሙስሊም ኦሮሞ ፈርስትአለን ማለት ነው፡፡ ስለዚህ እኔ እና ሌላው ዋቄፈታ ኦሮሞ ጃዋርን ይምራን ብለን መርጠነው ቢሆን ኖሮ እጣ ፈንታችን ቀና ስንል ሜንጫ ነበር ማለት ነው፡፡

አንድ ጊዜ ቤተሰባዊ ዝምድናውን ያስቀደመ ሰው ማብቂያ አይኖረውም፡፡ የምለው ለዚህ ነው፡፡ በደሉ የሁላችንም ነውና በደል የሌለባት ሀገር እንድትኖረን ሁላችን በአንድ ላይ ብንተባበር የተሸለ ነው የምለውም ለዚህ ነው…! “ሁላችንም ነፃ ካልወጣን አንዳችንም ነጻ አይደለንምየሚለው የኦባንግ ሜቶ ንግግር የሚማርከኝ ለዚህ ነው፡፡

በኦነግ ትግል ምስረታ ወቅት ከመስራቾች አንዱ የነበሩት ሀጂ ሁሴን ሱራ፤ ትግላችንን ለሁሉም ኢትዮጵያውያን እንዲሆን፤ጭርቁምፈምቶታ ኡመታ ኢትዮጵያ” (የተጨቆኑ የኢትዮጵያ ህዝቦች) እንበለው እና በጋራ በደልን እንታገል ሲሉ ቀደምት የኦሮሞ ታጋዮችን ለማሳመን አጥብቀው ሲከራከሩ እንደነበር ስለኦነግ ሚጢጢ እውቀት ያለው ሁሉ የሚያስታውሰው ነው፡፡ እናም ይህ ሀሳብ በኦሮሞ ዘንድ አዲስ ሀሳብ አይደለም፡፡

በአሁኑ ጊዜ ያሉ ኦሮሞ ታጋዮች የቀድሞ ንጉሳ ንጉሶችን በመኮነን በኦሮሞ ህዝብ ላይ የደረሰውን በደል ሲዘረዝሩ ይሰማሉ፡፡ እውነቱን ለመናገር በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የአማራም የኦሮሞም የጉራጌም የትግሬም ገበሬ ደልቶት የሚያውቅበት ጊዜ አላነበብኩም፡፡ ከንጉሳውን ቤተዘመዶች ውጪ አብዛኛው ህዝብ ጭቁን ነበር፡፡ ለዚህም ነበር በእነ ሃጂ ሁሴን ሱራ ዘንድጭርቁምፈምቶታ ኡመታ ኢትዮጵያየሚለው ሃሳብ የተወለደው፡፡

በአፄዎቹ ዘመን የተበደለው እና የተጨቆነው ኦሮሞው ብቻ እንኳ ቢሆን፤ እንደ ጃዋር የመሰሉት ምሁራን ያለፈውን ታሪክ ለታሪክ ፀሀፊዎች ትተው እነርሱ በሽሙጡም ሳይደነግጡ በሙገሳውም ሳኩራሩ ለወደፊቷ ኢትዮጵያ የሚበጀውን የመቻቻል መንገድ በመቀየስ ታሪክ ቢሰሩ መታደል ነበር፡፡

ዛሬ በወዳጃችን ጃዋር ድረ ገፅ ላይበዲያስፖራ ያለውን የወቅቱን የኢትዮጵያ ፖለቲካ በማስመልከት በአውሮፓ የኦሮሞ ወጣቶችና የሴቶች ማህበራት የጋራ መግለጫየሚል ፅሁፍ ተመለከትኩ፡፡

በተለይ ደግሞ ይቺ አንቀፅ ቀልቤን ሳበችው፡፡

እኛ በአውሮፓ የኦሮሞ ወጣቶችና የሴቶች ማህበራት በአሁኑ ወቅት በአልጀዚራ ላይ ቅድሚያ ኦሮሞ ነኝ በማለቱ ብቻ በፖለቲካ ምሁሩ ጀዋር ላይ የተከፈተውን የሀሰት ዘመቻ ማውገዝ ብቻ ሳይሆን ለመከላከልም በመገደዳችን ይህ አይነቱ አጼያዊ ዘመቻ እስኪያቆም ድረስ ከቅርብ ጊዜ በፊት ከሰላም ወዳድ የአንድነት ሀይሎች ጋር የጀመርነውን የቅርርብ ዲያሎጎችና የሀሳብ ልውውጦች በይበልጥ ልንገመግምው ወስነናል።

እኔ ጃዋርን ብሆን ኖሮ ይህንን ፅሁፍ በራሴ ድረ ገፅ ላይ አላትምም ነበር፡፡ ምክንያቱም ጃዋር የዚህ ማህበር አባል አይደለም እርሱ የሚኖረው አሜሪካ ነው፤ መግለጫው ደግሞበአውሮፓ የኦሮሞ ወጣቶችና የሴቶች ማህበራትያወጡት ነው፡፡ የአደባባይ ሰው ሲሆኑ ትችትም ሙገሳም እንደሚመጣ የታወቀ ነው፡፡ ለሚሰነዘርብን ትችት በሙሉ ዘመዶቻችን መግለጫ እንዲያወጡልን ከመጋበዝ ራሳችን ነጥብ በነጥብ ለመመለስ መሞከር የተሸለ ነው፡፡

ማህበሩም ቢሆን ጃዋር ላይ የሚሰነዘር ትችት ኦሮሞ ላይ የተሰነዘረ አድርጎ በማየት “…ከሰላም ወዳድ የአንድነት ሀይሎች ጋር የጀመርነውን የቅርርብ ዲያሎጎችና የሀሳብ ልውውጦች በይበልጥ ልንገመግምው ወስነናል።የሚል ትልቅ ፖለቲካዊ አንድምታ ያለው መግለጫ ማውጣቱ አስገራሚ ነው፡፡ ትልቅ ሀገራዊ ራዕይን አንድ ሰው ተነካ ብሎ እንደውም አንጫወትም ብሎ ለማቋረት መዳዳት ለማን እንደሚጠቅም ፈጣሪ ይወቅ…!

ጃዋር ወደፊትም ቢሆን ጥሩ ሲሰራ መመስገኑ መጥፎ ሲሰራ መተቸቱ የማይቀር ነው፡፡ ለትችቱ ምለሽ ለሙገሳውም ምስጋና መስጠት ያለበት ጃዋር እንጂ ዘመዶቹ አይደለንም፡፡

በአሁኑ ወቅት ትልቁ አሳሳቢ ችግርጭርቁምፈምቶታ ኡመታ ኢትዮጵያ” (የተጨቆኑ የኢትዮጵያ ህዝቦች) አለመተባበራቸው ነው፡፡ እኔ ብቻ ነኝ የተበደልኩት ብሎ የራስን ችግር ብቻ አግዝፎ ማየት እና ማሳየት የትም አያደርስም፡፡ (ብዬ አስባለሁማሰብ መብቴ ነው! (በሌላ ቅንፍ ደግነቱ ይሄንን ችግር ሀገር ውስጥ ብብዛት አላየሁትም…))

ጎበዝ ለማንኛውምበስጫው ትተን እስቲ ረጋ ብለን እንነጋገር…!

በስጫ”… ማለት የአራዳ ብሄረሰብ ቋንቋ ሲሆን ትርጓሜውም ብስጭት ማለት ነው፡፡

No comments:

Post a Comment