በፍች ጉዳይ ምክንያት በጠበቃው ክርክር የልረካው ኢትዮጵያዊ -እስራኤላዊ ጠበቃውንና የጠበቃውን ሴት ልጅ ገደለ፡፡ተጠርጣሪው በአካባቢው በሚገኝ ህንፃ የጥበቃ ስራ ይሰራ እነደነበርና ከጠዋቱ 9;40 ሰአት አካባቢ ግድያውን እንደፈጸመ ተናግሯል፡፡ገታሁን ታደሰ የተባለው ኢትዮጵያዊ -እስራኤላዊ የጥበቃ ሰራተኛ በፍች ሂደት ውስጥ እንደነበርና ሟች ጠበቃን ቀጠሮ ይከራከር እንደነበር የፖሊች ዘገባ ያስረዳል፡፡ ሆኖም ግን በፍርድ ሂደቱ ያልረካ በመሆኑ ጠበቃው ጋር ሄዶ የከፈለውን 5000 ሸቄል(ብር) እንዲመልስለት ጠይቆት እንደነበርና ቀጥሎም በያዘው መሳሪያ ጠበቃውንና ሴት ልጁን ከቅርብ ርቀት ተኩሶ እንደገደላቸው ተገልጿል፡፡
ኢትዮጵያዊ -እስራኤላዊም ወንጀሉን እንደፈጸመ በፖሊስ እንደተያዘና እርስ በረሱ የተቃረነ ማስረጃ እንደሰጠ የተዘገበ ሲሆን በወንጀሉ ወቅት አእምሮው ነትክክል እንዳልነበርና ሲታየው የነበረው ሁሉ ጨለማ እንደነበር ተናግሯል፡፡
ኢትዮጵያዊ -እስራኤላዊው ምንም አይነት የአእምሮ ህመም እንደሌለበትና የጥበቃ ስራውን ሲጀምር የተሰጠውን የአእምር,ሮ ጤንነት ፈተና አልፎ መሳሪያ እንደተሰጠው ተጠቅሷል፡፡ ይህንን ተከትሎ ዳኛው ሮብለት የአእምሮ ህመም ምርመራ እንዲያደርግና ለስምንት ተጨማሪ ቀናት እንዲቆይ ትዛዝ ሰጥተዋል፡፡
No comments:
Post a Comment