***የአስመሳይነት ካባ ለብሰው የሚያቀነቅኑ የኢህአዴግ/ወያኔ የራሱ የሆኑ
ልማታዊ ጋዜጠኞች አሉት !! የማያሻማ የአደባባይ ሚስጥር ነው።***
ይችን በጣም አጭር ፅሁፍ ለመከተብ ያነሳሳይ ስለ እውነት የቆሙትን ጋዜጠኞች ስም ማጥፋት
በየድረ ገፁ ፅሁፍ ሳነብ ነው።
ወያኔ የራሱ የሆኑ ፦
ልማታዊ ጋዜጠኞች
የፐሮፓገንዳ ጋዜጠኞች
የውሸት ካባ የለበሱ ጋዜጠኞች
እሊናቸውን የሸጡ ጋዜጠኞች
እንዲሁም
ለመኖር ብለን ነው የሚሉ ጋዜጠኞች እንዳሉት ግልፅ ነው።
በነፃ ጋዜጠኛነት ስታደናግሩ የማይታወቅባችሁ መስሏችሁ ይሆን..?ውሸትንም ማውራት ሱስ የሆነባቸው ተለታፊ የገዥው መንግስት አቀንቃኝ እንዳላችሁ እውን ነው።
ለሙያው፣ለህዝቡ በታማኝነት የሚያገለግሉትን ጋዜጠኞች ስም በመለጠፍ የህዝብን አመለካከት መቀየር አይቻልም።
ልማታዊ ጋዜጠኞች ከወያኔ ጋር ተለጥፈው ህዝብን እያስጨረሱ አይደለ እንዴ ሌላውን ጋዜጠኛ ደግሞ ከተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር በማበር ብለው ዘብጥያ ከማውረድ ሌላ መንግስት ምን ስራ አለው።
ተቃዋሚ ድርጅቶች ስለ እውነት ሲዘምሩ እውነት እንዲ ናት ብሎ ጋዜጠኛ እውነት የሆነውን ሲናገር፣ሲፅፍ አብረሃል ተብሎ መፈረጅ ምን የሚሉት ጀብድነት ነው።ልማታዊ ጋዜጠኞች አሉት !! የማያሻማ የአደባባይ ሚስጥር ነው።***
ይችን በጣም አጭር ፅሁፍ ለመከተብ ያነሳሳይ ስለ እውነት የቆሙትን ጋዜጠኞች ስም ማጥፋት
በየድረ ገፁ ፅሁፍ ሳነብ ነው።
ወያኔ የራሱ የሆኑ ፦
ልማታዊ ጋዜጠኞች
የፐሮፓገንዳ ጋዜጠኞች
የውሸት ካባ የለበሱ ጋዜጠኞች
እሊናቸውን የሸጡ ጋዜጠኞች
እንዲሁም
ለመኖር ብለን ነው የሚሉ ጋዜጠኞች እንዳሉት ግልፅ ነው።
በነፃ ጋዜጠኛነት ስታደናግሩ የማይታወቅባችሁ መስሏችሁ ይሆን..?ውሸትንም ማውራት ሱስ የሆነባቸው ተለታፊ የገዥው መንግስት አቀንቃኝ እንዳላችሁ እውን ነው።
ለሙያው፣ለህዝቡ በታማኝነት የሚያገለግሉትን ጋዜጠኞች ስም በመለጠፍ የህዝብን አመለካከት መቀየር አይቻልም።
ልማታዊ ጋዜጠኞች ከወያኔ ጋር ተለጥፈው ህዝብን እያስጨረሱ አይደለ እንዴ ሌላውን ጋዜጠኛ ደግሞ ከተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር በማበር ብለው ዘብጥያ ከማውረድ ሌላ መንግስት ምን ስራ አለው።
ልማታዊ ጋዜጠኞች ለመንግስት ሲያቀነቅኑ በኢቲቪ፣ በራዲዮ ፣በራሳቸው ጋዜጦችና መፅሔቶች ዲስኩር ሲነፉ ምነው ጋዜጠኞች ወገንተኞች አይደሉም ሊሉን ነው እንዴ ? እንዲማ ቢሉንም አንሰማቸውም።
አንድ ጋዜጠኛ ተቃዋሚውን ቢደግፍ ታዲያ ምንም አይገርምም እኮ!እሱም እኮ እንደማንኛውም ዜጋ ነፃነቱ ተከብሮና ስለ እውነት መስክሮ መኖር ይወዳል።
ምነው ታዲያ ልማታዊ ጋዜጠኞች ለመንግስት ጠበቃና አፈ ቀላጤ ሲሆኑ ለእውነት የቆመውን ታዲያ ጋዜጠኛ የእንደዚ ድርጅት አባል ነህ፣ደጋፊ ነህ እያሉ ማሰሩ ለምን አስፈለገ?
ጋዜጠኛውም እኮ ያመነበትን የተቃዋሚ ድርጅት መከተል ፣መደገፍ መብቱ ነው።
…በኢትዮጵያ ምድር፣ በኢህአዴግ መንግስት ‹‹ሃሳብን በነፃ የመግለፅ መብት›› እንዲከበር እና ስርዓቱ ከጠመንጃ ማምለክ ህግን ወደ ማክበር ይመጣ ዘንድ የከፈለው መስዕዋትነት በአንድ መጣጥፍ ተዘርዝሮ እንደማያልቅ ለውጥ ፈላጊው ወገን ብቻ ሳይሆን የአለም ህዝብ ያውቃል።
ጋዜጠኛች በነጻነት ያለ ጣልቃ ገብነት እንዲሰራ እንጂ ልማታዊ ጋዜጠኛ ሆኖ በትግል ላይ ያሉትን ተቃዋሚዎች የሚዲያ እድል እንዳያስፈለጋቸውና ጊዜ እዳያገኙ ማድረግ አይደለም።
ለእውነትና ለህሊናው ያልቆመ ጋዜጠኛ ሲጠየቅ እንደ እንቁራሪት ይመልሳል
እንቁራሪትን ብልቃጥ ውስጥ ከተው ዘግተውባት አለም የቷ ናት ብለው ቢጠይቋት፦ በሙሉ ልብ አለም ይህች ናት ብላ የብልቃጡን ስፋት አመላከተች አሉ።
መንግስት የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ከሀገር እንዲኮበልሉ እያበረታታና ለስቃይ እየዳረጋቸው መሆኑን ይታወቃል።
ጋዜጠኛ ስለ እውነት ሲናገሩ ሲመሰክሩ መንግስት ተብዬው በተለያዩ መንገዶች የኢትዮጵያን መንግሥት ለማዳከምና የሥርዓት ለውጥ በኢትዮጵያ ለማምጣት በግልጽ እየሠሩ ናቸው ብሎ ስም በመለጠፍና ህገ መንግስቱን በመናድ፣የመንግስትን ስም አጉድፏል በሚል ሰበብ፣ህዝብ በማነሳሳት፡“አመፅ ቀስቃሽ” ፅሁፎች በመፃፍ የቃላት መፈራረቅ ክስ በመመስረት የሚያስርበት ሁናቴ ነው ያለው።
ጋዜጠኛው ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ ህጋዊ መብቱን ለማዳከም የሚሰራ ሴራ አምባገነን ስልጣን ውስጥ ብዙ ነው።
እውነታው በተግባር ሲተረጎም መልሱ እስር፣ድብደባ፣ከአገር መሰደድ!!
በኢትዮጵያ ህገ-መንግስት አንቀፅ 29 ላይ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ያለገደብ የተቀመጠ ቢሆንም እኛ አገር ግን ዋጋ እያስከፈ ነው።
ስርዓቱን የሚተቹ ጋዜጦችን ከአደባባይ በማጥፋት የሀገሪቱን የፕሬስ ነፃነት ጉዞ ክፉኛ ወደኋላ መመለሱ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን የሚያስከትል መሆኑን ከግምት ያስገባ አይደለም፡፡
እውነት ያልዋለችበት የዋለ ሰው ደግሞ ነገ ደግሞ በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም !
በአገር ቤትና በውጪ ላላችሁ ለነፃነት ዋጋ የከፈላችሁ፣የታሰራቹ፣የተሰደዳችሁ፣በመታገል ላይ ያላችሁ ነፃነት ናፋቂዎች ክብር ይገባችዋል!!
እውነት ሁልግዜ እውነት ናት!እውነት ተደብቃ አትቀርም!
ነፃነት የሚታገል ጋዜጠኛ በፍራቻ የሚነጥፍ ብዕርም ሆነ በአፈና የሚንበረከክ የትግል ማንነት የለውም!
ነፃነት ለኢትዮጵያ ህዝብ !! ህዝብን በህትመት ነፃነት ማፈን አይቻልም !!!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!
ግልባጭ
ለልማታዊ ጋዜጠኞች
ከሰብኣዊ
No comments:
Post a Comment