የሰው ልጅ በዚህ ምድር ሲኖር እጅግ በርካታ ዓመታትን አሳልፎ እና አዲስም የሚለውን ዓመታት ተቀብሎ ከዚህ ደርሷል፡፡ ማዕበራዊ ሕይወት ደግሞ ሁላችንንም ስለሚያገናኘን በሆነውም ባልሆነውም አንዳችን ከአንዳችን ጋራ ባለመግባባት የነበርንን አንድነት ወደ ልዩነት ወስደን ከዚያም ሲያድር እና ሲውል ደግሞ ወደ ፍጹም ጥላቻ መንዝረነው ባልጀሮቻችንን እንደ ጠላት የምናይ በረካቶች ነን፡፡ ይህን ዓይነት ነገር ስናደርግ እና ስንከተል ብዙ ቆይተናል ዛሬም ግን እዛው ላይ ነን፡፡ እኛ ልባችንን ቸር እና ለፍቅር የተሰጠ መንደር ካላደረግነው ሕይወት ግቧን መታች ለማለት አንችልም ስለዚህ እንዲህ እናድርግ አሁን በይቅርታ የምናለፈው ዓመት መሆኑን ብቻ ሳይሆን ይቅር የሚል ልባችን እንዲሰራ እንፍቀድለት ይቅርታችን በጊዜ አይገደብ፡፡ አዲስ ዓመት ሊገባ ነው ይቅር እንባባል የሚለው እሳቤ ለእኔ አይስማማኝም ቢሆንም ለአዲስ ዓመት ይቅርታ ዓመቱ ሲያልቅ ደግሞ ጥላቻ የምንይዝ ከሆነ ምንም ልዩነት የለውም ይቅር የሚል ከፍጹም ልቡ ይቅር ይበል እኛም ይቅርታን ከፍጹም ልባችን እናድርግ፡፡ እውነተኛው ሰው ይህ ነው እና......
ለመሆኑ ህብረት ወይም ትብብር ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ያልተሞከረ ነውን? የኢትዮጵያንስ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የጎዳው ህብረት አለመኖሩ ነውን? እነዚህ ጥያቄዎች ምንም እንኳ ጥልቅ ጥናት የሚፈልጉ ቢሆኑም ለኔ በደፋናው አይመስሉኝም (ከተሳሳትኩ ለመታረም ዝግጁ ነኝ) በኢትየጵያ ፖለቲካ ከፓርቲዎች ብዛት እኩል ለቁጥር አሰልቺ የሆኑ ህብረቶችና ጥምረቶችን ሀገር ወስጥ ባሉም ከሀገር ውጭ ባሉም ድርጅቶች መካከል አይተናል፡፡ አንዳቸውም ግን መሰረታዊ ለውጥ ሲያመጡ አልታዩም ወይም የተጣመሩበትን ግብ እስኪመቱ እንኳ መቆየት አላቻሉም፡፡ እንደኔ በኢትዮጵያ ውስጥ ጠንካራ ፓርቲ እንዳይኖር ካደረጉት ምክንያቶች እንዱ ይህ “የህብረት” መንፈስ ይመስለኛል፡፡ አንድ ድርጅት ጠንክሮ የመውጣት አዝማሚያ ሲያሳይ ደካሞች የሚጠፉ ወይም የለመዱትን ጥቅማጥቅም የሚያጡ ስለሚመስላቸው ያንን ድርጅት ከነሱ ቁመት እንዳይበልጥ ወይም እራሳቸውን ከነችግራቸው እና ከነድክመቶቻቸው ካለ እነሱ እንዳይጓዝ ለማድረግ ሁሌ በኋላ ኪሳቸው የሚያስቀምጧትን ካርዳቸውን ይመዛሉ “ህብረት” ከዛም የጥፋት ዘራቸውን ይበትናሉ፡፡መቼ ይሆን በይቅርታ መንፈስ ተሞልተን የምንታደጋት በህብረት አገራችንን???
ህኛ ስንብላላ ለበኝ አገራችን እንሰጣለን!
ጠንቀቅ! ጠንቀቅ! ጠንቀቅ!
ከሰብኣዊ
No comments:
Post a Comment