Tuesday, July 23, 2013

***፨ የፍትህ ስርአቱ መሳቂያና መሳለቂያ የሆነበት ዜጋ ዋስትና የሌለው ነው። ህይወቱ ትርጉም የማይሰጡት ዜጋ ነው።፨***

ይድረስ ለህግ ባለሙያው ጓደኛዬ እና ለመሰሎቹ

ህጋዊነትን ያልተከተለ አካሔድ ህገ ወጥነትን እንደሚያስከትል ግልፅ ነው።
ህወሃት/ወያኔ እንደ መሳሪያ የሚገለገልበት የፀረ ሽብር ህግ የፍትህ ስርአቱን ሙሉ በሙሉ እያሽመደመደው እንደሆን በጽናት ቆመው መናገር ያለባቸው ከማናችንም ይልቅ በቅድሚያ የህግ ባለሞያዎች መሆን ይጠበቅባቸዋል። የፍትህ ስርዓት አለኝታ የማይሆነው ህብረተሰብ ኑሮው አንድም እስር ቤት ተፈርዶበት ሁለትም ሸሽቶ በፋኖነት ከመኖር ውጭ ሌላ አማራጭ የለውም።
ይህ በየጊዜው በመበርገግና በመሸበር በደንቆሮ ግምት እነ ወያኔ/ህውሃት በህግ የሚመሩ ለማስመሰል የሚወስዱት እርምጃ የሐገሪቱን የፍትህ ስርአት አደጋ ውስጥ እንደጣለው እንረዳለን
በሃሰት ክስ ወንጀለኛ ለማድረግ የሚፈፀመው የተሳሳተ ተግባር የዜጎች በጋራ አብሮ የመኖርና የመከባበር መሰረት በሆነው ፍትህና ዳኝነት ላይ ይቅር የማይባል ከፍተኛ ወንጀል እየፈፀመ መሆኑ በእጅጉ ያሳዝናል።
በእርግጥ << እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል >>በሚል እምነት የታወሩ መሪዎች የዛሬን እስከ ታደጋቸው ድረስ ነገ የእነሱ ባለመሆኑ የፍትህ ስርአቱ ሊገጥመው የሚችለው አደጋ ደንታ አይሰጣቸውም።

በመፈጸም ላይ የሚገኙት ወንጀል ነገ የሚኖረው ማህበረሰባዊ ጉዳት በሃገርና በወገን የወደፊት ሚዛናዊ ህይወት ላይ የሚያሳርፈው አንድምታ እና ትቶት የሚያልፈው ጠባሳ በቀላሉ እንደ ማይታይ በትክክል መገንዘብ የሚችሉት በህግ የሚያምኑ ኃይሎች ብቻ ናቸው።
የፍትህ ስርአቱ መሳቂያና መሳለቂያ የሆነበት ዜጋ ዋስትና የሌለው ነው ህይወትና ትርጉም የማይሰጡት ዜጋ ነው። መብቱን የሚያስጠብቅለት ጥቃቱን የሚከላከልበት ኃይል የሌለው ዜጋ መሸሸጊያ ካጣ ከዱር አውሬ ተለይቶ ላይታይ ይችላል። ኃይልና ጡንቻ ፣ዉሸትና ቅጥፈት በሚገዙት ህገ ወጥ ስርዓት ውስጥ እንዲኖር የተፈረደበት እስረኛ አድርጎ ራሱን እንዲቆጥር ይገደዳል።
በሐሰት << አሸባሪነት >> ከተከሰሱት ከነ አንዱአለም አንዳርጌ እስክንድር ነጋ ሌሎች በሐገር ዉስጥም ዉጭም ያሉ ተከሳሾች በላይ ዛሬ ወያኔ/ህውሃት ለስልጣን እድሜአቸውን ማራዘሚያ እንዲያገለግሏቸው ክብር የሚያሰጧአቸው ዳኞችና የፍትህ አካላት ወንጀል እየተፈፀመባቸው እደሆነ በህግ የበላይነት የሚያምን ሁሉ ልብ ይለዋል።
የፀረ ሽብር አዋጅን በመጠቀም በፍትህ ላይ የሚፈፀመው ይህ ወንጀል ከተራው ዜጋ ይልቅ በቅድሚያ ሊያስጨንቅና ሊያሳስብ የሚገባው ደግሞ በዘርፉ የተሰማሩትን ባለሞያዎች መሆኑ አያጠያይቅም።
ከፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እስከ ታች በዘርፉ የሚያገለግሉትን የህግ ባለሞያዎቻችን ሁሉ ህሊናቸው በፈቀደ መጠን በቅንነት ለማገልገል በምህላ የተቀበሉት ክቡር የስራ መስክ ነው። አንፃራዊ በሆነ እኩልነት የዜጎች ማህበራዊ ግንኙነት እንዲጠበቅ ሃላፊነት የተቀበሉና የሞራል ግዴታ የተጣለባቸው ዜጎች ተደርገው ስለሚቆጠሩ…………
ወያኔ/ ኢህአዲግ መንግስት ቀናቸው ደርሶ ከመንበራቸው ሲወርዱም ሆነ ሲዋረዱ ዳኞቻችን እንደደረቡት ካባ አውልቀው የሚጥሉት ሙያ አይደለም።
ዛሬ በሃሰት የወንጀል ክስ የተሰየሙት ዳኞችና አቃብያን ህጎች ከህወሃት\ኢህአዲግ ስርአት ዉጭ ነገ ሞያቸውን መተዳደሪያችን አይሆንም በማለት ሌላ የሙያ ስልጠና ወስደው ሌላ ሙያተኛ ሊሆኑ እንደሚችሉ ላንጠራጠር እንችላለን ይሁንና የህግ እውቀታቸው በተሰየሙበት መንበር የሰጡትን ብይን የፈፀሙትን ተግባር በየአጋጣሚው እያነሳ የራሳቸው ህሊና ዳኝነት እየሰጠ ሰላም እንደሚነሳቸው ግልፅ ነው በማህበራዊ ህይወታቸው ውስጥ የትም ይሁኑ የት የህግ ሰዎች ናቸውና የተዛባ ዳኝነትና ሚዛናዊ ያልሆነ ዉሳኔ በገጠማቸው ቁጥር በድፍረት<< ይህ ዉሳኔ ትክክል አይደለም>> ብለው ለማለት የሞራል ብቃት አይኖራቸውም። እንደ ሰው የሚያስቡ እስከ ሆነ ድረስ ዘወትር ህሊናቸው ይሞግታቸዋል። እስከ እለተ ሞት በህሊና ባርነት ዉስጥ ከመውደቅ በላይ የሚሰቀጥጥ የፍርድ ዉሳኔ የለምና።
በዚህ ፍትህ ባጣ ህዝብ ላይ የገዢው መንግስት ሲጫወትበትና ሲቀልድበት ማየት የተለመደ ሆኗል <<ኧረ የፍትህ ያለህ! እያለ በሚጩኽው ህዝብ መቀለድ ዋጋ ያስከፍላል>> በዚህም ምክንያት የፍትህ ስርአቱ ሲዋረድና ፣አልፎ ተርፎ የህግ አዋቂዎቻችን ለፍትህ ስርዓቱ ዘብ በመቆም ፈንታ ደንታ ቢስ ሲሆኑ መመልከት እጅግ ያሳስበናል ነገ የሚያስተዛዝበን ሌላ ቀን እንደሆነ እናውቃለንና…… ነገ ደግሞ በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም!
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment