አስቻለው በላይ
በርዕሱ ወደ ገለጽኩት የዛሬ አስተያየቴ ከመግባቴ በፊት ሰንደቅ ጋዜጣ ሐምሌ 3/2005 ዕትም ላይ አንብቤ ስላዘንኩበትና ስላፈርኩበት ጉዳይ ትንሽ ልበል። ያፓርላማ አባሉና የአንድነት ፓርቲ ም/ል ሊቀመንበር የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ ከጋዜጣው ከፍተኛ አዘጋጅ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ለቀረቡላቸው አብዛኛዎቹ ጥያቄዎች የሰጡዋቸው መልሶች ሁለቱንም ኃላፊነቶቻቸውን የሚመጥኑ ሆነው አለገኘኋቸውም። በፓርላማ ቆይታቸው የሚጠበቅባቸውን ያህል አለመስራታቸውን አስመልክቶ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች “በሚቀጥለው ምርጫ ተመርጠህ ቦታውን ለምን አንተ አትወስደውም፣ በደንብ አልተናገረክም” የሚለኝ ካለ ደግሞ እራሱ በምርጫ ተወዳድሮ ወደ ፓርላማ ገብቶ ሊናገር ይችላል፣ አንተ ተመርጠህ ግባና ስራው አንተ ስትገባ ሰርተህ ታሳየናለህ” ወዘተ በማለት የሰጡት ምላሽ እሳቸውንም በም/ል ሊቀመንበርነት የሚመሩትንም ፓርቲ የሚያስንቅ ነው። አባልና ደጋፊውን ደግሞ የሚያሳፍር። ስለ አንድነት መድረክ ወቅታዊ ሁኔታ ጋዜጠኛው ላነሳው ጥያቄም አቶ ግርማ ሲመልሱ “አላወቅም” ነው ያሉት። ም/ል ሊቀመንበሩ ርሳቸው ያላወቁ ታዲያ ማን ሊያውቅ ነው። የአቶ ግርማ ቃለ መልልስ ብዙ የሚያስብል ቢሆንም የዛሬ ርዕሰ ጉዳዬ አይደለምና በዚሁ ይብቃኝ።
ጠያቂውን ጋዜጠኛ ግን ሳላመሰግን አላልፍም። በርዕሱ ወደ ገለጽኩት የዛሬ አስተያየቴ ከመግባቴ በፊት ሰንደቅ ጋዜጣ ሐምሌ 3/2005 ዕትም ላይ አንብቤ ስላዘንኩበትና ስላፈርኩበት ጉዳይ ትንሽ ልበል። ያፓርላማ አባሉና የአንድነት ፓርቲ ም/ል ሊቀመንበር የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ ከጋዜጣው ከፍተኛ አዘጋጅ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ለቀረቡላቸው አብዛኛዎቹ ጥያቄዎች የሰጡዋቸው መልሶች ሁለቱንም ኃላፊነቶቻቸውን የሚመጥኑ ሆነው አለገኘኋቸውም። በፓርላማ ቆይታቸው የሚጠበቅባቸውን ያህል አለመስራታቸውን አስመልክቶ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች “በሚቀጥለው ምርጫ ተመርጠህ ቦታውን ለምን አንተ አትወስደውም፣ በደንብ አልተናገረክም” የሚለኝ ካለ ደግሞ እራሱ በምርጫ ተወዳድሮ ወደ ፓርላማ ገብቶ ሊናገር ይችላል፣ አንተ ተመርጠህ ግባና ስራው አንተ ስትገባ ሰርተህ ታሳየናለህ” ወዘተ በማለት የሰጡት ምላሽ እሳቸውንም በም/ል ሊቀመንበርነት የሚመሩትንም ፓርቲ የሚያስንቅ ነው። አባልና ደጋፊውን ደግሞ የሚያሳፍር። ስለ አንድነት መድረክ ወቅታዊ ሁኔታ ጋዜጠኛው ላነሳው ጥያቄም አቶ ግርማ ሲመልሱ “አላወቅም” ነው ያሉት። ም/ል ሊቀመንበሩ ርሳቸው ያላወቁ ታዲያ ማን ሊያውቅ ነው። የአቶ ግርማ ቃለ መልልስ ብዙ የሚያስብል ቢሆንም የዛሬ ርዕሰ ጉዳዬ አይደለምና በዚሁ ይብቃኝ።
የሠማያዊ ፓርቲን ሊቀመንበር ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ የሆነ አምባሳደሮች በአሜሪካን ኤምባሲ ጋብዘው ማነጋገራቸውን ከሰንደቅ ጋዜጣ አነበብን። ፈረንጆቹ ይህን ለማድረግ ያበቃቸው የራሳቸው ምክንያት አላቸው። ለስምንት ዓመታት ተዘግቶ ደፋሪ አጥቶ የነበረውን ተቃውሞን በሰላማዊ ሠለፍ የመግለጽ መብት ተግባራዊ አድርጎ አደባባይ ለመውጣት የበቃ መሆኑ ከምክንያቶቹ አንዱና ዋናው እንደሆነ ይገመታል። ረንጆቹ ከብዙ ወሬና ፕሮፓጋንዳ ትንሽ ተግባር ይሻሉ።
በሰልፉ ሊተባበሩ ለስኬቱም አድናቆታቸውን ሊገልጹ ይገባቸው የነበሩ “ፓርቲዎች” ተቃራኒውን የፈጸሙበትና የተናገሩበት ሰልፍ የፈረንጆቹን ቀልብ ስቦ ሠማያዊ ፓርቲን ለዚህ ማብቃቱን ሌሎች ሊማሩበት ቢገባ መልካም ነው። ነገር ግን ሰማያዊ ፓርቲ በተደረገለት ግብዣ ሠይጣናዊ ቅናት አድሮባቸው ለሰልፉ ስኬት የተለያየ ምክንያት እየፈጠሩ እንደተናገሩት ሁሉ ለዚህኛውም የፈረንጆቹ ተግባር የማይታይ ቅጽል እየሰጡ ቢናገሩ ራሳቸውን ነው የሚጎዱት። በተግባር እንጂ በከንቱ ፕሮፓጋንዳ የመኖሪያው ዘመን እየመሸ ነውና።
የሰንደቅን ገጽ በመድረክነት ተጠቅመን (ዝግጅት ክፍሉ ከፈቀደልን) ሠማያዊ ፓርቲን ለአሁኑ ከአይን ያውጣህ እደግ ተመንደግ ብለን እናበረታታው፣ ለነገውም ትንሽ ምክር እንለግሰው ትንሽ አሰተያየት እንስጠው።
ለሠማያዊ ፓርቲ ምስረታ ግንባር ቀደም ባለድርሻዎች ወጣቶች መሆናቸው፣ በሁለት ዓመት ዕድሜው በአባልነት የተቀላቀሉትም በአብዛኛው ወጣቶች መሆናቸው፣ ከፓርቲው አካባቢ ይሰማል። ወጣቶች በዛ አባላሽኝ ዘመን ያልጎደፉ፣ በጥሎ ማለፍ የፖለቲካ ሴራ ውስጥ ያላለፉ፣ በአፍቅሮተ ሥልጣን ያልተለከፉ እንደመሆናቸው የወቅቱን ትግል በአዲስ አስተሳሰብ ለመምራት የአቅም እጥረት (ልምድ ገንዘብ) ይገጥማቸው ካልሆነ በስተቀር ወደ ኋላ የሚጎትታቸው ነገር የለም።
ነገር ግን ግን መተባበር ህብረት መፍጠር አብሮ መስራት በሚለው 21 ዓመት ተግባራዊ ሊሆን ባልቻለ የድክመት መሸፈኛ ልፈፋ ሰማያዊ ፓርቲ ተጠልፎ ታጥቦ ጭቃ እንዳይሆን ያሰጋል። 33ቱ ፓርቲዎች ካልወሰኑ ካልደገፉትና ካልተሳተፉበት ሰልፉ አይሳካም ተብሎ በመገናኛ ብዙሀን ሳይቀር የተነገረው ሠማያዊ ፓርቲን ቢያዘገየው ኖሮ ሰልፉ መቼም ባልተደረገ ነበር።
ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ ብዙ ህብረቶች ተመሰረተ ሲባል እንጂ ህብረት የመሰረቱት ፓርቲዎች አመራሮች ከጥሎ ማለፍ ጨዋታ ወጥተው፣ ከመጠላለፍ ሴራ ጸድተው፣ ይሄ ተብሎ የሚጠቀስ ስራ ሲሰሩ አልታዩም። ቅንጅትም ቢሆን ከዛን መሰል ድልና ያን ሁሉ መስዋእትነት ካስከፈለ ትግል በኋላ አይሆኑ የሆነው በዚሁ ምክንያት ነው። እንደውም ከተግባራቸው እንዳየነው በእኛ ሀገር መተባበር ጠንካሮችና ደካሞች ተባብረው ጥንካሬ የሚፈጥሩበት ሳይሆን ደካሞች ተባብረው ጠንካራውን የሚያዳክሙበት ነው፡
ደካሞቹ የሚጠቀሙበት መተባበር የሚባለው ቃል ዛሬም አላረጅ ብሎ ለተግባር ሳይሆን ለፕሮፓጋንዳ መዋሉን አነደቀጠለ ነው። የፕሮፓጋንዳው አቀንቃኞች ደግሞ ‘የይስሙላው መተባበር’ እነርሱን ለሥልጣን የማያበቃ ከሆነ እንዲኖር አይሹም፣ ሥልጣኑን መመኘታቸው ባልከፋ፣ በእነርሱ አመራር የተገኘ ውጤት ያለመኖሩ እንጂ ክፋቱ። እነርሱ ግን ከውጤት አልባነታቸው ተምረው በእነርሱ አመራር የተከፈለው ውጤት አልባ መስዋዕትነት አስቆጭቶአቸው ራሳቸውን ለውጤታማ መሪነት አያዘጋጁም፣ ወይንም ከሥልጣን ፍቅራቸው አይላቀቁም፤ ወይንም ተተኪ አፍርተው ገለል አይሉም። የዚህ ፓርቲ ሊቀመንበር እየተባሉ መኖር ለአነርሱ ትልቅ ነገር ነው።
በመሆኑም ተከታይ እንጂ ሀሳብ አፍላቂ አባላት በፓርቲያቸው ውስጥ አይኖሩም። አዲስ አስተሳሰብ ለማራመድ፣ ከተለመደውም መንገድ ወጣ ለማለት የሚሞክር ፓርቲ ብቅ ካለም እነርሱን ወደ መቃብር የሚገፋ አድርገው ስለሚያዩት በቀና አለመመልከት ብቻ ሳይሆን ከፊት እንቅፋት በማስቀመጥ ከኋላም በመጎተት ከጎንም በመጋፋት ቢችሉ ለማክሰም ካልሆነም ርምጃውን ለመግታት ይጣጣራሉ። የሠማያዊ ፓርቲን ሰልፍ ለማስቀረት ይደረደሩ የነበሩ አሰናካይ ሰበቦች ለዚህ በቂ ማሳያ ይመስሉኛል። ሰማያዊ ፓርቲ ግን ከቻላችሁ ኑ እሰየው፣ ካልቻላችሁ ደግሞ ቆሜ አልጠብቃችሁም ብሎ የሰበውን በመፈጸሙ ነው ለውጤት ያበቃው። ‘ወደ ኋላ ሄደሽ በሀሳብ ከማለም ቀኑ እንዳይመሽብሸ ትናንት ዛሬ አይደለም’ አይደል ድምጻዊው ያለው።
የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት የሰላማዊ ሰልፉ ዝገጅትና ስኬት ትናንት ከተማሩት በላይ ያስተማራቸው ይመስለኛል። ስለሆነም ፓርቲያቸው በቀጥታ ከሚታገለው ኢህአዴግ በተጓዳኝ ከተቀዋሚውም ጎራ ከፍተኛ ተግዳሮት ሊገጥመው እንደሚችል ወጣቹ ተገንዝበው ታጥቦ ጭቃ እንዳይሆኑ በጥንቃቄ መራመድ ይገባቸዋል።
No comments:
Post a Comment