Wednesday, July 24, 2013

የአዜብ-በረከት የተንኮል እቅድ

መለስ ዜናዊ የስልጣን እድሚያቸውን ለማራዘም ከተጠቀሙባቸው ዘዴዎች አንዱና ዋናውየትግራይ ህዝብ የሥርዓቱ ልዩተጠቃሚእንደሆነ አድረገውበካድሬዎቻችው በኩል ያለመሰልቸት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ማካሄድ ነበር። ይህ ዘዴ የትግራይ ህዝብ
ተጠቃሚ፤ የኢትዮጲያ ህዝብ ግን የበይ ተመልካች ሆኖ እንዲሰማውአድርጎታል። አቶ መለስነፃሚድያሙሉ በሙሉ ሊባል በሚቻል ሁኔታ ስላጠፉትና የኢትዮጵያ ህዝብም የሳቸውየፕሮፓጋንዳ ሰለባ ስላደረጉት እሳቸውየሚናገሩት እና የሚያወሩት እውነት ይሁን ውሸት ለማወቅ ይቸገራል። ውሸት ተደጋግሞ ሲነገረውውሸቱን እውነት ነው ብሎ ይቀበለዋል። አቶ መለስ ኢኮኖሚህ 11 በመቶ አድጓል እያሉ
ነጋ ጠባ ሲወተውቱት፣ ከአመት ወደ አመት ኑሮው እየከፋ፣ ጉልበቱ በረሀብ እየደከመ የሄደው ወገን ውሸቱን እውነት አድርጎ ከመቀበል ውጪ ሌላ አማራጭየለCም።

መለስ የትግራይ ህዝብ አጋዥ አጣ እንጂ በምን አይን እንደሚያያቸውጠንቅቀውያውቃሉ። መለስ እና ኢትዮጵያ እሳትና ጭድ
መሆናቸው ጎልቶ የወጣው በተለይ የኢትዮ-ኤርትራን ጦርነት አክሽፈው፣ የኢትዮጵያ መሬቶችን ለኤርትራ አሳልፈውለመስጠት ባለ
አምስት ነጥብ የሰላም እቅድ የሚል የማጭበርበርያ እቅድ ነድፈው እሱን ለመተግበር ደፋ ቀና ሲሉ በነበረበት ወቅት ማለት ነው!
ቀጥሎም ከመተማ እስከ ጋምቤላ ያለውን እጅግ ለም መሬት ያላንዳች ሀፍረት ለሱዳን እጅ መንሻ ሲያደርጉ፣ ሰውየው ኢትዮጵያን
በሁሉ መንገድ ለማዳከም ቆርጠው የተነሱ እንደሆኑ ታወቀ። ባለፈው አመትም ቢሆን የሻቢያ ሰራዊት በተደጋጋሚ የኢትዮጵያን ድንበር
ጥሶ፣ በሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን አስሮ፣ ያገሬውን የቀንድ ከብቶች፣ በጎችና ፍየሎች እንደልቡ ዘርፎ ሲወስድ፣ መለስሻቢያ ግልጽ ጦርነት
እስካልከፈተብን ድረስ፣ በትንንሽ ትንኮሳዎች ተታለን ዋናውጠላታችን የሆነውንድህነትንከመዋጋት ወደኋላ አንልምሲሉ በኢትዮጵያ
ህዝብና ሀገራዊ ሉዓላዊነት ሲያሾፉ ተስተውለዋል።

መለስ ከክልሎች ሁሉ የሚፈሩት እና ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግለት የሚሹ ቢኖር የትግራይን ክልል ነው። የትግራይ ህዝብ አመፅ ማለት
በሰራዊቱ ውስጥ ያለው ወታደርም አመፀ ማለት ነው። ደግሞ የመለስ የስልጣን እድሜ ያሳጥረዋል። አደገኛ ሁኔታ እንዳይከሰት
ነበር አቶ መለስ ቴዎድሮስ ሐጎስን የክልሉ የበላይ ጠባቂ ያደረጉት። ኤርትራዊውቴዎድሮስ ሐጎስ ከፊሎቹ ወንድሞቹ የሻብያ ተዋጊዎች
ስለነበሩ፣ ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ስትከፈት እና መቀሌ የሚገኘውየአይደር የህፃናት /ቤትን በቦምብ ሲደብደብ፣ ቁጣውን
በሰልፍ የገለፀውየመቀሌ ነዋሪ ህዝብ ከጠየቃቸውጥያቄዎች አንዱቴዎድሮስ ሐጎስንእንዲባረርለት ነበር። አቶ መለስ ደግሞ እራሱ
አስጊ ሁኔታ ውስጥ ቢኖርም፣ ፈራ-ተባ ከማለት ውጪ፣ ከኤርትራ ጋር የወገነውን /ሚኒስቴር ደፍሮ ከስልጣን ሊያባርር የሚችል
የህወሓት ኃይል ስላልነበር፣ ቴዎድሮስ ሐጎስን ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት አውጥቶ ወደ ኃያሉና ታማኙ የፖሊት ቢሮ አባል አድርጎ
ሾመው። ያቺን የመቀሌ ህዝብ ክስ ለመበቀል ነበር ቴዎድሮስ ሐጎስም በምርጫ97 ጊዜትግሬ ወደ መቀሌ፣ ዕቃ ወደ ቀበሌየምትል
መርዝ በቅንጅት ስም አዲስ አባባ ሆኖ የረጫት። የኢትዮጵያ ህዝብሙሉ ድጋፍ የነበረውቅንጅት ለዘር ግጭት ትንኮሳ የተበተነችውን
መርዝ ተጠያቂው ቅንጅት እንዳልሆነ በሚድያ ወጥቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ ለመግለጽ ተደጋጋሚጥያቄ ቢያቀርብምሚዲያውን
የተቆጣጠረውበረከት ስምኦን ግን የቅንጅትን ጥያቄ ሊያስተናግድ ቀርቶ አመራሩን እንዳለ በጅምላ ዘብጥያ እንዳወረዳቸውየትናንቱ
ትውስታ ነው።
ዛሬ መለስ የሉም። ያሉት የአቶ መለስ ባለሟሎች ናቸው። በረከት ስምኦን፣ ሳሞራ ዮኑስ፣ ብርሃነ /ክርስቶስ እና ሌሎች የኤርትራ ዝርያ
ያላቸውሰዎች ዋናውን የስልጣን ቁልፍ ከወ/ አዜብ መስፍን ጋር በመሆን አቶ /ማርያም ደሳለኝን አንደ ጋሪ ፈረስ ከፊት አስቀድመው
እየተጓዙ ይገኛሉ። ፍርሃት እናጭንቀት የሞላበት ጉዞ እንደሆነ ግልጽ ነው።ያለን አማራጭመለስ ሲጠቀምበት የነበረውን ስልት
መጠቀም አለብንእንደሚሉ ልዩ ትምህርትን አይጠይቅም። አንደኛና ዋነኛውደግሞ የትግራይ ህዝብ ከቀሪውወገኑ ጋር እንዳያብር
አሁንም ተነጥሎ የሚመታበት መንገድ መዘየድ የግድ ይላል። ይህን ዘዴ ተግባራዊ ለማድረግ የተመደበችው ደግሞ አዜብ ሆናለች።
መለስ ትግራይን በኢንዱስትሪ ለማልማት 5 አመት እቅድ ነድፎ ነበር” - አዜብ መስፍን
አዜብ ኢህአዴግ ወይም ራስዋ በምትቆጣጠረውቴሌቭዥን ሰሙኑን ታይታ ነበር። ጋዜጠኛዋን ያነጋገረቻች ኤፈርት ቢሮውስጥ ቢሆንም፣
አዜብ ግን አሁንም ሀዘን ላይ የተቀመጠች እንደሆነች ተመልካች እንዲያውቅላት የምትሻ ትመስላለች። ድምጽዋ በልቅሶ የጎረነነ
ታስመስለዋለች።መለስ ትግራይን በኢንዱስትሪ ለማበልጸግ የአምስት አመት እቅድ ጽፎ ነበር!” አለች አዜብ በጎረነነ ድምጽ።
አሃ!ጨዋታ እዚህ ላይ ተጀመረ።
መለስ እሱ ራሱ አልፎ አልፎ ሲናገር እንደተደመጠው ወደ ክልል ወርዶ ጣልቃ ልግባ እንኳ ቢል ጊዜ እና አቅሙእንደሌለው፣ እሱ
የተወጠረው፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ጉዳዮች፣ በአፍሪቃ ቀንድ ፖለቲካ (ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኬንያ ወዘተ) ከዛም አልፎ በአፍሪቃና
በጥቂቶችና በበለፀጉ የዓለም መሪዎች ስብሰባ (G-8 እና G-20) ላይ እየተገኘ በንቃት መሳተፍን እንደሆነ ደጋግሞ ይገልጽ ነበር።
ታድያ ዛሬ / አዜብ ከነበረከት ስምኦን ጋር ሆነውየጠነሰስዋትን ተንኮል ይዘውወደሚድያ በመቅረብ መለስ ትግራይን የኢንዲስትሪ
ማእከል ለማደረግ መጽሀፍ ጽፏል ብለው አረፉት። መለስ ለትግራይ ልዩ የእንዲስትሪ ራእይ ቢኖራቸው ምነው 21 አመት ሙሉ ስልጣን
ላይ በነበሩበት ጊዜ አልተገለፀላቸውም? ይቺ ራእይ የአዜብ እና የበረከትትግራይን የማጥመድ ራእይእንጂ፣ እንደተባለው የልማት
ራእይ ሊሆን ፈጽሞ አይችልም። ደፋርዋ አዜብ አክላምየኔ ኃላፊነት የመለስን ራእይ እውን ማድረግ ነውካለች በኋላ EFFORT
(ትእምት) ኩባንያዎች ዘንድሮ 16.5 ቢልዮን ብር በላይ የሚገመት ምርትና አገልግሎት ለገበያ ለማቅረብ እቅድ ተይዟል አለች።
ለሲሚ ጀሮ እንዲጥም ግን አዜብ ከሁሉ አስቀድማየህዝብ ንብረትስትል የገለጸችውን ኤፈርት ባለፈው አመት ብቻ 376 ሚልዮን ብር
በግብር ለመንግስት ገቢ አድርጓል አለች። ዋናውጥያቄ ደግሞየህዝብ ንብረትከሚሉ ቃላቶች ጋር ይሆናል። እውነት ኤፈረት የህዝብ
ነውን? ከሆነ ታድያ ለምን በድብቅ በአንድ ቤተሰብ ቁጥጥር ስር ዋለ? የህዝብ ከሆነ ህዝቡ የማኔጅመንት ቦርድ አቋቁሞ በየጊዜውለምን
የኤፈርት ገቢና ወጪአንዲያውቅ አልተደረገም?
ከወ/ አዜብ በፊት ኤፈርትን በሥራ-አስኪያጅነት ይዞ የነበረውየመለስ ታማኝ ካድሬ አባዲ ዘሞ (የአሁኑ በሱዳን የወያኔ አምባሳደር)
መሆኑ ይታወሳል። ከአባዲ ዘሞ በፊት ኤፈረትን በመዳፉ አስገብቶ ይቆጣጠረው የነበረውሽማግሌውስብሃት ነጋ ነበር። ታድያ በሱ ጊዜ
በውጭየሚገኙ የህወሓት ደጋፊዎች መሃል ኤፈረት የህዝብ ነውከተባለ ለምን ኦዲት አይደረገም የሚልጭቅጭቅ ተነስቶ ኦዲት መደረግ
አለበት የሚሉ አሽንፈውየውጭአዲተር ቀጥረውወደ መቀሌ ይልካሉ። ወደ ኤፈረት ዋና /ቤት ያመራውየሂሳብ አካውንት መርማሪ
ደግሞ ሽማግሌውን አግኝቶ ለምን እንደመጣ ሲነገረው፣ ስብሃት ነጋ ኃይለ-ቃል በተሞላበት አንደበትበል ሌላ ችግር ሳይከተልህ
ወደመጣህበት ቶሎ ተመለስ!” ብሎ አሰናበተው።
/ አዜብ ደግሞ ከኤፈርት የሚዘርፉት ገንዘብ አልበቃ ብሏቸውየትግራይን ህዝብ ከተቀረውወገኑ ጋር ለማጋጨት ድርጅቱን የፖለቲካ
መሳሪያ አድረገው ለመጠቀም እየተንቀሳቀሱ ያሉት። እዚህ ላይ አንዳንድ ተንኮሉ ያልገባቸውወገኖቻችን የአዜብን ቃል እንዳለ በመውሰድ
ይኸውእነኚህ ዘረኞች ትግራይን ለማልማት እንጂቀሪውየኢትዮጵያ አካል ምናቸውም እንዳልሆን ነውየሚያሳየውእያሉ በጽሁፍ
ሳይቀር ብሶታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። ይኽም ማለት የነ በረከት/አዜብ አደገኛና ከፋፋይ ስትራተጂውጤትማ ሁኗል ማለት ነው።
ምክንያቱም እነሱም ያቀዱት ፕላን ቢኖር፣ ተቃዋሚ ከሚባሉት ክፍሎች በኩል የሚሰነዘረውን አስተያየት ቀንጭቦ በመውሰድ፣ መልሰው
ለትግራይ ህዝብይኸውእኛ ትግራይን በኢንዲስትሪ እናበለፅጋለን ስንል፣ ትምክህተኞችና ነፍጠኞች ግን ያንተን እድገት እየተቃወሙት
ይገኛሉ። እነዚህ ኃይሎችን ነውመፍራት ያለብህ። መድረክም ይሆን ሌሎች ተቃውሚዎች ጠላቶችህ መሆናቸውን ላንድ አፍታም ቢሆን
መዘንጋት የለብህም!” እያሉ ህዝቡን ይበልጥ በወገኑ ላይ እንዲጠራጠር፣ ለውጥ ፈላጊ እንኳ ቢሆንምከማላውቀውመልአክ የማውቀው
ሰይጣን ይሻለኛልወደሚል ድምዳሜ እንዲደርስ ይገደዳል። ስለዚህ / አዜብ ተናገረች ተብሎ እስዋን አምኖ፣ ነገሮችን በሰከነ አእምሮ
ሳያጤኑ ወደ ድምዳሜ እና ወደ ማውገዝ መጓዝ የተቃዋሚውን ጎራ ትግል እንደሚጎድውና ይባስ ብሎ የገዢውን አካል እንደሚያጠናክር
ከወዲሁ መታወቅ ይኖርበታል።
ኢትዮጵያ በልጆችዋ የተባበረ ሃይል ታፍራና ተከብራ ትኖራለች!
ጋሻ ለኢትዮጵያውያን

ሲያትል ዋሽንግተን


No comments:

Post a Comment