Thursday, July 25, 2013

***፨ ተስፋ ቆርጦ፣ ህይወት አበቃለት ከማለት በፊት ከእኔ የከፋም አለ ብሎ ማሰብ ትልቅ መላ ነው፡፡ ፨***

ከዕለታት አንድ ቀን ብዙ ጥንቸሎች ተሰብስበው ይመካከራሉ፡፡ 
አንደኛ ጥንቸል - “ጐበዝ እኔ ኑሮ መሮኛል፡፡ በየአቅጣጫው ጠላት እኛ ላይ እያነጣጠረ መግቢያ መውጪያ አሳጣን፡፡ በየጊዜው መደበቅ፣ ከሰው መሸሽ በጣም ነው ያስጠላኝአለች፡፡ 
ሁለተኛዋ ጥንቸል - “እኔ ደሞ በጣም የሰለቸኝ ከውሻ መሸሽ፡፡ ድንገት ብቅ ካለ እኮ ካለእኛ ጠላት ያለው አይመስለውም፤ ክፉኛ ያባርረናል፣ ያሳድደናልአለች፡፡ 
ሦስተኛዋ ጥንቸል - “እኔ ደግሞ እንደኛው የዱር አራዊት የሆኑ አውሬዎች ናቸው እረፍት የነሱኝ፡፡ ምን እንደሚበጀኝ ንጃአለች፡፡ 
እንዲህ እንዲህ እያሉ ሁሉም ብሶታቸውን ተነጋገሩ፡፡ በመጨረሻም፤እንዲህ ስቃይ ከሚበዛብንና በየቀኑ የሰውም፤ የውሻም፣ የአዕዋፍም፣ የዱር አውሬም ምግብ ከምንሆንና ምንም አቅም የሌለን ፍጡራን ሆነን ከምንቀር በቃ ውሃ ውስጥ ሰጥመን ብንሞት ይሻለናልአሉ፡፡ 

ከዚያም ሁሉም በአንድ ድምጽአሰቃቂውን ህይወታችንን ላንዴም ለሁሌም እንገላገለውበሚል በአቅራቢያቸው በሚገኝ ሰፊ ኩሬ ውስጥ ሰምጠው ሊሞቱ ሩጫቸውን ቀጠሉ፡፡ 
በኩሬው ዳርቻ ብዙ እንቁራሪቶች ተቀምጠው ፀሐይ ይሞቃሉ፡፡ እንቁራሪቶቹ በርካታ ጥንቸሎች ወደነሱ እየሮጡ ሲመጡ ተመለከቱና፤ 
ጐበዝ፣ ጥንቸሎች ሊዘምቱብን ወደኛ እየተንደረደሩ ነው፡፡ በጊዜ ብናመልጥ ይሻለናልተባባሉ፡፡ 
ወዲያው ከኩሬው ዳርቻ ወደ ውሃው ጡብ ጡብ እያሉ በጣም ወደታች ጠልቀው ተደበቁ፡፡ 
ይሄኔ ከጥንቸሎቹ መካከል ብልሁ፤ 
ቆይ ቆይ ቆይብሎ ሁሉንም ጥንቸሎች አስቆማቸው፡፡ 
ሁሉም በርጋታ እሱን ለማዳመጥ ዞሩ፡፡ 
ጥንቸሉም፤ 
አያችሁ፤ ራሳችንን ማጥፋት የለብንም፡፡ ልብ ብላችሁ ካስተዋላችሁ፣ እነዚህ እንቁራሪቶች እኛን ፈርተው ውሃ ውስጥ ገቡ፡፡ እኛንም የሚፈራን አለ ማለት ነው፡፡ እኛ ሌሎችን ፈርተን ራሳችንን እናጥፋ አልን፡፡ በዓለም ላይ ግን ሁሉም የሚፈራው አለው፡፡ ስለዚህ ሌሎች ያጠፉናል ብለን መፍራት የለብንም፡፡ እኛም የምናጠፋው አለናብሎ ሁሉንም መለሳቸው፡፡ 
***
ተስፋ ቆርጦ፣ ህይወት አበቃለት ከማለት በፊት ከእኔ የከፋም አለ ብሎ ማሰብ ትልቅ መላ ነው፡፡ ሁሉም የላይና የበታች አለው፡፡ የህይወት ሰልፍ ይህን ልብ እንድንል ያስገድደናል፡፡ ከጅምላ ውሳኔ መጠንቀቅ ደግ ነው፡፡ የተሻለው ካልተሻለው ጋር መክሮ ዘክሮ ካልተጓዘ አገር የጥቂቶች ብቻ ትሆንና ኑሮ በምሬት የተሞላ ይሆናል፡፡ 
የሀገራችን አሳሳቢ ጉዳዮች አያሌ ናቸው፡፡ በለውጥ ጐዳና ላይ አሳሳቢ ጉዳዮች ከበዙ ለውጡን ማዥጐርጐራቸው አይቀሬ ነው፡፡ ነባራዊ ሁኔታው በፈቀደው የሚከሰቱትን እንቅፋቶች ሁሉ ግንፀረ ልማት፣ ፀረ ዕድገት፣ ኪራይ ሰብሳቢነትወዘተ ብሎ ከመፈረጅ መጠንቀቅ ይገባል፡፡ ሩጫችን በፈጠነ መጠንችኩል ጅብ ቀንድ ይነክሳል አለመርሳት ነው፡፡
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment