Thursday, July 25, 2013

እኛ ደግሞ እንጮሃለን

የተኛም ይተኛ፤ ያንቀላፋም ያንቀላፋ፤ የደከመም ይድከም፤ የተሸነፈም ይሸነፍ፤ አብሮና ተባብሮ የሚዘርፍና የሚያዘርፍ - የሚገድልና የሚያስገድልም - ይዝረፍም ይግደልም፡፡ እኛ ደግሞ እንጮሃለን፤ የሚያነብብ ያንብ፤ የሚሰማ ይስማ፤ ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ እንደጨለመ አይቀርም፤ ያኔ የጨለማው ውስጥ ሲራ በገሃድ ይገለጥና በምን ዓይነት ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ምን ዓይነት የመከራ ሕይወት እያሳለፍን እንደነበር ቀጣዩ ትውልዳችን ይማራል፤ እንዲሆን የታዘዘን ከመሆን የሚያሰናክል የለም፤ ሁሉም በጊዜው ይሆናል፡፡ ጠቢቡ ቀድሞ ተናግሮታል - ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም፡፡
የብርሃንና የጨለማ መፈራረቅም የነበረ እንጂ ዛሬ የተጀመረ አይደለም፡፡ አገኘሁ ብለህ አትኩራ፤ አጣሁ ብለህም ከመጠን ባለፈ አትፍራ፡፡ ይልቁንስ ሰው ለመሆን ጣር - ሰው ሆኖ መገኘት ትልቅ የወቅቱ ፈተና ነውና፤ከገዳይ ይልቅ ሟች የበለጠ የፅድቅ ቦታ አለው፤ ጊዜው ቀርቧል፡፡ ለዚያ ጊዜ ወዮ እንበል!!
**የመከራ ሕይወት እያሳለፍን እንደነበር ቀጣዩ ትውልዳችን ይማራል**

ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment