አንድ ኢትዮጵያዊ የሆነ ሰው የፖለቲካ ፓርቲ ፣ድርጅት በተለያየ ስም ሊያደራጅ ይችላል ችግር የለውም ዋናው ነገር ለህዝባችን የሚጠቅም ሲሆን ደስ ይላል ግን በብሔር ተደራጅቶ ብሔሬን ነፃ ላውጣ ሲል ብሔር ከኢትዮጵያ የተመሰረተ ነው እኮ እረስተውት አይመስለኝም ማላገጥ ካልሆነ በስተቀር! የፖለቲካ ፓርቲ ፣ድርጅት ideology ላይቀበለው ይችላል ይህ ደግሞ የአስተሳሰብ ውጤት ነው ግን ለብሔሬ ፣ለሕብረተሰቤ ሲል ግን ለታላቋ ኢትዮጵያ አይመስልም ! ከኢትዮጵያ ህዝብ ሌላ የሚወደው ህዝብ ሊኖረው ኣይችልም።
ህዝብን መውደድ የኣስተሳሰብ ዉጤት ነው፣ ህዝብ መጥላትም እንዲሁ። ሰው ሰው በመሆኑ ብቻ መውደድ ካልቻልን የዘር ሓረጉ ማጣቀስ የመውደዳችን ምንጭ ሊሆን ኣይችልም።
ምክንያቱም እኛ (ሁላችን) በወላጆቻችን በኩል ስንወለድ በፍቃዳችን ወይ ያለፍቃዳችን ኣይደለም። ከሆኑ ሰዎች ከሆነ ቦታ በሆነ ግዜ ተወለድን ፣ወደዚች ዓለም ተቀላቀልን። ከዛም መወለዳችን ፣መምጣታችን ወደድነው፤ ምክንያቱም የኛ መወለድ የተፈጥሮ እንጂ የምርጫ ጉዳይ ኣይደልም።ህዝብን መውደድ የኣስተሳሰብ ዉጤት ነው፣ ህዝብ መጥላትም እንዲሁ። ሰው ሰው በመሆኑ ብቻ መውደድ ካልቻልን የዘር ሓረጉ ማጣቀስ የመውደዳችን ምንጭ ሊሆን ኣይችልም።
ተፈጥሮኣችን ሰው ሁነን መገኘታችን ያልወደደልን ሰው ወይ ድርጅት ‘ከማንና የት’ እንደተወለድን እንደ መስፈርት ተጠቅሞ ቢወደን ለፖለቲካ ፍጆታ መመፃደቅ እንጂ እውነት ሊሆን ኣይችልም። ምክንያቱም እኛነታችንን (ተፈጥሮኣችንን) ያልወደደልን ሰው እንዴት ሁኔታችንን (የተወለድንበት ቦታና የመጣንበት ብሄር) ሊወድ ይችላል?
ስለዚህ አንድ (ወይ ብዙ) ብሄር ጠልተን ሌላው እንደምንወድ ስንገልፅ ከማላገጥና ከግብዝነት ዉጪ ሌላ ትርጓሜ ሊሰጠው አይችልም። መውደዳችን ካልቀረ ሰው እንደ ብሄር ሳይሆን እንደ ሰው እንውደደው። ሰው እውነትና የተፈጥሮ ስጦታ ሲሆን ብሄር ግን የማሕበራዊ (ሰው ሰራሽ) አስተሳሰብ ውጤት ነው።
ከሰብኣዊ
No comments:
Post a Comment