ኢትዮጵያን አናፈቅራትም”የሚሉት ኢትዮጵያውያን፦ኢትዮጵያን ለምን አላፈቀሯትም? ከማለታችን በፊት፤እኔስ አገሬ ኢትዮጵያን ማፍቀሬን በምን እገልጸዋለሁ? ብዬ ራሴን በግልፅ መጠየቅ አለብኝ፤ እያንዳንዳችንም ራሳችንን ልንጠይቅ ይገባናል።ያለ-በቂ እና ያለ-አሳማኝ ዝርዝር መረጃ፣በስሜት ብቻ አገሬን ማፍቀሬ ወይም አገሬን መጥላቴ በአገሬ ጉዳይ ላይ መብትና ግዴታዬን እንዳውቅ አያደርገኝም። እናም ለምንድን ነው ኢትዮጵያን አናፈቅርም በሚሉት ዜጎች የማፍረው?እነሱ “አናፈቅራትም፣ አንወዳትም፣ብትንትኗ ይውጣ፣ የተረገመች ትሁን፣ዘሯ እንደአሸዋ የበዛ ሳይሆን እንደጭቃ ተመርጎ ይቅር፣ በሕይወትም ያሉት በቁማቸው ይሙቱ፣እንዴ ሳይሆን ሁለቴ ዽብን ይበሉ፣”እያሉ በራሳቸው ጊዜ በእማማ-ኢትዮጵያ እና በዜጎቿ ላይ ዝምታቸውን እያየሁ ሕሊናዬ እንደምን ይቀበለዋል?እማማ-ኢትዮጵያ ምን አደረገች?ይልቅስ በስሟ ዜጋ ነኝ የሚለው ነው በዜጎቿ ላይ የሰው ሥጋ ለብሶ መዓቱን ያወረደባቸው።
ብዙ ከማለቴ በፊት በሐቅ እንነጋገርና እያንዳንዳችንን ራሳችንን እንጠይቅ፦ለምንስ አገሬ ኢትዮጵያን እወዳታለሁ?ለምንድንስ አንድ ሰው አገሩን ይወዳል? ሁላችንም አገራችንን የመውደዳችን መ-ገ-ለ-ጫ-ው ምንድን ነው?አዎ ለነዚህና ለሌሎች መጠይቆች ተገቢውን ምላሽ በሕሊናችን ውስጥ ካላስቀመጥን የአገር ፍቅር-ተግባር ሊኖረን አይችልም።ፍቅሩ ከሌለን ደግሞ ደንታ ቢሶች እንሆናለን።አዎ!የአገር ፍቅር ምክንያት በትክክል አለመታወቅ እና ከዜጎቿ መካከል ከአገር በላይ ነን የሚሉ ስላሉ ነው የሚምታታው።በመጀመሪያ እያንዳንዱ ዜጋ አገር ሊኖረው ይገባልና፤የእኔ፤የግሌ አገሬ ኢትዮጵያ ነች እንበል።አገርህ/ሽ የት ነው ተብለን ስንጠየቅ ኦሮምያ አሊያም አማራ ከሆነም ትግራይ ብለው መልስ የሚሰጡ ከመሃይማን መንግሥት ነኝ ባይ ገዥ ቡድን የቀሰሙት ሳይሆን የጋቱት(ዝንብ አትቀስምምና)ምላሽ ነው።አገሬ ኢትዮጵያ ነው ማለት፤ሐረርም፤ጎጃምም፤ ትግራይም፤ አሩሲም፤ጂማም፤ጎንደርም፤ወለጋም፤ጎሞጎፋም፤አዲስ አበባም፤ባሌጎባንም ሁሉ አራቱንም ማዕዘናት እና በጠቅላላው ግዛቷ ያሉትን ሁሉ ያጠቃልላል፤ኢትዮጵያዊነት።ለምሳሌ ሥማችንን ስንጠየቅ፦አዎ ከሥም በኋላ አባት እና አያት ተጨምሮ ይነገራል፤እንደው በየትኛው አገር ነው ሥም ሲጠየቅ የእናቱን ሥም የሚናገር???ፀረ-አንድነት ስርዓት ለማስረፅ የደከመበት የባንዳዎች ቡድን የጅል ዘዴ መሆኑ ነው እንጂ።ጉጅሌው የ”ኢትዮጵያን”ሥም ሊያጠፋ አልቻለምና ንብ ሳይሆን ዝንብ መሆኑ ስለተረጋገጠበት፦መልሱ ሁሉ”በቅሎ አባትህ ማነው ቢሉት”ሆነ፦አህያነታቸው እንዳይታወቅ።እናም በተፈጥሮዋ ለም የሆነችው አገራችን ኢትዮጵያን “እናለማታለንiii” በሚሉ የባዕዳን-ድሐዎች እንድትቦጫጨቅ አድርገው ንብ ነን ሲሉ የነበሩት የጉጅሌ ገዥ ቡድን፦ጀሌ ዝንቦቹን አደራጅቶ እና ባንዳ አጋሮቹን አሰልፎ እስከወዲያኛው ትውልድ የማያልቅ ዕዳ ሊያሸክመን ይሄው ሃያ ሁለት ዓመታት ሙሉ በዝርፊያ ኢትዮጵያን አቁስሏታል።ታዲያስ የማን አገር ነች?ያንተም ያንቺም የሁላችንም አገር አይደለችም?አሁንም እየቆሰለች ያለችው??
በሁለተኛ ደረጃ አገራችን ኢትዮጵያ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ያለምንም ልዩነት በእኩልነት ደረጃ “የእኔም ነች”ብሎ በሙሉ ልብነት በነፃነት ሊኖርባት የሚገባ አገር ናት።በእርግጥ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በነፃነት እና በእኩልነት የምንኖርበት አገራችን ናት?የሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ መብት ከአገር ፍቅሩ እና ከመስዋዕትነቱ ዋጋ ጋር እንደ ድምጻችን እኩል ናቸው?ይህ ሐቅ በግልፅ መታወቅ ያለበት አንዲቷም መብታችን ልትሰነጠር ስለማይገባት ነው።ከግለሰብ መለኮታዊ ሥጦታ አንፃር መሠረታዊ ሕልውናዬን ያለምንም ድርድር የሚያሳጣኝ ኢትዮጵያዊ ዜጋም ሆነ የባዕድ አካል ሊኖር አይገባም።በሰብዓዊነቴ ብቻ በማናቸውም መንገድ ሊደፈር የማይገባው የኔን ነፃነት ማስጠበቅ ኃላፊነቱ የኔው ብቻ መሆኑን ስለማምን፤ልዋጋውም የትውልድ ግዴታ አለብኝ።
ሦስተኛው እና የመጨረሻው፦የኔም ቤተሰቦች ከትውልድ ወደ ትውልድ ለኢትዮጵያ ደማቸውን አፍስሠው፤ሥጋቸውን ቆርሰው እና አጥንታቸውን ከስክሰው በነጻነት ያቆዩልኝ አገሬ ናትና ይህ ዕዳ ዋጋ ሊኖረው ይገባል።እንዲህ ፀረ-ነፃነት ድርጊት ለማድረግ የተደራጁ ካሉ ደግሞ እኔም ከወገኖቼ ኢትዮጵያውያን ጋር ወግኜ እንደቀድሞዎቹ ዘር-ማንዘሮቼ እስከሞቴ ድረስ እፋለማቸዋለሁ።ይህም ደግሞ ስለተባልኩ ሳይሆን አምኜበት በመሆኑ እምነቴም ነፃነቴ ነውና ነጻነቴን የሚያሳጣኝን ግለሰብ፣ቡድን፣አካል፣ባለሥልጣን ወይም በሌላ ዓይነት መልክ የተሰሩ ግኡዛን ፍጥረታት ሁሉ በክንዴ ሊወገዱ ይገባልና ነፃነቴን ለማስጠበቅ እስከ ሕይወቴ መጨረሻ ድረስ፦የደም፣የሥጋና የአጥንት መስዋዕትነት እከፍላለሁ።እኔ ፈቃደኛ ባልሆንም በጭካኔ ያስከፍሉኛል፤እናም ምንድነው ልዩነቱ?እኔ የምከፍለው ለነፃነቴ እነሱ ግን ለባርነት ነው።
በተዘረዘሩት ሦስት አበይት ምክንያት እያንዳንዳችን ግንዛቤ ያለን”ኢትዮጵያን አናፈቅራትም”ለሚሉት ኢትዮጵያውያን፦እግዚአብሔር የሰጠን ኢትዮጵያችን ምንም አድልዎ እንዳላደረገች ለማሳየት ሰዎች እንደተወለዱባት ራቁታቸውን እንደማንኛውም ሰው እንደሚሞቱባት ማስረዳት ይኖርብናል።በተግባራቸውም መልካም ያደረጉ ሲመሰገኑ፤ከትውልድ ትውልድ የሚረገሙባት ጨካኞች እና አረመኔዎች ደግሞ ወደፊትም ሐቁ እየወጣ አጥንታቸው ተፈልጎ እንደጋዩ እንድሚደረግ ሊጋቱ ይገባል።ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጉሮሮ ነጥቀው በሌሎች አገሮች ባማሩ ቪላዎች ትሸሽገው የደም ሐብት እየጠጡ ለሚኖሩ የመለሰ ዜናዊም ሆነ የሌሎች አምባገነን ሎሌዎች እየቃዡ ይኖሯታል እንጂ እንደናዚዎች እየታደኑ ባደባባይ ደም ይከፍሉባታል።
እናም በአረንጓዴው አገላለጽ:- ልምላሜዬን፣በቢጫው ምልክቴ:-ዕምነቴን እና በቀዩ ትግል:-መስዋትነቴን እንደገለፅኩት የእኔ የዜግነት ድርሻዬ ከነፃነቴ ላይ ቅንጣት እንዳይነካ በተደራጀ አመራር ውስጥ መስዋዕትነት እከፍላለሁ።ይህንን ሐቅ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊም በሚገባ ተረድቶ ሕሊናው በንቃት እየጠበቀ ከምር እንዲታገል የሁለታችንም-ዝምታ:-[ዝም-ያሉት]እና[ዝም-ያሉት
No comments:
Post a Comment