Wednesday, July 24, 2013

መኢአድ የውስጥ ችግሩን ሳይፈታ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ  አቶ አበባው መሐሪን በፕሬዝደንትነት መረጠ


በፋኑኤል ክንፉ

በኢንጅነር ኃይሉ ሻውል ከአስር ዓመታት በላይ ሲመራ የነበረው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ሐምሌ 13 እና 14 ቀን 2005 . ጠቅላላ ጉባኤ ማድረጉን ተከትሎ ሌላው የመኢአድ አመራር ቡድን አባላት የተካሄደው ጠቅላላው ጉባኤ ሕገወጥ ነው ሲሉ ጉባኤውን ውድቅ አድርጓል።
መኢአድ በሶስት የተለያዩ የአመራር ቡድኖች የተከፈለ ፖለቲካ ፓርቲ መሆኑ በስፋት የተዘገበ ጉዳይ ነው። ሶስቱን የአመራር ቡድኖች በበላይነት የሚመሩት የነበሩት ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል (አምስት ሥራ አስፈፃሚዎችን በመያዝ) አቶ አሠፋ /ወልድ (አስር ሥራ አስፈፃሚዎችን በመያዝ) አቶ ማሙሸት አማረ (ሶስት ሥራ አስፈፃሚዎችን በመያዝ) መሆኑ ይታወቃል። የእነዚህ የፖለቲካ ሃይሎች አለመግባባት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀርቦ በጋራ በመኢአድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ልዩነታቸውን አቅርበው እንዲፈቱ አቅጣጫ መቀመጡም የሚታወስ ነው።

ይህ በእንዲህ እያለ በአቶ ኃይሉ ሻውል የሚመራው የመኢአድ አመራር ሐምሌ 13 እና 14 ቀን ባደረገው ሶስተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ፓርቲውን ለቀጣዩ ሁለት ዓመታት በፕሬዝደንትነት እንዲመሩ አቶ አበባው መሐሪን መምረጡን አስታውቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ የምርጫውን ሕጋዊነት ለመከታተል የሰው ሃይል ማሰማራቱን ገልፆ፣ ሪፖርቱን አጠናክሬ አልጨረስኩም፤ ለጊዜው የምለው የለኝም ሲል ለዝግጅት ክፍላችን አስታውቋል።
የዚህን ጠቅላላ ጉባኤ ሕጋዊ ነው ወይስ አይደለም ከሚሉት ወገኖች መካከል፣ በኢንጂነር ኃይሉ ሻውል አመራር ከሚመሩት መካከል የፓርቲውን ዋና ፀሐፊ አቶ ተስፋዬ ታሪኩን እና ጠቅላላ ጉባኤው ሕገወጥ ነው የሚል መከራከሪያ ከሚያነሱትና በአቶ አሠፋ /ወልድ ከሚመራው የመኢአድ አመራር መካከል፣ የመኢአድ ሥራ አስፈፃሚና የትምህርትና ስልጠና ክፍል ሃላፊ የነበሩትን አቶ ጌታቸው ባያፈርስን አነጋግረናቸዋል።
የተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ኮረም ሳይሞላ የተደረገ ነው። ምርጫ ቦርድ ባቀረበው አቅጣጫ የተፈፀመ አይደለም። ጉባኤው -ዴሞክራሲያዊና ሕገ ወጥ ነውሲሉ አቶ ጌታቸው ተከራክረዋል። በአሁኑ ጉባኤ የመኢአድ ዋና ፀሐፊ ሆነው የተመረጡት አቶ ተስፋዬ በበኩላቸው ሲመልሱጉባኤው ሕጋዊ ነው። ምክንያቱም፣ 2003 .. ባደረግነው ጠቅላላ ጉባኤ 80 የላዕላይ ምክር ቤት አባለት ነበሩ። ከእነዚህ ውስጥ የታገዱ፣ በራሳቸው ፈቃድ የለቀቁ አባላት ስለነበሩ አሁን የቀሩት የምክር ቤቱ አባላት 65 ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ የምርጫ ቦርድ አባላት በተገኙበት 53 አባላት ተገኝተዋል። ዘይግተው የደረሱ አባላት በመኖራቸውም በኋላ ላይ አራት ተጫማሪ አባላት ተደምረው 57 አባላት በጉባኤው ተገኝተዋል። በመተዳደሪያ ደንባችንም ሃምሳ ሲደመር አንድ በመሆኑ ስብሰባውን ያካሄድነው በሕግ አግባብ ነው። ሥራ አስፈፃሚውን በተመለከተ ከሁለት ዓመት በፊት 18 አባላት የነበሩበት ነበር። በእነማሙሸት አማረ የተፈጠረው አንጃ ከተወገደ በኋላ እና በሐምሌ 30 ቀን 2003 .. ምክር ቤቱን በመጥራት ደንቡ በሚያዘው መሰረት እጩዎች አቅርበን ማሟያ ምርጫ አድርገን ተክተናል፤ እየሰራንም እንገኛለን። በዚህ ጠቅላላ ጉባኤ ላይም 13 የሥራ አስፈፃሚ አባላት ተገኝተዋል። ጠቅላላ ጉባኤው ሲጀመር የተገኙት 257 አባላት ናቸው። ስብሰባ ከተጀመረ የመጡት የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ተጨምሮ ግን 300 አባላት ተገኝተዋልብለዋል።
ከምርጫ ቦርድ ጋር ተያይዞ ለተነሳው አቶ ተስፋዬ ሲገልፁ፣ለምርጫ ቦርድ በወቅቱ ለላከው ደብዳቤ ምላሽ ሰጥተናል። ምርጫ ቦርድ ያለው ኃላፊነት ፓርቲዎች በራሳቸው መተዳደሪያ ደንብ እየሰሩ መሆናቸውን መከታተል ነው። ይህ የምርጫ ቦርድ ክትትል እንቀበላለን። ሆኖም በፓርቲዎች የውስጥ ጉዳይ ላይ ግን ይህ አድርግ፣ ያን አታድርግ የሚል ስልጣን የለውም። ለምርጫ ቦርድም በፃፍነው ደብዳቤም ላይ እንደገልፅነው ይህን ጥራ፣ ያን ይዘህ ተሰብሰብ የሚል ስልጣን እንደሌለው አስረድተናል። ምርጫ ቦርድም ይህን ተገንዝቦ ማሟላት ያለብን አሟልተን በመጨረሳችን 2005 .. የምስጋና ደብዳቤ ጽፎ ሰጥቶናል። ስለዚህም የቀረ ደብዳቤ ነው። ምርጫ ቦርድም ጥያቄ አንስቷል። እኛም በመተዳደሪያ ደንባችን ላይ እንደተቀመጠው፣ በሁለት ዓመት ወይም በሁለት ዓመት ከስድስት ወር ጠቅላላ ጉባኤ እንድናደርግ ስለሚያዝ ስብሰባውን አካሂደናል ብለዋል።
የአቶ ተስፋዬ አስተያየት ግን አቶ ጌታቸው ባያፍርስ አይቀበሉትም። አቶ ጌታቸው እንደሚሉት፣ጠቅላላ ጉባኤውን በተመለከተ ምርጫ ቦርድ ሶስት ጊዜ ደብዳቤ ጽፏል። ጉባኤው መደረግ የነበረበት በታህሳስ ወር ነበር። ከዚህ አንፃር ጉባኤው መደረጉ ተገቢ ነው። ሆኖም ግን ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ሶስት ቦታ የተከፋፈለው የመኢአድ አመራር ልዩነታቸውን ለጉባኤው አቅርበው ማነው ትክክል? ማነው ጥፋተኛ? የሚለውን ለማየት ዝግጅት ጨርሰን ባለበት ሁኔታ ፕሬዝደንቱ እሳቸውን ከሚመስሉ ብቻ ጋር ጠቅላላው ጉባኤ ማካሄዳቸው ሕጋዊ መሰረት የለውም፤ ሕገ ወጥ ነውብለዋል።
ሁለተኛው፤ በምርጫ ቦርድ በሥራ አስፈፃሚነት የተመዘገቡና ምርጫ ቦርድ በራሱ ደብዳቤ አውቃቸዋለሁ ብለው በስም ከጠቀሳቸው 18 የሥራ አስፈፃሚ አባላት መካከል በጉባኤው የተገኙት 5 ብቻ ናቸው። 105 የላዕላይ ምክር ቤት ተመራጮች አባላት መካከል 65 አባላት አልተገኙም። ይህን መረጃ የምርጫ ቦርድ አባላት ስብሰባውን ለመታዘብ በመጡበት ሰዓት አስረድተናቸዋል። ምንም እንኳን ምርጫ ቦርድ ለሶስት የተከፈለውን አመራር የጋራ ሪፖርት በጠቅላላ ጉባኤው ላይ ቀርቦ ሪፖርት እንዲደረግለት ቢያሳስብም፣ ወደ ጠቅላላ ጉባኤ ውስጥም እንዳንገባ መከልከላችን ለምርጫ ቦርድ ታዛቢዎች ነግረናቸዋል፣ እነሱም አይተዋል። ጉባኤተኛውም እኛ ወደ ጠቅላላ ጉባኤ ውስጥ እንድንገባ ጥያቄ አቅርቧል። ተቀባይነት ግን አላገኝም።
ሶስተኛ፣ የጠቅላላው ጉባኤ ኮረም ሞልቷል የሚባለው እስከ 450 ድረስ ነው። ምክንያቱም 2002 ጉባኤ ላይ የጠቅላላው ጉባኤ አባላት ቁጥር 816 ነበር። ይህ ከቅንጅት መልስ መኢአድ ራሱን በአዲስ መልክ በማደራጀት የጠራው ጠቅላላ ጉባኤ በመሆኑ እንደመነሻ እንዲወሰድ ተወስኗል። 2003 .. በተደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተገኙት የአባላት ቁጥር 400 በላይ በመሆናቸው በዚህ ጠቅላላ ጉባኤ ከዚህ በታች ቁጥር መሆን የለበትም። በመተዳደሪያውም ደንብ መሰረት ጠቅላላ ጉባኤውን ለማካሄድ ሃምሳ ሲደመር አንድ (50) መሆን እንዳለበት ስለሚደነግግም ከየትኛውም እቅጣጫ ጉባኤውን ብትመለከተው ሕገ ወጥ ጉባኤ ነውሲሉ ጉባኤውን ተቃውመዋል።
አያይዘውም አቶ ጌታቸው ሲናገሩ፣የሚገርመው በአቶ አሠፋ /ወልድ እና በአቶ ማሙሸት አማረ የሚመራው አመራር ወደ ጉባኤው ለመግባት ጭቅጭቅ ውስጥ እያለ ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል ይህን በማወቃቸው ወደ መኖሪያ ቤታቸው ተመልሰው ሄደው ነበር። የሳቸውን መሄድ ተከትሎ አቶ አበባው መሀሪ እና አቶ ተስፋዬ ታሪኩ መድረኩን ለመምራት ሲሞክሩ ከጉባኤው ተሳታፊዎች ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል። በፓርቲው ደንብ መሰረት ፕሬዝደንቱ ነው ጠቅላላ ጉባኤውን መምራት ያለበት። ፕሬዝደንቱ በማይኖሩበት ጊዜ /ፕሬዝደንቱ ነው የሚመራው። /ፕሬዝደንቱም በጉባኤው ውስጥ ነበሩ። ይህን መተዳደሪያ ደንብ በመጣስ ነበር እነዚህ ሁለት ግለሰቦች ስብሰባውን ለመምራት ሲሞክሩ ጉባኤው ያወገዛቸው። የተፈጠረው ነገር ለፕሬዝደንቱ በስልክ ተነግሯቸው ከሰዓት በኋላ በጉባኤው ላይ ተገኝተው ነው፣ ጉባኤውን የመሩት። በቀጣይ በተደረገው ምርጫም /ፕሬዝደንቱ ተሰናብተዋል። የፕሬዝደነት ምርጫውም አቶ አበባው መሐሪ እና አቶ ተስፋዬ ታሪኩ ቢጠቆሙም፣ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ ለእኔ የምትሰጡትን ድምጽ ለአቶ አበባው መሐሪ ስጥዋቸው በማለታቸው አቶ አበባው መሐሪ ፕሬዝደነት ሆነው ተመርጠዋል ተብሏል። ይህ ፈጽሞ በምርጫ ሕግ የሚፈቀድ አይደለም። ፕሬዝደነት በምርጫ እንጂ በሰዎች በጎ ፈቃድ የሚገኝ አይደለም። በአጠቃላይ -ዲሞክራሲ እና ሕገወጥ ጉባኤ ነውብለዋል።
አቶ ተስፋዬ ምርጫው በተመለከተ የተሠነዘረውን ሃሳብ አይቀበሉትም። እሳቸው እንደሚሉት ከሆነ፤የምርጫው ሂደት የተሳሳተ መሆኑ በጽሁፍ የሚገልጽ አንድም ሰው አይኖርም። እኔ ነኝ ከምርጫው  ራሴን ያገለልኩት። የወሰድኩት ውሳኔ ለፓርቲው ይጠቅማል ከሚል መነሻ  ነው። አሁን ባለሁበት ደረጃ መኢአድ የሚያህል ትልቅ ፓርቲ ለመምራት ስለሚያስቸግረኝ ውስጤም በማመኑ ከውድድሩ ራሴን አግልያለሁ። ስለዚሀም ለእኔ የምትሰጡትን ድምጽ ለአቶ እከሌ ስጡ ብያለሁ። ይህ አይነት አሰራር በየትም ሀገር የተለመደ ነው። ስለዚህም ይህ ሂደት ሕገ ወጥ ነው የሚባልበት ሁኔታ ያለ አይመስለኝምሲሉ ተከላክለዋል።
ለጉባኤው የቀረበው የኦዲት ሪፖርት የተሳሳተ ነው፤ ገቢው 300 ሲሆን ወጪው ግን 600 ነው የሚሉ የስብሰባው ተሳታፊዎች አሉ። በዚህ ላይ የእርሶ አስተያየት ምንድን ነው ተብለው ለቀረበላቸው አቶ ተስፋዬ በሰጡት ምላሽ፤የተባለው ቁጥር ፈጽም የተጋነነ ነው። በርግጥ ወጪው የተጋነነ ነው የሚል ነገር አለ። ይህ እንግዲህ በሂሳብ አሰራር ስህተት ተፈጥሮ ሊሆን ይችላል። አዲሱ ሥራ አስፈፃሚም ይህን ተከታትሎ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ጠቅላላ ጉባኤው ሃላፊነት ሰጥቶታልሲሉ መልሰዋል።


No comments:

Post a Comment