Friday, July 26, 2013

***የኗሪ አኗኗሪ ***

ተቀጣሪ ሠራተኛ በመንግሥትም ሆነ በግል ተቀጥሮ መሥራትን ባይፈልግ አይፈረድበትም፡፡ የኗሪ አኗኗሪ ሆኖ በሀገሩና በቀየው በርሀብ አለንጋ እየተገረፈ ከሚሞት በማያውቀው ሀገር ተሰድዶ ከሁለቱ ዕድሎች በአንደኛው እንደፍጥርጥሩ መሆንን ይመኛል - መሞት ወይም መዳን፡፡ በሀገሩ የበይ ተመልካች ሆኖ ነቀዞችና ግሪሣዎች የገዛ ሀብት ንብረቱን ሲመዘብሩና እርሱን ለከፋ ድህነት ሲዳርጉ ከሚያይ ዐረብ ሀገርና አፍሪካ ሀገራት አይደለም የቀይ ባሕር ዓሣና በበረሃ እያደፈጡ የሰውነት አካልን ለመለዋወጫነት የሚዘርፉ ሽፍታዎች ሲሳይ መሆንን ይመርጣል - ሲጠየቁ መልሱ ይህ ነው - እዚህም ሞት ነው - እዚያም ያው ሞት ነው፤ የሞት ደግሞ ነጭና ጥቁር የለውም፡፡

በበኩሌ ይህን የወጣቶቹን መጥፎ ምርጫ መደገፌ አይደለም፡፡ 
ነገር ግን እኛን በነሱ ቦታ ተክተን ስናስበው የምርጫዎች መጥበብ የማያስደርጉት ነገር እንደሌለ መረዳት አይከብደንም የሚል ግምት አለኝ፡፡ ሰው ሲጨክንብህ፤የኔ ዜጋ ነው፤ አለኝታውና ዋስ ከለላው ልሁንለትየሚልህ ተቆርቋሪ መንግሥት በሀገርህ ስታጣ፣ የኔ መንግሥት የምትለው አንተን እንደባይተዋር ቆጥሮ የእንጀራ ልጁ ሲያደርግህና እርጎውንና ዐይቡን የኔ ለሚላቸው ወገኖች እየሰጠ ለአንተ ሞትንና እሥራትን የሚያከፋፍልህ ከሆነ ምርጫህ እግርህ ባወጣ ያቺን የሲዖል ምድር ኢትዮጵያ ለቅቀህ መሄድ ነው(የሲዖል ምድር ኢትዮጵያ አድራጊው መንግስት ተብዬ ነው ኢትዮጵያማ ቅድስት ነበረች )፡፡ 
ዜጎች እያደረጉ ያሉትም ይህንኑ ነው፡፡ ለአፍ አቀበት የለውምና መንግሥትና አሽቃባጭ የጥቅም ተጋሪዎቹ በያዙት ሚዲያ ቢያሽቃብጡ ሰርቆ እንጂ ሠርቶ ሊያልፍለት የሚችለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር እጅግ አነስተኛ በመሆኑ አምላከ ኢትዮጵያ ፊቱን እስኪመልስልን ድረስ ያለን ብቸኛ አማራጭ ስደትና ፍልሰት ነው።
እንደኔ ይህ ባይሆን ምርጫዬ ነው አላበረታታምም ሁሉም ምርጫው ስደት ከሆነ ይህችን አገር ማን ነፃ ያውጣት፡፡ እናም ይህንከሠራህ በሀገርህ ያልፍልሃልየሚሉትን ፈሊጥ ራሳቸው ለራሳቸው ይዘምሩት፤ ሠራሁ ፣ለፋሁ፣ ግን ምን ተጠቀምሁ? የሚለው በዝቷል ከመልካም አስተዳደር ጉለቶች የመጡብ ዘርፈ ብዙ ችግሮች አሉባት ኢትዮጵያ
ባይገርማችሁ ለስደት የተነሳሳው ደህና ሥራ ያለው ሁሉ ነው፤ ሁሉም ሕዝብ ነው ለስደት የጓጓው ማለት ይቻላል፡፡ ግን ዕድሉ ጠባብ ነው፡፡ ነጋዴውም ስራውን ላሳድግ ሲል፣ህብረተሰቡ ልማርም ሲል፣ልቀጠርም ሲል ኧረ ወዘተ የወያኔ አሽቃባጭ መሆን ሊኖርበት ነው ሰው ደግሞ ከእንግዲህ በኋላ ተነስቶ እንዲ ልሁን ቢል አንደኛ የወያኔ አሽቃባጭ መሆን ሊኖርበት ነው፤ ሁለተኛ የመንግስት ሀሁ ስለማያውቅብሎ መማር አለበት፤ ሦስተኛ ሁሉም ሰው የመንግስት ሰው እንዲሆን አይጠበቅበትም በራሱ መንገድ መጓዝ መብቱ ነው።
ሁሉም ሰው በሚሠራው ሥራ ሕይወቱን በአግባቡ ሊመራ የሚያስችለው ክፍያ እንደወቅቱ የገንዘብ የመግዛት አቅም እየተሰላ ሊከፈለው ሲገባሁልህም ነጋዴ ሁን፤ ሁልህም እጅ መንሻ ወደሚያስገኝ ሥራ ተዛወርብሎ ፍርደ ገምድል ብያኔ መስጠቱ አግባብ አይመስለኝም፡፡

ለማንኛውም ከመሰደድ ይልቅ ፊት ለፊት መጋፈጡ የተሻለ ነው እምነት አለኝ
የምንፈልገውን ውጤት የምናመጣው መስዋዕትነት በመክፈል ነው።
እውነቱነ ለካ ሁላችንም ነፃ ካልወጣን ማንም ነፃ አይወጣም ያለው ኦባንግ
እውነትም ሁላችንም ነፃ ካልወጣን ማንም ነፃ አይወጣም !!!
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment