Wednesday, July 31, 2013

! ….. ሽብርንና ‘ፀረሽብር ሕግ’ን አልደግፍም …….!

በአብርሃ ደስታየኢህአዴግ መንግስት በኢቲቪ በኩል ስለሽብር ፀረሽብር ሕግአስፈላጊነት ያወራል። አንዳንድ ተቃዋሚዎች ደግሞ ስለፀረሽብርሕጉ -ሕጋዊነት ይሰብካሉ። 

እኔም የፀረሽብር ሕጉ ከማይደግፉ ሰዎች ጋር እንደምሰለፍ ካሳወቅኩ ከጥቂት ግዜ በኋላ አንድ የምወደው የህወሓት አባል የሆነ ጓደኛዬ እንዲህ ሲል በውስጥ መልእክት ላከብኝ፣ 

ፀረሽብር ሕግ መቃወም ሽብርን መደገፍ ነው። አንዳንድ አክራሪዎች በሰላማዊ ሰልፍ ስም ሽብርተኝነትን ማስፋፋት ይፈልጋሉ። ዓመፅ ቀስቅሰው እስላማዊ መንግስት ማቋቋም ይፈልጋሉ። በኢትዮዽያ ዓመፅ ተቀሰቀሰ ማለት ደሞ ልክ እንደ ሶርያ ቀውስ ነው የሚሆነው። 


ሽብር ምንድነው? ሽብር ሃይል ተጠቅሞ ወይ ሃይል የመጥቀም ዛቻ በማሰማት ሌሎች ሰዎች ሰግተው፣ ፈርተው የግል ዓላማውን እንዲያሳኩለት ማድረግ መቻል ወይ እርምጃ መውሰድ ነው። 

የነጻነት ዋጋ ስንት ነው መጽሐፍ

ክፍል አንድ
የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ


ከአፍ የሚወጣ ግን ከልብ ይወጣል ሰውንም የሚያረክሰው ነው
ማቲዎሰ 1519
ምስጋናና አድናቆት፣
· ለመጪው ትውልድ ትምህርት የሚሰጥ፣ በታሪክም ሊዘከር የሚችል ብዙ ነገር እንደያዙ ወደ መቃብር የሚሄዱ አሉና አቶ ግርማ ሰው ሊያወቀው ይገባል ያሉትን ምንም ይሁን ምን ጽፈው በማቅረባቸው ላመሰግናቸው እወዳለሁ። እኔስ ይህችን አስተያየት እንድጽፍ ምክንያት ሆኖኝ የለ።

· አንድነትና መድረክ ውሃና ዘይት ሆነው በቀረቡበት ምርጫ አቶ ግርማ እጩ ሆነው ለማሸነፍ ያደረጉት ጥረት አድናቆት የሚቸረው ነውና እነሆ አድናቆቴ ይድረስዎ ብያለሁ። የምርጫ ዘመቻ ኃላፊ ሆና የሰራችው እህታቸውም ተግባር ለእህቶቻችን ምሳሌ የሚሆን ነውና የአድናቆቴ ተካፋይ ነች።የሴቶች ችግር ድፍሮ አለመግባት እንጂ ከገቡ ውጤታማ የፖለቲካ ስራ እንደሚሰሩ የጥሩ ዘር የምርጫ ዘመቻ ኃላፊነት አፈጻጸም በቂ ማሳያ ነው። 

ኢትዮጵያዊ ሙስሊሞችና ኢትዮጵያዊ ክርስቲያኖች ግንኙነት ላይ ሊሰራ የታሰበው ሴራ ከየት የመጣ ነው?

ኢንጂነር ረዲ ዘለቀ


ዛሬ ስለአጋሮ ጮጬና ሊሙ ሻይ ትንሽ ልበላችሁ። ሊሙሻይ ማለት የዚህ ጽሁፍ ጸሐፊ የተማረበት ቦታ ስትሆን ይህ ጸሐፊ ተወልዶ ካደገበት ጋሌ ቡሳሴ 34 ኪሜ ያህል ትርቃለች። ጋሌ ተወልደው ያደጉ ልጆች ሁሉ ከሰባተኛ ክፍል ጀምሮ ሌላ ቦታ መማር ካልፈለጉ በስተቀር የሚማሩት ሊሙ ሻይ መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ /ርት ቤት ነው። ሊሙ ሻይ በመንግስት ቡና ተክል የጎማ አንድ የሚባለው ቦታ የሚገኝባት ሲሆን በተጨማሪ ከጥርኝ ዝባድ የሚያመርቱ ሰዎች ያሉባት ቦታ ነች። አሁን አሁን የጥርኝን ኢንቨስትመንት በርካታ ኢንቨስተሮች ላናውቀው እንችላለን። ይህንን ለማንሳትና ሊሙሻይንና የተወለድኩበትን አካባቢ እንድጎበኝ ያደረገኝ አንድ የፖለቲካ ተንታኝ ሙስሊምንና ክርስቲያንን የሚለያይ አንዳንድ አባባሎች ከሰማሁ በሁዋላ ነው። በነዚህ አካባቢዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መካከል የሀይማኖትም ይሁን የዘር ልዩነት የለም። በእርግጥ አንዳንድ የራሳቸው አጀንዳ ያላቸው ሰዎች ጅማን የተለየ ችግር ያለባት ቦታ እንድትሆን ለማድረግ ሞክረዋል። ሆኖም የጅማ ህዝብ ፍቅር ነው። በልዩነት አያምንም። ይህንን ወደ ሁዋላ እመጣበታለሁ።