ከኢንጅነር ከዘለቀ ረዲ
ሰሞኑን እንደተነጋገርነው ሁሉ እስካሁን ያው በወሎ ሰማይ ስር ነኝ። አሁን ደግሞ በደቡብ ወሎ ዋና ከተማ ደሴ፤ በተለያየ ጊዜ ስለ ደሴ በአዝመሪዎችም በዘፈንም ብዙ ተብሏል። ደሴ በጎርጓዳ ውስጥ ያለች ከተማ እና በሩቅ የማትታይ ከተማ መሆኑዋን ለመግለጽ ደሴ ጎርጉዋዳ ነው። አይታይም ጢሱ በረጅም አውቶቡስ ከዚያው ካልደረሱ ይባላል። ደሴ እንደሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች ከየትኛውም አቅጣጫ ከሩቅ አትታይም። ደሴ የምትታየው ከውስጡዋ ሲገቡ ብቻ ስለሆነ ይህ ተባለላት።
በሌላ መልኩ በደሴ ብቸኝነት እንደሌለ ለማመልከትና ባለፈው ስናውራ እንደነበረው ሁሉ በውሎ ህዝብ ዘንድ በሀይማኖት መለያየት አለመኖሩንና እንዲሁም በወሎ በስም ብቻ አንድን ሰው ሙስሊም ወይም ክርስቲያን ነው ብሎ መገመት አይቻልም።
መሐመድ ብሎ ክርስቲያን መኮንን ወይም ገብረመድህን ተብሎ ሙስሊም አለ። በአንድ ወቅት አንዱዋ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ተቀጥራ ለመሥራት ካላት ጉጉት ክርስቲያን ነሽ ሲሉዋት አዎ ትልና እርግጠኛ ነሽ ሲሉአት ወላሂ ክርስቲያን ነኝ ብላለች ይባላል።ይህንን የሙስሊም ክርስቲያኑ አብሮ መብላት መጠጣቱንና ፍቅሩን ለማመልከት አዝማሪዎች የሚከተለውን ግጥም በማሲንቆአችው አጅበው ይሉታል።በሌላ መልኩ በደሴ ብቸኝነት እንደሌለ ለማመልከትና ባለፈው ስናውራ እንደነበረው ሁሉ በውሎ ህዝብ ዘንድ በሀይማኖት መለያየት አለመኖሩንና እንዲሁም በወሎ በስም ብቻ አንድን ሰው ሙስሊም ወይም ክርስቲያን ነው ብሎ መገመት አይቻልም።
እንደዚህ ነው ፍቅር ካምላክ የወረደው፣
የከበደን በሬ እንድሪስ አረደው፣
ሀገር ደሴ ነበር ጦሳ ባይጋርደው።
የደሴ ከተማ በጦሳ ተራራ የተከበበች ነች። ያ ጦሳ በሚባል ተራራ ተጋረዶ በሩቅ አልታይ ከማለት በስተቀር ደሴ በጣም ጥሩ ሀገር ነው ለማለት ነው።አሁን ባለንበት ጊዜ በርካታ ከተሞች አድገዋል። ከደሴ በስተቀር የደሴ ከተማ የከተማ አስተዳደርና ባለሙያ መሐንዲስ ያለው አይመስልም። በደሴ ከተማ የሚገነቡ ቤቶች በሙሉ ማለት ይቻላል። ከአስፓልቱ መሐል ግድግዳቸው ሳይሆን የቀረው የአስፓልት አምላክ ከልክሎአቸው እንጂ ከልካይ ኖሮአቸው አይደለም።
የደሴ ከተማ በኢትዮጵያ ቀደምት ከሚባሉት ከተሞች ከመጀመሪያ ተርታ የምትገኝ ስትሆን አሁን ግን በርካቶች ከኋላዋ ተነስተው ጥለዋት ሄደዋል። ቀደምት ከነበሩት የኢትዮጵያ ከተሞች ተጠቃሾቹ የዛሬን አያድርገውና አስመራ፣ ደሴ፣ ጅማ፣ሐረር፣ጎሬ ነበሩ፡፡ በተለይ ጅማና ደሴ ትልቅ የሚባሉት ነበሩ። አሁን ግን አይደለም። ከተሞች ሲያረጁ እነዚህን ከተሞች እንደሚመስሉ ይነገራል። በአሁኑ ሰዓት በደሴ ከተማ አንድ ቤት አልፎ አንድ ከፍተኛ ክሊኒክ የሚኖር ሲሆን ሶስት ቤት ያህል እንዳለፉ ደግሞ ቢያንስ አንድ ሆስፒታል ያገኛሉ።
ከተማዋን ሁሉ ዞረው ግን አንድ ደህና ሆቴል አያገኙም። በደሴ ሁሉም ሀብታሞች ማለት ይቻላል ሆስፒታል ቢከፍቱ ደስተኛ እንደሆኑ ሰምቻለሁ። የሰማሁት ምክንያት ከጠቃሚነቱ ጎጂነቱ ስለሚያመዝን ለመተው ተገድጃለሁ።በደሴ ከሶስት ያልበለጡ ፓርኪንግ (የመኪና ማቆሚያ)የሌላቸው ፔኒሲዎኖች ብቻ አሉ። ማንኘውም እንግዳ በተለይ መኪና ይዞ ቢሔድ መኪናው ከአስፓልቱ ላይ ማቆም ግድ ይላል። በደሴ የትኛውም ፔኒሲዎን ሲሔዱ መኪናዎን አቁመው ልክ የመኪነዎትን በር ሲከፍቱ የመኪናዎ በርና የፔኒሲዎኖቹ በር ሊጋጭ ይችላል። ይሄ እንግዲህ በደሴ ለኢንቨስትመንት የቆመ የመንግስት አካል ያለምኖርና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ለሚመጣው ተጽዕኖ ደንታ ቢስ የሆነ አስተዳደር መኖርን ያመላክታ ል። ምክንያቱም መንገድ ተጠግተው የሚሰሩ ቤቶች አሁን የተሰራውንና አገልግሎት እየሰጠ ያለውን መንገድ የሚያጣብብ ሲሆን ቀጥሎ ደግሞ ከፕላን ውጭ ስለተሰሩ ሲፈርሱ ሁለት ጉዳት አለው። የመጀመሪየው ቤቶቹን ለማፍረስ የሚወጣው ገንዘብ የመንግሥት ኪሳራ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ አሁን ቤቶቹ ሲገነቡ የወጣው ገንዘብ እሳት ላይ የገባ ቅቤ ማለት ነው። ይህን አጠቃለን ስንመለከት
በደሴ ዙሪያ በርካታ የቱትሪስት መስህብ የሆኑ ቦታዎች አሉ። ነገር ግን የሚያሳስብዎት ጉዳይ ቢኖር ሰንሰለታማዎቹ የአምባሰል ተራራ ውስጥ ያሉ ተሪካዊ ቅርሶችንና ግሩም አፈጣጠር አለው ተብሎ የሚነገርለትን የሀይቅ እስጢፋኖስን ለማየት ቢሄዱ የት አድራለሁ ብለው መጨነቅዎ አይቀርም። እኔ ባየሁት ሁኔታ አንድ የተሻለ ማደሪያ ያለው ሆቴል አይቻለሁ። ነገር ግን የሆቴሉን የበረንዳ ኮለን ያው አስፓልቱን ገጭቶ ነው የተመለሰው። በርካታ ሰዎች በደሴ ከተማ የተሻለ ሆቴል ለመስራት ፍላጎት ያላቸው ቢሆንም የከተማው አስትዳደር ሰፋ ያለ ቦታዎችን ለባለ ሀብቶች ሰጥቶ ከተማዋን ከማሳደግ ይልቅ አሮጌ ቤቶችን ታቅፎ መዝለቅን የፈለገ ይመስላል።በእርግጥ ለደሴ አለማደግ የጦሳ ተራራ የበኩሉን አስተዋጽዖ ቢያበረክትም ከተማዋን ወደቦሩ ሜዳ አቅጣጫ፣ዳውዶና ቧነቧ ውሃ ሮቢትን ጨምሮ ባለው አቅጣጫ ማሳደግ በተቻለ ነበር።
ደሴ የነ ሙሉጌታ ከበደ የትውልድ ቦታ ነች። ታዋቂው የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኩዋስ ተጫዋች ሙሉጌታ ከበደ የተገኘው ከደሴ ነው። ያን ጊዜ የዋልያና የፔፕሲ ቡድን በደሴ ስታዲዮም ሲጋጠሙ የዛሬውን የቅዱስ ጊዮርጊስና የቡና አይነት ድባብ እንደነበረው ነዋሪዎች ያነሳሉ። በደሴ በአንገታቸው ላይ የብር መስቀል ያንጠለጠሉ ቆንጃጅት እና በግንባራቸው ላይ የመስቀል ቅርጽ የተነቅሱ ኮርዳዎች የደረጉት ብርም ይሁን የተነቀሱት ምልክት ጌጥ እንጂ የሀይማኖት መገለጫ አይደለም። ደሴን ሄዶ በመጎብኘት ያንን ዋህ ህዝብ፣ሀይቅ እስጢፋኖስን፣ ግማደ ማሰቃሉንና ልሎች… ታሪካዊ ቦታዎቸን ማወቅ ይቻላል፡፡
ወደዛሬው ርዕሴ ልግባ ገዥው ፓርቲ ከፌዴራላዊ አወቃቀር ወደ አሀዳዊ አገዛዝ እየተሸጋገረ ይመስላል። የፌዴራላዊ ሥርዓቱ እንዲጎለብት ቆመናል ብለው የተደራጁት ፓርቲዎችም አንዱ አንዱን ከመንቀፍ የዘለለ አንዳችም ሌላ ያታሻለ ሥራ ሲሰሩ አይታይም።
ዛሬ በኦሮሚያ ክልል ያሉ ፓርቲዎችን ለመመልክት እሞክራለሁ።በእርግጥ የኢህአዴግ የፈዴራላዊ አውቃቀር ብሔር ተኮር እንጂ ሀገራዊ ራዕይ ያለው ፌዴራላዊ አወቀቀር አይደለም። ያም ስላልሆነለት በርከታ ብሔሮች ካንዱ ጋር ተጣምረው ወይም ተዳብለው ሲቸገሩ ይታያል።
ዛሬ ኦህዴድን ለመውቀስ አልፈልግም። ምክንያቱም ኦህዴድ ሲመሰረት መሰረታዊ አንሳሱ የመንግስትን ጥቅም ከማስጥበቅ አንጻር እንጂ ከኦሮሞ ህዝብ ጥቅም አኩያ ስላልሆነ የሚል ግምት አለኝ። እባካችሁ በዚህ አነጋገሬ የኦፒዲዮ ባለስልጣናት ልትቆጡ ትችላለችሁ። ሆኖም ለኦሮም ህዝብ ያለመቆማችሁን በአንድ ሁለት ምሳሌዎች ላስረዳ። የመጀምሪያው የኢትጵያ ዋና ከተማ ፊንፊኔ የሀገሪቱ ርዕሰ ከተማ ሆና እንድትቀጥል በህገ መንግስቱ ሲወሰን ኦሮሚያ ክልል ሊያገኝ የሚችለው ጥቅማጥቅም በተመለከተ በአዋጅ አንደሚወጣ እና በመመሪያ እንደሚወሰን የተቀመጠ ቢሆንም ህገ መንግስቱ ሁለት አስርተ ዓመታት በላይ ቢያስቆጥርም ኦህዴድ አዋጁንና የአፈጻጸም መመሪያውን እንዲወጣ ማድረግ አልቻለም። በዚህም የኦሮሚያ ክልል ተጨመሪ ከዲፕሎማቱ ማህበረሰብ ከሚሰበሰብ ገቢና ከተለዩ ሁኔታዎች የሚሰበሰበውን ሀብት እንዳታገኝ አድርጓታል።
ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ኦህዴድ የቆመው ለመንግስት ነው። ለኦሮሞ ህዝብ አልቆመምና እኛ መታገል አለብን ብለው በብሔሩ ስም የተደራጁ የፖለቲካ ድርጅቶች ያሉ ሲሆን ኦፒዲዮን ከመውቀስና አነርሱ አማራ ድርጅቶች ናችው ከሚሉአቸው ፓርቲዎች ጋር ከመካሰስ የዘለለ አንዳችም የረባ ሥራ አልሰሩም። እንደውም አሁን የኦሮሞ ህዝብ ለሚደርስበት በደል የአንበሰውን ድርሻ እንዚህ ተቃዋሚ ነን የሚሉ ነገር ግን በኦሮሞ ህዝብ ላይ ለሚደርሰው በደል ሁሉ ከመታገል ይልቅ የቅምጥል ኑሮን የመረጡ፤ ትግል ማለት በፓርቲ ተደራጅተው የፖለቲከ ፓርቲ ፈቃድ መያዝ ብቻ የሚመስለቸው የፍየል ጭራ ወይም የአህያ ባል የሆኑ ፓረቲዎች አሉ፡፡ የአህያ ባል ከጅብ አያሰጥልም። አነርሱም እየሰሩ ባለው ስራ ሲገመገሙ እንዳዚያው ናቸው፡፡
የኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ የሚያገኘውን ጥቅም በተመለከተ ገዥው ኦፒዲዮ እየፈጸመ ያለው የሥርዐቱን ፈቃድ ከሆነ እነርሱ የህዝብ ፈቃድ እንፈጽማለን የሚሉት ምን ሰሩ? የፓርቲዎች ብዘት ለኦሮሞ ህዝብ ምንም አልጠቀመውም። እንደውም አነዳንድ ፓርቲዎች አቋቋማቸው በራሱ ሌሎችን ለማዳከም እንደሆነ ይሰማል፡፡የአንድ ኦሮሞ ልጆች በራሳቸው መስማማት አቅቶአቸው አንዴ ምንትሴ እንዴ ቅብርጥርሴ እያሉ በዓላማም በስምም የተለያዩ ፓርቲ መመስረት ሊቀመንበር የመሆን ፍላጎትን ከማሟላት የዘለለ አንዳች ጥቅም የለውም። ጥቅም ሰጥተናችኋል የምትሉ ከሆነ የሰራችሁትን ሥራ ዘርዝሩ እንመናችሁ። እናንተም በራሳችሁ ይህንን ትልቅ ህዝብ ይዛችሁ በመንግስት ላይ ጫና ማሳዳር በቻላችሁና በህገመንግስቱ ላይ የተቀመጠውን የኦሮሞ ህዝብ ጥቅም ማስጠበቅ ትችሉ ነበር ነገር ግን አልሞከራችሁም አልሰራችሁም። የሚፈራ መሪ መመለስ ሲገበው እናንተ ከነፍራታችሁ ከፊት ቆማችሁ ከሁዋላችሁ ያሉ ጀግና ወጣት ኦሮሞ መሪዎች በእስርቤት ይታጎራሉ። ለነግሩ ህገመንግስቱ ለማስፈጸም መታገል የታሰሩትን ለመስፈታት ከመተገል አይቀል? በተንሹ ታግላችሁ ሳታሳዩ ትልቁን መጠበቅ እንዴት ይቻላል?
አንድን የመጣን ነገር ካልተቀበሉት መቃወም ይቻላል። ያም ደግሞ ትክክልና መደረግ ያለበት ነው፡፡ ነገር ግን ዝም ማለት መስማማትን ያመለክታል።አሁን የኦሮሞን ህዝብ ወክለን ቆመናል ብለው የቆሙ ድርጅቶች ኦሮሚያ እየጠበበች ነው። መሬቷ በወፍ በረርእየተሰላ ወደ አዲሰ አበባ እየገባ ነው፡ ታዲያ ቆመናል ለሚሉት ዓላማ ህዝባቸውን ይዘው የሚጮሁት መቼ ነው? ኦሮሚያ ባሙሉ ዋዳፊነፊኔ ገብታ ስታልቅ? ከዚያስ አሁን ባለው ሁኔታ በርካታ ጥያቄዎች አሉ።
በቅርቡ የኦህዴድ ሥራ አስፈጻሚና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ኩማ ለሃያ አምስት ዓመት የሚዘልቅ ማስተር ፕላን የኦሮሚያ ልዩ ዞኖች ከአዲስ አባባ ጋር ተዳብለው መሰራታቸውን አብስርዋል። ኦሮሞን ወክለናል ብለው የተቋቋሙ ድርጅቶች የባሌም የቦሌም አላሉም። ዝም ብለዋል፡፡ ይገባኛል፤ እነዚህ ሰዎች አሁን መናገር ያልፈለጉት በኋላ ለፓርላማ ውድድር ጊዜ አንስተው ሊከራከሩበት ስለፈለጉ ነው፡፡ እንገዲህ አብዛኛው ለኦሮሞ ታግያለሁ እየታገለኩ ነው የሚሉ ልሂቃን እስካሁን የእግር እሳት ሆኖ የሚቆጫቸው የፓርላማ ወንበር ማጣታቸው እንደሆነ እሙን ነው፡፡ ለዚህም እነርሱ የነበሩበትን ወንበር ሌሎች ሲቀመጡበት መተቸታቸው ምሥክር ነው፡፡ አንዳንዶቹ በተለይ ፈፅሞ ለኦሮሞ ህዝብ የማይጠቅም እገሌ አማራ ነው፡፡ የእገሌ ፓርቲ እንዲህ ነው በማለት ያለመስራታቸውን ህዝብ እንዳያውቅባቸው በአሉባለታ ብልኮ ሲሸፍኑት የሰተዋላል፡፡ በዚህም መታገያ ጊዜያቸውን ዘር በመቁጠር ሲያሳለፉ ይታያሉ፡፡ የአሁኑን የኦሮሚያ ልዩ ዞን ዋዳአዲስ አበባ መካተት በተመለከተ መንገስት ይህንን ያደረግሁት ከሚሰጠው ጥቅምቅ አኳያ ነው ብሎ ያስቀመጣችው ነገሮች አሉ። በሚቀጥለው ከህገመንግስት አኩዋያ ኢህአዴግ ክልሎችን አንድ ለማድረግ እየሔደ ያለበትን ሁኔታ ለማየት እንሞክራለን ቸር ይግጠመን።
No comments:
Post a Comment