Friday, July 5, 2013

***ኢትዮጵያን ዛሬ ዘመናችን ባመጣብን ጎጠኛ አስተሳሰብ ማየት የለብንም፡፡***

ኢትዮጵያ የሚለው ስም ተራ ስም አይደለም፡፡
አርበኞች አባቶቻችን መስዋት የሆኑላት አገር ናት።
ብዙ ሚሊዮኖች እንዲሠዉ ያደረገ ስም ነው፡፡
ኢትዮጰያዊነት እንደ ዘይትና ውሃ ተደባልቆ የተለየ አይደለም።

ብዙዎች በስፖርት አደባባይ ካገኙት ድል በላይ ይህ ስም ሲጠራ አንብተዋል፡፡
ይህ ስም በቅዱስ መጽሐፍ ከአርባ አራት ጊዜ በላይ የተጠቀሰ ነው፡፡ 
ይህ ስም ሲጠራ ብዙዎች ኢትዮጵያውያን ደማቸው ይሞቃል፣ ስሜታቸው ይንራል፣ ነርቫቸውነም ይነዝራቸዋል፡፡
ኢትዮጵያዊን አይቶ ከየት ነው ሊሉት የማይባል መልክ።
**
ኢትዮጵያን ዛሬ ዘመናችን(ወያኔ) ባመጣብን ጎጠኛ አስተሳሰብ ማየት የለብንም፡፡**
ኢትዮጰያዊነት በጠባብ አስተሳሰብ የምትወሰን አይደለችም ከዚህም አስተሳሰብ የሰፋች የተለየቺም ናት፡፡ 
*
ከዚህኛው ወይም ከዘኛው ዘር ብቻ እወለዳለሁ ብሎ መናገር የዋሕነት ሳይሆን አላዋቂነት ነው፡፡**
ይኽኛው ወይንም ያኛው ሥልጣኔ እና ታሪክ፣ ገድል እና ተአምር የዚህ ወገን ብቻ ነው ብሎ መጻፍም ኢትዮጵያን አለመረዳት ነው፡፡
ኢትዮጰያዊነት የአማራ፣የኦሮሞ፣የጉራጌ፣የሱማሌ፣የቤንሻንጉል፣የትግሬ ,, ብቻ አይደለችም የብሔርና ብሔረሰቦች አገር ነች።


በእርግጥ በማንኛውም ወገናችን ላይ በተናጠል የሚደርሰው በጎም ይሁን ጉዳት የጋራችን መሆኑን መቀበል አለብን፡፡
የማንኛውም ክፍል ወጋናችን በተናጠልና በተራ በሚደርስበት መሰቃየት መታሰር፣ መፈናቀል መጋዝ መዋረድ ለሌላውም ህመም ሆኖ ሲሰማው ኖርዋል ፡፡
ለመፍትሄውም አብሮ ተዋድቋል ታግሏል አብሮ በደም የተሳሰረ አንድነት ገንብቷል ፡፡
ያም እየተደናቀፈም ቢሆን ወደፊት ይቀጥላል ፡፡

በተለምዶ በአባቴ የትውልድ ሃረጌ የዚህኛው ዘር ነኝ በእናቴ የዚያኛው የእከሌ ወገን ነኝ እንደምንለው ሁሉ ሁላችንም በኢትዮጵያዊነታችን ከአማራውም ከኦሮሞውም ከሃዲያውም ከሁሉም የሐገራችን ሕዝብ ጋር ትስስር ስላለን የትኛውም ወገናችን በተናጠልም ይሁን በጋራ ለሚደርስባቸው ጥቃት፣ የራሳችን ጥቃት መሆኑ ተሰምቶን፣ ከማንኛውም የተገፋ ወገናችን ጎን ቆመን ጥቃቱን በጋራ ልንከላከል ይገባል ፡፡
ኢትዮጵያ የሚለው ሁላችንንም የሚያገናኝ ማእከል ነው ካልን ? 
እኔ በኢትዮጵያዊነቴ ዶርዜነት አለብኝ፣ በኢትዮጵያዊነቴ አፋርነት አለብኝ በኢትዮጵያዊነቴ አማራነት በኢትዮጵያዊነቴ ኦሮሞነት ....ወዘተ አለብኝ ብለን አምነን በተግባር በክፉም ሆነ በደጉ ጊዜ አብረን ተደጋግፈን ስንቆም ነው እውነተኛ ኢትዮጵያዊነታችንን በተግባር የምናስመሰክረው፡፡

ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment