ከኢንጅነር ከዘለቀ ረዲ
ዛሬ ከአስዲስ አበባ በስተምዕራብ 250 ኪ.ሜ. ገደማ ላይ እገኛለሁ። ሳጃ ከየም ብሔረሰብ ከተማ አንዱዋ ነች። የየም ብሔረሰብ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ከጅማ ዞን በስተምሥራቅ የሚገኝ የደቡብ ክልል ልዩ ወረዳ ነች። በጅማ ከተማ ባሉ ሰዎች ዘንድ አንድ ታላቅ እምነት አለ። አንድ ሰው የየም ብሔረሰብ አባል ከሆነ በምንም ዓይነት ሙያ ለመቀጠር ቢፈል ዋስ አያስፈልገውም። ለታማኝነቱ በጅማ ከተማና አካባቢ ባሉ ህብረተሰብ ዘንድ ባለ ዕምነት የየም ብሔረሰብ አባል ሆኖ መፈጠር በራሱ ከበቂ በላይ ዋስትና ነው።
በየም ማሀበረሰብ ዘንድ ጸያፍ ሥነ ምግባር ማለት ሌብነትና አለመታመን ነው። የየም ብሔረሰብ አባላት በተራራማና ደጋማ በሆነ አካባቢ የሚኖሩና የተለያየ አይነት አትክልትና አዝዕርትን በማምረት ይተዳደራሉ። ዶሮና በግም በማርባት የሚታወቁ ሲሆን ያልተዳቀሉ የህገራች ዶሮዎችና እውነትኛው የሀብሻ ዶሮ እንቁላል ለማግኘት ከፈለጉ የም መሔድ ያስፈልጋል። ማለት ነው።
የሶኮሩ ከተማ ለሁለት ተከፍላ በምዕራብ ያለው ክፍል ወደ ኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን የሚጠቃለል ሲሆን በስተምስራቅ ወደአዲሳባ መለስ ያለው ክፍል ደግሞ በደቡብ ክልል የሚካተት ይሆናል ማለት ነው። በሶኮሩ ከተማ ውስጥ አንድ ከበሮ ግድግዳ የሆነ ቤት ግማሹ የየም ልዩ ወረዳ ግማሹ የጂማ ዞን ሊሆን ይችላል። በዚህ አጋጣሚ ከነዚህ ሰዎች አንዱ ቤቱን አፍርሶ ለማሰራት ቢፈልግና አንዱ ባይስማማ ጉዳያቸው የት ሊታይ ይችል ይሆን?
የብሔር ተኮር ፌዴራሊዝም ችግር አንዱ ይህ ነው። በመሐከል የሚከሰቱ ችግሮችን ለመፍታት ድንበር ተሻግሮ መሔድ ጊዜንና ገንዘብን ማባክን። በመሰረቱ በስኮሩ ከተማ ያሉ ሰዎች ይሄ ኦሮሞ ነው ወይም የም ነው። ብሎ ማለት ያስቸግራል። ሁሉም ተዋልደዋል። አባቱ ኦሮሞ የሆነ እንድ ሰው እናቱ የም ልትሆን ትችላለች። እንዲሁም በተቃራኒው
የየም ብሔረሰቦች አስደሳች የሙዚቃ (የጭፈራ ባህል) አላቸው። ጭፈራውን መንቀሳቀስ የሚችል ሰው ሁሉ አጨፋፈሩን ብቻ ካየ በአንዴ ለምዶት አብሮ ደስ ብሎት ይጨፍራል። ሁሉም ሰው ዙሪያ ገጥሞ እየዞሩ ከወገብ በታች በመንቀሳቀስ ሲጨፍሩ ደስ ይላል። የየም ብሔረሰብ ጭፈራ ላይ ገብቶ ለመጨፈር የሚፈልግ ሰው አትችልም ውጣ አልችልምና ልቅር ማለት የለም። ገብቶ በደስታ መጨፈር ነው። የጭፈራው ድምቀት እንደትግርኛ ጭፈራ ይሆንና ልዩነቱ የትግርኛው ጭፈራ ከእግር እንቅስቃሴ በተጨማሪ ከትክሻ በላይ ሲሆን የየሞች ደግሞ ከእግር እንቅስቃሴ በተጨማሪ ከወገብ ብታች ነው።
አንዴ በጥምቀት ወይም በአንድ የንግስ በዓል ቢሄዱ ይህንን አስደሳች ጭፈራና ጀግና ህዝብ አይተው መምጣት ይችላሉ። በተጨመሪ እጅግ ጣፋጭ የሆኑ አትክልት ወረዳ ነች የም ልዩ ወረዳ ጎደሬ የሚባል የድንች ዝርያ ስሩ የሚበላ ሲሆን ቅጠሉ ደግሞ ተጠቅልሎ እንደውሃ መጠጫነት ያገለግላል። የየም ልዩ ወረዳ ምንጭ ውሃ በተለይ በጎደሬ ቅጠል ሲጠጡት በጣም ከመጣፈጡ የተነሳ ሳይረኩ ብዙ ይጠጣሉ። ሌላም ወጭኖ የሚባል እንዲሁም በጣም ጣፋጭ ሙዝና ቡርቱካን ማንጎ ሸንኮራ አገዳ ያለባት የም ልዩ ወረዳ ሌላም በርካታ ታሪካዊ ነገር ያገኛሉ።
የየም ህዝብ ከታማኝነቱ በተጭማሪ ጀግናና አትንኩኝ ባይ ሲሆን ምስክርነትን በተመለከተ ያየውን ከመመስከር ውጭ በዝምድናና በትውውቅ የራሴ ሰው ስለሆነ በሐስት መስክሬ ላውጣው ብሎ ነገር የለም። ህዝቡ ክድሮ ጀምሮ ጠላት ሲምጣ በአንድ ላይ ሆኖ ሀገሩን ከጠላት የሚከላክል ህዝብ ነበር። ሌላውን ለሀገሪቱ ታሪክ አጥኚዎችና ለቱሪዝም ኮሚሽን ትቼው በዚህ ላብቃ። ወደዛሬው ርዕሴ ልግባ፤
ዋናው ርዕሰ
ባለፈው ሳምንት ኢህአዴግ ከብሔር ፈዴራላዊ አወቃቀር ወደ አሀዳዊ አገዛዝ ጉዞ በሚል ቀንጨብ አድርጌ ሰፋያለውን ሀተታ በተከታታይ ለማቅረብ እሞክራለሁ።ብዬ ነበር። ዛሬ በቀጠሮዬ መጥቻለሁ። በፖለቲካ የለውጥ አስተሳሰብ በአንድ ሌሊት አይጸነስም። የተጸነሰም ካለ ከብዙ ሂደቶች በኋላ ራሱን ማዋሀድ ስላለበት ብዙ ጊዜ ይፈጃል። የምናራምደው ፖለቲካ ከሂደቶች ውስጥ የሚወለድ ነው። ሂደቶች ደግሞ በጊዜያቸውና ያለጊዜያችው ይወለዳሉ። በደርግ ጊዜ የነበረው የፖለቲካ ትግሉ አመጣጥና የወቅቱ የንጉሠ ነገሥቱ መውደቅ በሂደቶች የመጣ ለውጥ ነበር።
ሆኖም የወቅቱ የህዝብ ጥያቄ እና በህዝቡ በራሱና በልጆቹ መስዋዕትነት የመጣውን የትግል ውጤት የተቀበልው ግን ደርግ ነበር። ይህንን በጊዜው የተወለደ ልጅ ትክክለኛ ባልሆነው አሳዳጊ ደርግ እጅ ወደቀ። ለራሱ ትክክለኛ ያልሆነ አሳደጊ ደግሞ እራሱ ስላልተስተካከለ የተስካከለ የፖልቲካ ሥርዓት እንዲኖር እና ሂደቱን ጠበቆ ፖላቲካው በሥርዓቱ ኢንዲያድግ አያደርግም። ያንጊዜ ደርግ በጊዜው የተወለደውንና በህዝብ ከፍተኛ ተጋድሎየመጣውን ለውጥ አላግባብ እንዲያድግ በማድረጉ ተከታዩ የለውጥ ትግል በሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ሳይሆ በነፍጥ እንዲመጣ አደረገ። በዚህም ፖለቲካው ሙሉ አካል ያልሆነ መጻጉዕ ፖለቲካ ሆነ። ስለዚህ ሙሉ አካል የሌለው ጎደሎ ሆነ ማለት ነው።
የጎዶለነቱ ምልክት የወቅቱን ሥርዓት በርካቶች ተቃወሙት። ብዞዎች የተቃወሙት ደግሞ ሙሉ አይደለም ማለት ነው። በርካቶች ለነጻነት ለፍትህ ልዴሞክራሲ ጫካ ገብተው ደረታቸውን ለጦር እግራቸውን ለጠጠር ሰጥተው የፈልጉት ነጻነት እነርሱና ህዝባቸው እንዲያገኙ ታገሉ። ባደረጉት ቆራጥ ትግል የወቅቱን አምባገነን መሪ ገርስሰው የጣሉ ቢሆንም ጀግኖቹ የወደቁለት ዴሞክራሲና ዋጋ የክፈሉለት ፍትህ ዛሬም የለም። በትግላቸው የተገኘው ውጤት የጀግኖቹ ለዴሞክራሲ መሞት ብቻ ነው። አሁንም ሲታገሉት የነበረው ዓይነት ሥርዓት እንደነበረ መሆኑ ማንም የሚያውቀው ነው።
ሌላው ያለጊዜው የተወለደ ልጅ የማደግ እድሉ የመነመነ ሲሆን እርሱን ለማሳደግ ከተፈለገም ከፍተኛ ወጪ ይጠይቃል። ያለጊዜው የሚወለዱ የፖለቲካ ለውጦች የአውላለዳቸው ጊዜ እርዝማኔና እጥረት ወጪው ሊበዛና ሊያንስ ይችላል። ለምሳሌ ከስድት ወር በፊት የሚወለድ ልጅ እንዲያድግ ለማድረግ ከፍተኛ የሆነ የኢንኩቤቴር ወጪ ይጠይቃል። ያለጊዜው የሚመጣ የፖለቲካ ለውጥ የበለጠ ዋጋ ያስከፍላል። በተለይ በእኛ ሀገር ሁኔታ እንኩዋን ያለጊዜው የተወለደ የፖለቲካ ለውጥ ይቅርና በጊዜው በሂደቱ የተወለደውንም ቢሆን የሚወስደው የቀደመው ስለሆነ ከተቀደመው ጋር በሚደረግ ግብግብ ከፍተኛ እልቂት እና ዋጋ ያስከፍላል።
የሀገራችን ፖለቲከ ለውጥ አካሄድ የየሥርዓቱን ሂደት የተከተለ ሳይሆን ከአንዱ ሥርዓት በቀጥታ በመዝለል ወደሌላው በመሻገር ይታውቃል። ለምሳሌ ያህል የኣጼው ሥርዓት ፊውዳላዊ አገዛዝ የነበረ ሲሆን ለውጡን ተከትሎ በቀጥታ የመጣው ሥርዓት ሶሻሊዝም ነው። ሁለቱ ነገሮች ደግሞ የማይምሳሰሉና ተቃርኖአችው የፖዘቲቭና የነጋቲቭ አይነት የሆነ ነው። ሶሸሊዝምን አልቀበልም ብሎ የመጣው ኢህአዴግ በተለያዬ ጊዜ ራሱን እየለዋወጠ ከመሄድ ውጪ አንዱን ሥርዓት አስትካክሎ ሊያሳድግ አልቻለም። አለን የምነል ፖለቲከኞችም ኢህአዴግ የሚያመጣውን ዘዴና መልቲነት እየተከተልን ጋዜጣዊ መግለጫ ከማውጣት የዘለለ ጠብ ያለ ሥራ አልሰራንም፡፡
ኢህአዴግ መጀመሪያ ሀገሪቱን እንደተቆጣጠረ ዴሞክራሲን ለማስፈን ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው የቆሰለው፣ የደማው፣ የወደቀውና የሞተው የህዝቡን ዴሞክራሲያዊ መብት ለመስከበር በነጻነት የመሰብሰብ፣ በሰላመዊ ስልፎች ማስፈቀድ ሳያስፈግ በማሳወቅ ብቻ ሀሳብን በነጻነት በመግለጽ መደገፍም ይሁን መቃወም እንደሚቻል ነው ብሎ ነበር፡፡ በህገ መንግስቱ የተደነገገ ቢሆንም፤ እንዲሁ ለውጡ ያስፈለገው ለዚህ ነው። የሚል ዲስኩር ቢነገረንም በሀገሪቱ ውስጥ ከአንዴ በስተቀር ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ አልፈቀደም። ያም በ1997 ሚያዚያ 30 ማለት ነው። ያም ሰልፍ በወቅቱ የኢህአዴግ ከፍተኛ አምራሮች በዝቅተኛ አመራሮች የተታለሉበትና ህዝብ እነርሱን እንደሚወድ ሲነገራቸው የነበረውን የውሸት ሪፖርት ያወቁበት ጊዜ ነበር።
ከዚያን ጊዜ በኋላ እስካሁን ድረስ ሰላማዊ ሰልፍ እንኩዋን አሳውቆ አስፈቅዶ ማድረግ አልተቻለም። ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርኩት ኢህአዴግ በሐምሌ 1987 አድርጎት በነበረው ስብሰባ ከየተወካዮቹ ፊትለፊት የነበረው የሥም መገለጫ TPLF, OLF,ONF,.... የምን ነጻ አውጪ የምንትስዬ ነጻ አውጪ ግንባር የሚልስም ነበረ።በወቅቱ የኢህአዴግ መንግስት ሊያዋጣውና ወንበሩን ሊያረጋጋለት የሚችለው ርዕዮት የጎሳ ፖለቲካ ስለነበረ ያችን መንገድ ያዘ። በወቅቱ የነበሩት ተወካዮቻችን አንዱ የአንዱን ስም በማሞገስ ታምራት ላይኔ ማለት ላይኔ ተአምር አሳየኝ ማለት ነው ብለው ተወዳደሱ። በወቅቱ ለእነርሱ ተአምር የሆነው የታገሉለትን አላማ ማስፈጸም ሳይሆን ወክለነዋል ያሉትን ድርጅት ስም ለጥፎ በስብሰባው ላይ መገኘት መስሎአቸው ነበር። ከዚያም በላይ ሳይሰሩ ወከለነዋል ያሉትን ህዝብ ሜዳ ላይ በትነው ስለመሄዳቸው ወደፊት እናየዋለን።
በእርግጥ ኢህአዴግ በወቅቱ ከጎሳ ፖለቲካ እና ከብሔር ፌዴራሊዝም ውጪ የሚያዋጣው ሌላ ስላልነበረ በዚያች መንገድ ትንሽ ከተጓዘ በኋላ አቢዮታዊ ዴሞክራሲ የምትል ባርኔጣ በአናቱዋ ደፋባት ለነገሩ አቢዮት ብሎ ዴሞክራሲ የለም። ኢህአዴግ ይዞት የመጣው ርዕዮተ ዓለም ሀገርን አነደማያሳድግለትና የእርሱንም ህልውና እንደማያስጠብቅለት ከተረዳ ዉሎ ያደረ ቢሆንም ቀጥታ ወዳሰበው ሀሳብ ለምግባት ግን የተቸገረ ቢሆንም አሁን ግን በቀጥታ ልማታዊ መነገስት ነኝ በማለት የልማታዊ መንግስት ኦቶቶሪያል ባህሪይን በቀጥታ መተግበር ጀምሮአል።
ልማታዊ መንግስት ከተግባሮቹ ውስጥ ብሔራዊ ስሜት የሚፈጥሩ ጉዳዮችን መፍጠርና የተፈጠሩትም ማጠናከር ነው። ለምሳሌ ስፖርት ኢህአዴግ እንደገባ ከማወዳቸው ነገሮች አንዱ ነበር፡፡ ስታዲዮም መገንባት አስፈላጊ እንደሆነ ሲነገራቸው ለአንድ ገበሬ ጥቂት ማዳበሪየ ገዝቶ መስጠት እንደሚሻል ተናግረው የነበረ ሲሆን አሁን ግን ኢህአድግ ለስፖርት ማዘውተሪያ ስታዲዮም ለማስገንባት ከ200,000,000.00 ብር በላይ ከመንግስት በጀት እንደመደበ በዜና ሰምተናል። ይህ ከልማታዊ መንግስት ባህሪይ አንዱ ነው። ስፖርት ብሔራዊ ስሜትን በመፍጠር ረገድ ከፍትኛ ቦታ ካላችው ነገሮች እንዱ ስለሆነ የልማታዊ መንግስት በስፖርቱ ላይ ከፍተኛ ሥራ ይሠራል። አሁን ኢህአዴግ ያንን እየሠራ ይገኛል። በአሁኑ ሰዓት ኢህአዴግ የአንድነትን ስሜት የመፈለግ ስሜት እየታየበት ነው። ምክንያቱም በተከፋፈለ የፖለቲካ አስተሳሰብ መንገድ ሀገር አታድግም በሚለው አስትሳሰብ ማለት ነው።
ልማታዊ መንግስት የድሮ የማስታወሻ ፎቶዎችን በማንሳት ኢግዚብሽን በማሳየት ለንጻነት ወይም ስልጣን የተደረገውን ትግል የጦርነት ቪዲዮችን በማሳየት ድሉ በቀለል እንዳልተገኘ ለማሳየት ይሞክራል። በዚህም የተገኘውን ሥልጣን ለመያዝ የተከፈለውን ዋጋ ክብደት ሌሎች እንዲረዱ በማድረግ በቀላሉ ስልጣን እንደማይለቅ ግንዛቤ ያስጨብጣል። ከዚህ አንጻር የኢህአዴግ መንግስት በተለያየ ጊዜ ከደርግ መንግስት ጋር ያደረገውን ጦርነትና የከፈለውን ዋጋ በማሳየት ቀዳሚ የለውም።
በልማታዊ መንግስት መሬት የመንግስት ነው። መሬትን እንደዋና ሀብት በመጠቀም ከፈለገው እየነጠቀ ለፈለገው ይሰጣል። በርካቶች ስለመሬታቸው ሲሉ ለአግዛዙ እንዲንበረከኩ ይደረጋል። በሀገራችን ያለው ፌዴራላዊ አወቃቀር ብሔር ተኮር ሲሆን አሁን እየተፈጸመ ያለው ግን ያንን የተከተለ አይደለም። በእርግጥ ይህንን ጸሐፊ ጨምሮ በርካቶች ለሀገራችን የሚጠቅማት ፌዴራላዊ አወቃቀር ጂኦግራፊካል ነው በሚል የተከራከርን ቢሆንም መንግስት ግን በተመቸው ቦታ ጂኦግራፊያዊ ባልተመቸው ቦታ ብሔራዊ ፌዴራሊዝም የመሰረተ ቢሆንም አሁን ከያዘው ልማታዊ መንግስትነቱ ጋር ሊሄድለት ስላልቻለ በራሱ በልማታዊ መንግስት አስትሳሰብ ጉዞ እየሄደ ነው። የመንግስትን አሰራር ለመቃወም የተደራጀን ተቃዋሚዎችም መንግስት የሚያወጣውን ፖሊሲ ከማስፈጸም የዘለለ ምንም የረባ ሥራ አልሰራንም።
የልማታዊ መንግስት ሌላው ተግባሩ ትላልቅና ሀገራዊ ስሜት ሊፈጥሩ የሚችሉ ግንባታዎችን መጀመር ሲሆን የተጀመረው ግንባታ አለቀም አላለቀም ጉዳዩ አይደለም። ብቻ የተለያዩ ሀገረዊ ስሜት ሊፈጥሩ ይችላሉ የሚላቸውን ፕሮጀክቶች ግን ይጀምራል።በሀገራችን ትልቁ የግልገል ግቤ ሦስት ፕሮጄችት በተጀመረ እና የዓለም ህዝብ በኬኒያ ላይ ጽዕኖ ያመጣል እያለ እየተንጫጫ በነበረበት ማግስት የኣባይ ግድብ መጀመሩ አንዱ መገለጫው ነው።በእርግጥ የዓለም ህዝብ ለኬኒያ አስቦ ሳይሆን አፍሪካ በእድገት ጎዳና እንዳትሄድ እርስ በርስ በማጋጨት እድገትዋን ለማስቆም ነው። ምክንያቱም አሁንም ቢሆን አፍሪካ ለምዕራባውያን ሀገራት የተደራጀ ሸቀጥ ማራገፊያ ከመሆን አልዘለለችምና
የልማታዊ መንግስት ዴሞክራት መስሎ ለመታየት ይሞክራል። ሆኖም ለዴሞክራሲ መስመር የሚያዝጋጅ ሲሆን እስከ አረንጓዴው መስመር የፈለገ መንቀሳቀስ የሚችል ሲሆን ቀይ መሥመሩን ያለፈና ያልፋል ተብሎ የተገመተ ግን እርምጃ ይወሰድበታል። አሁን ባለንበት ሰዓት የፈለገ ሰው አንድም ሁለትም ሆኖ ፓርቲዎችን ማቋቋም ይችላል። ነገር ግን ከሰላማዊ ሰልፍ ተቃውሞ በመለስና ከህዝባዊ ስብሰባ ውጪ መሆን ግን አለበት።
ሶሸሊስታዊው ደርግ መሬት ላራሹ ቢልም መሬት ግን ለአራሾቹዋ የሆነችው በአዋጁ ላይ በወረቀት እንጅ ህዝቡ ቀድሞ የግለሰቦች ጭሰኛ ነበር በሁዋላም የመንግስት ጭሰኛ ነው የሆነው። በእርግጥ ኢህአዴግ አሁን መሬት የክልሎች ነው ያለ ቢሆንም እውነት የክልሎች ነው ወይ? የሚለውን ማየት ያስፈልጋል።
በልማታዊ መንግስት ምርጫ አለ ነገር ግን ምርጫው ፍትሀዊ አይደለም። አቶ ግርማ ሰይፉ የነጻነት መንገድ ብለው ባወጡት መጽሐፍ ላይ በተለይ የሁለት ሺ ሁለት ምርጫ የኢህአዴግ አሸናፊነት የተበሰረው ተቃዋሚዎች የተሻለ ሥራ ያለመስራት ነው። ብለው ገልጸውታል። ሆኖም ይህን አባባል ታዋቂውና ትሁቱ ምሁር ዶክተር ሀይሉ አረዓያ ደግፈውታል። በእርግጥ ይህቺን ነገር መተቸት አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም አባቶቻችን ወጣቱን አታስጠጉም የሚለው ውትወታ ጎድቶአቸው ይሆናል እንጂ አቶ ግርማ ለኢህአዴግ የሰጡትን እውቅና ዶክተር ሀይሉ አረአያ ማጠናከር ግን ነበረባቸው የሚል እምነት የለኝም።
አቶ ግርማ በፖለቲካ ጉዞአቸው የገጠሙአቸውን ውጣ ውረዶች በገለጡበት በዚሁ መጻፋቸው በ2002ቱ ምርጫ እርሳቸው ፓርላማ መግባት እንዲችሉ ረጂም ስዓት ያለ እንቅልፍ ሰርተው ኢህአዴግ ድምጼን እንዳያጭበረብር አደርጉኝ ያሉአቸውን ታዛቢዎቻቸውን በስም ጠቅሰው ያሞካሹ ሲሆን ሌሎች ተወዳዳሪዎች የተሸነፉት ግን ከሥራ ማነስ መሆኑን በገለጡበት በዚሁ አንቀጽ ኢህአዴግ ስለሰራ እንጂ ስለቀማ አለማሸንፉ ላይ እውቅና የሰጡ አስመስሎአቸዋል። በዚህም የእርሳቸውን ታዛቢዎች ጥንካሬ ሲገልጡ በወቅቱ ሌሎቻችን የመደብናቸው ታዛቢዎች ችሎታና ብቃት ላይ ጥላሸት ቀብተዋል።
በዚህ ጉዳይ ላይዶ/ር ሀይሉ አርዓያም ቢሆን ከየዋህነት በመነሳትና ወጣቱን ለማበረታታት ካላቸው ቅን ፍላጎት የተነሳ ለእርሳቸው ታዛቢዎች እውቅና ስለነፈጉ ቆም ብሎ ማሰቡ ተገቢ ነው። መድረክ ማለት ፕሮፌሰር በየነ ነው። የሚለው አረፍተ ነገርም ቢሆን ሌሎች የመድረኩ አባል ድርጅቶች አመራር ላይ የድፍጠጣ ስትራቴጂ ይሆናል። ይህንንም ዶ/ር ሀይሉ ስላልነቀፉት የደገፉት ያስመስለዋል። ከአቶ ግርማ ጋር የሚያስማማኝ እኔና እርሳቸውን ጨምሮ በተቃውሞ ጎራ ያለን ሰዎች ምንም አልሰራንም የሚለው ሀረግ ነው። እያንደንደችን ለግላችን የሰራነው ስራ ከሀገር አንጻር መመዘን የለበትም። በዚህ በኩል ወጣቱ የፖለቲካ ተንታኝና ቆራጡ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለ የሰጠው አስትያየት አርክቶኛል ምስጋናየ ይድረሰው።
ይህንን እንድል ያደረገኝ የልማተዊ መንግስት ባህሪይ አንዱ ፓርቲዎች በምርጫ እንዲውዳደሩ ማድረግ እንጂ በውድድሩ የተሸለ ነጥብ አምጥተው አንዲያልፉ አይደለም። ለዚህም ነው ኢህአዴግ እንዳያማህ ጥራው እደይበላ ግፋው የሚል ስትራቴጂ ተጠቅሞ በርካታ ፓርቲዎች በምርጫው ሂደት ከአግልግሎት መስጫ ክልል ውጪ ያደረጋቸው። እኔ ፕሮፌስር እንደሚሉት አቶ ግርማን በኢህእዴግ መልካም ፈቃድ ገብተዋል ከሚለው ወገን አይደለሁም። ምክንያቱም ኢህአዴግ መልካም ፈቀድ የለውምና ነው። እንደ እቶ ግርማም እኔ ከሌላው የተሻለ ስለሰራሁ አለፍኩ ሌሎቹ ያልተሻለ ስላልሰሩ የፓርላማ ወንበር አጡ ከሚለው ህሳባቸውም እለያልሁ። በአጠቃላይ ግን ይህንን መጽሐፍ ለማዘጋጀት ያደረጉትን ጥረት ሁሉ አደንቃለሁ።
የልማታዊ መንግስት ሌላው ባህሪይ እርሱ በሚያስበውና በሚያልመው መንገድ ብቻ ነገሮች እንዲሄዱ የመፈለግ ችግር ነው። በልማታዊ መንግስት ከሚያስተዳድረው ህዝብ ፈቃድን አይጠይቅም። ልማት ያመጣሉ ብሎ የሚያስባቸውን ነግሮች ሁሉ በራሱ አንዲፈጸሙ ያደርጋል። በዲሞክራሲያዊ መንግስት ሊስራ የታቀደውን ሁሉ በቀጥታ ህዝቡን ያለብለዚያም ህዝቡ በነጻ ምርጫ በወከላቸው ወኪሎቹ በኩል አማክሮ ስራውን ይጀምራል። ልማታዊ መንግስት ግን ነግሮቹን በራሱ ከጀመረ በሁዋላ ህዝቡን የሚያንቀሳቀስው የተጀመረውን ፕሮጄክት ለማስፈጸም በምዋጮ ነው።
በእርግጥ ትክክለኛ የሆነ ልማታዊ መንግስት ባህሪይ ከተከተለ ለህገር እድገት በተለይ በኢኮኖሚ ለማደግ አማራጭ ሊሆን ይችላል። ኮሪያ በመጀምሪያ አሁን ያለችበትን ደረጃ ለመድረስ ከመነሳትዋ በፊት ሁሉም ነገር ወደ ልማት በሚለው የልመታዊ መንግስት አስተሳሰብ መሠረትዋ ሲሆን እያንደንዱ ኮሪያዊ የሚያስብ የነበረው ስለኮሪያ ነበር። ሁሉም ኮሪያዊ ስለነበረ። ኢህአዴግ ግን የወቅቱን አስትሳሰብ ለማስታገስ ሲል የተከተለው የብሔር ፌዴራሊዝም እያንዳንዱ ሰው ማለት ይቻላል። በኢትዮጵየዊንቱ ላይ ከፍተኛ ጥርጣሬና ኢትዮጵያዊ ስለመሆኑ ከፍተኛ እምነት ማጣት ላይ የወደቀበት ወቅት ላይ ነን። ታዋቂው የፖለቲካ ተንታኝ ጁዋር መሐመድ በራሱ የዚህ አስተሳሰብ ሰለባ በመሆኑ ኢትዮጵያዊነት በግድ የተጫነብኝ ሸክም ነው ለማለት በቅቶዋል። ይህ ክሃያ ዓመት በላይ የወሰደ የብሔር ፖለቲካ በ 5ዓመት ስትራቴጂ ማስተካከል ፈጽሞ አይቸልም።
በእውነቱ ከሆነ ኢህአዴግ የሚከተለው ርዕዮተ ዓለም የቱ እንደሆነ እንኩዋን የዚህ ጽሁፍ ጸሐፊ ገዢው ፓርቲ በራሱ ያውቀዋል ማለት ስህተት ነው። የልማታዊ መንግሥት መጨረሻው የት ነው ይቃጥላል፡፡
No comments:
Post a Comment