የ<ሪፖርተር> ጋዜጠኛ የማነ ናግሽ ባወጣው አንድ ዘገባ በተለይ « ያላነበቡ ገምጋሚዎች» በሚል ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን የሚመለከት አደገኛ ሃተታ አስፍሯል። ተመስገን የነበረውን እውነታ በመግለፅ መልስ ሰጥቷል። ዋናው ትኩረቴ ወዲህ ነው፤ « አደገኛ» ያልኩበት እስክንድር ነጋ በአንድነት ፓርቲ ስብሰባ ላይ ተገኝቶ ንግግር ስላደረገ ብቻ «አሸባሪ» የሚል የነበረከት/ሽመልስ የተለመደ የፈጠራ ክስ ተለጥፎበት እንዲፈረድበት ተደርጓል። አሁን ደግሞ የማነ ይህን <ፈጠራ> ሲያቀናብር ነገ በተመስገን ላይ ምን ሊከተል እንደሚችል በሚገባ ታስቦበትና ታቅዶበት የተደረገ ለመሆኑ መጠርጠር አይከፋም። ሌላው የማነ በዘገባው « ተቃዋሚ ነው ወይስ ጋዜጠኛ ?» ሲል ተመስገንን ለመፈርጅ ሞክሯል። ከዘገባው ጀርባ ካለው <ድብቅና አደገኛ አላማ> ባሻገር ሁለት ጥያቄዎችን የማነ ናግሽ እንዲመልስልኝ እጠይቀዋለሁ፤ የመጀመሪያው፥ ከአንድ አመት በላይ ያስቆጠረው የሙስሊሙ ማህበረሰብ ሰላማዊና ፍትሃዊ ጥያቄ በተመለከተ አንተም ሆንክ አለቃህ አማረ አረጋዊ አንድ መስመር ለመዘገብና ለመፃፍ ያልደፈራችሁት ለምንድነው?…ከማን ብትወግኑ ነው?…መልስ እንደሌለህ ባውቅም..ነገር ግን በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው፥ ስለሙስሊሙ ፍትሃዊ ጥያቄ የማትዘግቡት ለገዢው ፓርቲ በመወገናችሁ ነው! አራት ነጥብ። ..ሁለተኛው፥ ገዢው ፓርቲ ያደረጀውና እራሱን « የጋዜጠኞች ህብረት» ብሎ የሚጠራው ስብስብ « የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን የመፈታት ጥያቄ ውድቅ አደረገው» ተብሎ ለወጣው ዘገባ ለምን መልስ አልሰጠህም?…ጋዜጠኛ ተመስገን ያላለውን ፈጥረህ <ወጥመድ ለማስገባት> ስትለቀልቅና « ተቃዋሚ ወይስ ጋዜጠኛ..» ብለህ በጭፍን ስትፈርጅ…ምነው እነዚህ ጋዜጠኛ ተብዬዎች..ያውም “በማህበር ተሰባሰብን” ብለው በአደባባይ የሚደሰኩሩትን፥ « ጋዜጠኛ ናችሁ ወይስ የበረከት ካድሬዎች?» ብለህ አልጠየክም፣ አልፃፍክም?…ይህን ለማድረግ በጭራሽ አታስበውም።..ታዲያ አንተ፣ አማረ፣ እነዚህ የበረከት ተላላኪዎች የምትሰሩት ከገዢው ፓርቲ የወገነ የካድሬ ስራ አይደለም ?…እናንተ ይህን <ስውር> መሰል ካባ ደርባችሁና በነፃ ጋዜጠኛነት ስታደናግሩ የማይታወቅባችሁ መስሏችሁ ይሆን..? …የማነ አንድ ነገር እግረመንገዴን ልገልፅልህ እወዳለሁ፤ የአንተን ዘገባዎች ማንበብ ያቆምኩት በቀድሞ ጠ/ሚ/ር ዙሪያ በተከታታይ ያወጣኸውን እጅግ የተጋነነ <ዘገባ> ከታዘብኩ በኋላ ነው። < ሟቹን አለም ያጣችው ትልቅና ብቸኛ መሪ > አድርገህ ያቀረብከውን ሳነብ…በቃኝ ብዬ ተውኩት። ..እናስ ይህ ወገንተኛነት አይደለም?…እናንተ ገዢውን ፓርቲ ስትደግፉ «ትክክለኛ ጋዜጠኛ ልትባሉ» ሌላው ግን በተቃዋሚነትና በአሸባሪነት እየተፈረጀ በፈጠራ ክስ ወህኒ ሊበሰብስ?….ይህ ነው የእናንተ የተንሸዋረረ አሳፋሪ <አቋም>። በተጨማሪ፥ አንተም ጠንቅቀህ በቅርብ የምታውቀውን ነገር ልንገርህ፤ ከአለቃህ አማረ ተነጋግራችሁ የወሰዳችሁት <አቋም> የሙስሊሙን ጥያቄና ድምፅ በጋዜጣው ላለመዘገብ አልወሰናችሁም?…ውሳኔያችሁን ተግባራዊ በማድረግ የገዢው ፓርቲ «ታማኝና ደጋፊ» በመሆን ወገንተኝነታችሁን በአደባባይ አላሳያችሁም?…በተለይ አማረና አንተ ከዚህ ቀደም ይስተናገዱ የነበሩ የተቃዋሚ አመራሮችን ለይታችሁ በማውጣት እነዚህን ወገኖች መድረክ አልነፈጋችሁም? ደብዳቤና መግለጫ ከማፈን ባሻገር ስልክ እስካለማንሳት የደረሰ እርምጃ አልወሰዳችሁም?…ይህን ያደረጋችሁት ለነበረከት መስመር (ለገዢው ፓርቲ ሕወሐት ) ተገዢና ታማኝ መሆናችሁን ለማስመስከር አይደለም?…ዘወትር የምትመፃደቁለትና በጋዜጣው የይምሰል የለጠፋችሁት « ነፃ ሃሳብ…» ወዘተ በተግባር የሌለ ባዶ ድንፋታ ወይም የአስመሳይነት ካባ ነው!!
No comments:
Post a Comment