ደግነቱ
የገዛ ልጆቿ የገዛ ወንድሞቻቸውን እያረዱ እናት ኢትዮጵያ ለ17 ዓመታት በደም ታጠበች፤ በሞት ማዕበል ተመታች፤ ጩኸት፣ ለቅሶና ሰቆቃ ነገሰባት፤ ከአገር ወደ አብራክ ክፋዮቿ መታረጃ ቄራነት ተለወጠች፤ በጦርነት ገሞራ ከዳር እስከ ዳር ተናጠች፤ መልከ ዓምድሯ በታንክ፣ በመድፍ፣ በምርታር፣ በሮኬት፣ በቢ.ኤምና በላውንቸር ታረሰ፣ ክላሽን ኮቭ በህዝቦቿ ጆሮ ላይ ለዘመናት አፏጨ፣ ጋራና ሸንተረሮቿ ቀይ ደም ቀለሙ… ይህ ሁሉ የሆነው ነፃነትን ለማምጣት በሚል ነበር፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ አናቶች ዘጠኝ ወር በማህፀናቸው ተሸክመው ያለሀኪም አርዳታ ብቻቸውን አምጠው ወልደው ለዓመታት በጀርባቸው እያዘሉና ጡቶቻቸውን እያጠቡ በድህነት ማቅቀው ያሳደጓቸውን ወንድ ልጆቻቸውን ገብረው የወላድ መሃን ከሆኑ በኋላ፤ ባሎቻቸውን ተነጥቀው ከገለሞቱ በኋላ፤ ወንድሞቻቸውንና አጎቶቻቸውን አጥተው ያለአለኝታና መከታ ብቻቸውን ከቀሩ በኋላ ይመጣል ተብሎ በተስፋ ሲጠበቅ የነበረው ነፃነት የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ፡፡ ያሳዝናል፡፡ የእነኛ ህልቆ መሳፍርት ወገኖቻችን በየጋራ፣ ሸንተረሩ፣ ወንዙና ሸጡ የወዳደቀ አፅም የዱር አራዊትና አእዋፋት ማሽካኪያ ብቻ ሆኖ ቀረ፡፡ “ህልም እልም” አንዳለው ዘፋኙ ሁሉም ነገር የቁም ቀዠት ሆኖ ቀረ፡፡

የበደኖ ወገኖቻችን ጂው ወዳለ ገደል እየተወረወሩ ተጣሉ፤ የተረፉት ደግሞ ልክ አንደ በግ ተጋድመው በስለት ታረዱ፤ የኢትዮጵያ አብራክ ክፋይ የሆኑት አኙዋኮች በክላሽን ኮቭ፣ በመትረየስና በዙ-23 ተጨፍጭፈው በድናቸው በየጥሻው ተጣለ፤ በጎንደር ከተማ አምሃ ኢየሱስ የተባሉ ባህታዊ ደቀ መዝሙሮችና ስብከት ተከታታይ የሆኑ ምዕመናን በደደቢት በረሃ ወታደር ተጨፈጨፉ፤ በ1993 ዓ.ም የዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአደባባይ በግፍ ተረፈረፉ፤ በ1997 ዓ.ም ለተቃውሞ ሰልፍ የወጡ ወጣቶች በደም መንኩሶ ከአናቱ ላይ ቀይ የዘረኝነት አክሊል በደፋው አግአዚ ኮማንዶ ስናይፐር ግንባር ግንባራቸውን እየተመቱ ጭንቅላታቸው ፈርሶ ለገናዥ ያስቸገረው አስከሬናቸው በየጎዳናው ተዘራ፤ ከኤርትራ ጋር በተደረገው ጦርነት መቶ ሺህ የድሃ ልጆች በከንቱ አንደ ቅጠል ረገፉ… ከ17 ዓመታት የእርስበርስ መበላላት በኋላ ህወሓት በተባለ ቡድን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተፈፀመው ግፍ ይህ ብቻ አይደለም፤ ሁሉም አንድ በአንድ ይዘርዘር ቢባል ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካን የሚያክል ግዙፍ መጽሓፍ ይወጣዋል፡፡
አሁንም ቢሆን ግፉ ተጠናክሮ አንደቀጠለ ነው፡፡ እልፍ አዕላፍ ወገኖቻችን አሸባሪ እየተባሉ በየወህኒ ቤቱ ውስጥ ታጉረው በከፋ የእስር ሁኔታ አሳር ፍዳቸውን እያዩ ይገኛሉ፤ የኢትዮጵያ የነገ ተስፋ የሆኑ ወጣቶች በደህንነት ሰዎች እየታፈኑ ወደተለያዩ ስውር የምርመራ ማዕከላት እየተወሰዱ ከደርግ ጊዜ ባልተለየ ሁኔታ እየተደበደቡ፣ በኮረንቲ እሳትና በአሲድ እየተቃጠሉ ይገኛሉ፤ የህወሓትን የግፍ አገዛዝ የሚቃወሙ የትግራይ ወጣቶች የቀን ጀምበር ከሰባት ሰዓት በኋላ ከምትከሰትበትና ደደቢት በረሃ ውስጥ ከሚገኝ ባዶ ስድስት የተባለ የትግራይ ጓንታናሞ ታስረው እጅግ በጣም በከፋ ሰቆቃ ላይ ይገኛሉ፤ በሚናገሩት ቋንቋ ልዩነት ብቻ ምንም የማያውቁት ደሃ ገበሬዎች ቤት ንብረታቸውን እየተነጠቁና በድብደባ አካላቸውን እያጡ በመፈናቀል ላይ ይገኛሉ…
ወያኔ ኢህአዴግ እሱ ራሱ የሚፈጽምብን ግፍና በደል አልበቃ ብሎት ጭራሽ ወገኖቻችንን ባህር ተሻግረው በመጡ የውጭ አገር ሰዎች እያስደበደበና እያሳረደ ይገኛል፡፡ አቶ ጥላሁን እራንዱፋ ኢተያ የተባለ አንድ አጁና አንድ እገሩ በድብደባ ሽባ የሆኑ ወጣት ለኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ አንደገለፀው በምስራቅ ወለጋ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ለመንገድ ስራ ተብሎ ወደ አካባቢው በመጡ ቻይናዊያን ከፍተኛ ግፍና ሰቆቃ እየተፈፀመባቸው ነው፡፡ አለት የቆፈሩበትን፣ ደንጋይ የፈነቀቀሉበትን፣ የፈለጡበትንና የፈጩበትን፣ አሸዋና ሲሚንቶ ያቦኩበትን የላባቸውን ዋጋ ደመወዛቸውን ተከልክለው አንደባሪያ ከመቆጠራቸው በላይ በድብደባ አካላቸው እየጎደለ ነው፡፡ ጣልያንስ ከዚህ በላይ ምን አድርጎናል፡፡
ኧረ በዛ! ኧረ በዛ! ኧረ በዛ! ኤሎሄ! ኤሎሄ! ኤሎሄ! ላማ ሰበቅታኒ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ ፈጣሪ ዘርግታ ለምን ረስቶ ተዋት? “እስከማዕዜኑን” ለመሆኑ እስከ መቼ ድረስ ነው አንደዚህ የግፍ ግፍ እየተፈፀመብን አልቅሰን ዝም ብለን ህሊናችን እየደማ የምንኖረው? ኢትዮጵያስ እስከ መቼ ነው የወያኔ ኢህአዴግና የሆዳም አጨብጫቢዎች አገር ብቻ ሆና የምትቀጥለው?
ያለምንም ማጋነን ይህንን ፅሁፍ ስፅፍ በዓይኖቼ አንባ አውጥቼ ስቅስቅ ብዬ እያለቀስኩ ነው፡፡ ግን ዜመኛው በድምፁ አንዳንቆረቆረው
“ወንድ ልጅ ሲከፋው ኑሮ ሲመርበት
ይሰደዳል ከዱር ቀን ሲጨልምበት
ምንጥቃት ቢገባው በሃዘን ቢጎዳ
የወንድ ልጅ አንባ አይፈስም በሜዳ፡፡” አዎ ልክ ነው የወንድ ልጅ እንባ ምንም ቢዘገይ አሲድ ሆኖ በዳዮቹን እየበላ በጣጥሶ መፍጀቱ አይቀሬ ነገር ነው፡፡
ኧረ መረረን! ኧረ መረረን! ኧረ መረረን የት አንሂድ!? አዎ ጆሮ ያለው ይስማ ይህ የወገኖቹ ሰቆቃ በእጅጉ ያንገበገበው የአንድ ኢትዮጵያዊ ብላቴና የምሬት ድምፅ ነው፡፡ የጉልበት አገዛዝ አንገፈገፈን፤ አንደ ሳማ በላን፤ አንደ አሬት መረረን፤ የት አንግባ? የተፈጠርንባትን የኢትዮጵያን ምድር ለቅቀን የት ብለን አንሂድላቸው? ሌላ አገር የለን፡፡ ልክ አንደ እነሱ ጫካ አንዳንገባ መልሰን የገዛ ወንድሞቻችንን መውጋት ነው የሚሆነው፡፡ ደግሞም ሰው በመግደል ብቻ ነፃነት ሊመጣ አንደማይችል ከህወሓት ታሪክ ተምረናል፡፡ ታድያ ከወያኔ ኢህአዴግ ግፍ የተሞላበት የጠመንጃና የጉልበት አገዛዝ ቀንበር አንዴት አንገታችንን አናሹልክ? ከእሱ አልፎ እኮ ለውጭ አገር መንግስት ጭምር እያስረገጠን ነው፡፡ ቅኝ እያስገዛን እኮ ነው፡፡ በሰብአዊነት መቃብር ላይ የሚገነባ መንገድና ህንፃ ከምኑ ላይ ነው ጠቀሜታው? ከሰብአዊ ልማትና ከቁስ ልማት የትኛው ይቀድማል? ደግሞስ ለማ የተባለው ልማት መች ከችጋርና ከረሃብ አወጣን፤ አሁንም ለማኞች ነን፤ እኛ ነፃ በነበርንበት ዘመን በአውሮፓዊያን የቅኝ ግዛት ቀንበር ውስጥ የቆዩት በርካታ የአፍሪካ አገራት ዛሬ በዲሞክራሲም በኢኮኖሚም አድገት የትና የት ሲደርሱ እኛ አንደዚህ ተዋርደን የዓለም ሁሉ መሳለቂያና መሳቂያ አንሁን፡፡ ወጣቶች ኃላፊነቱ እኮ ከእኛ ትከሻ ላይ ነው ተከምሮ ያለው ምን እናድርግ? የእነጥላሁን ግዛው፣ ማርታ፣ ዋለልኝ… አደራ አኮ አለብን፡፡

No comments:
Post a Comment