በመንግሥታችንና በኢትቪ ደጋግሞ ከሚነገሩን ነገሮች አንዱና ዋነኛዉ ሀገራችን ሁለት አሃዝ (11%) የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች መሆኑን ነዉ:: በርግጥ አሃዙ ላይ የሚነሱ በርካታ ጥያቄወች ቢኖሩም እስኪ መንግስት እንደሚለዉ ሀገሪቱ በተከታታይ ሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ እድገት እያስመዝገበች ነዉ የሚለዉን ስታትስቲክስ እንቀበልና ያልተፈቱልንን እንቆቅልሾች እንጠይቅ::
፩. የኢኮኖሚ እድገት አለ ካልን የኢኮኖሚ ልማትስ?
በኢኮኖሚክስ የኢኮኖሚ እድገት (economic growth) እና ኢኮኖሚ ልማት (economic development) የተለያዩ ነገሮች ናቸዉ:: የኢኮኖሚ እድገት ማለት ጠቅላላ ሃገራዊ ምርት (gross domestic Product- GDP) መጨመር ማለት ሲሆን የኢኮኖሚ ልማት ደግሞ የኢኮኖሚ እድገት እና ሌሎች ነገሮችን ያካትታል::
የኢኮኖሚ ልማት ማለት የኢኮኖሚ እድገት ሲደመር ከእድገቱ የተገኝዉ ሀብት ክፍፍል ፍትሃዊነት ፣ እድገቱ የህዝቡን መሰረታዊ ፍላጎቶች ማለትም ምግብ፣ መጠለያና ልብስ በማሽሻል ያመጣዉ ለውጥ ፣ እድገቱ ያመጣዉ የአካባቢ መራቆት
(environmental impact) ፣ እድገቱ ማህበራዊ ጠንቆችን ማለትም ወንጀልን፣ ሴተኛ አዳሪነትን፣ አደንዛዥ እጭ ተጠቃሚነትን ፣ ጎዳና ተዳዳርነትን ወዘተ በመቀነስ ያመጣዉ ለውጥ ፣ በሀገሪቱ ዉስጥ ከኢኮኖሚ እድገቱ ጎን ለጎን የተመዘገቡ የዲሞክራሲ እና ሰብአዊ መብት መሻሻሎች ( ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዱ መስፈርት ሁኗል) እና ልሎችንም የህብረተሰቡ አኗኗር ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ነገሮችን ያካትታል ፤ ለዚህም ነዉ የኢኮኖሚ ልማት መለኪያወች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻሉና እየተለወጡ በመሄድ ላይ ያሉት:: ባጭሩ የኢኮኖሚ እድገት በአሀዝ የሚቀመጥ ሲሆን የኢኮኖሚ ልማት ግን የኢኮኖሚ እድገትን ተከትሎ በህብረተሰቡ አኗኗር ላይ የመጣዉን ለዉጥ በመመዘን ይገለፃል:: ስለዚህ በየዓመቱ 11 % የኢኮኖሚ እድገት አለ ካልን ይህ እድገት የህብረተሰባችን አኗኗር ላይ ምን አይነት ለዉጥ አመጣ? ማለትም የኢኮኖሚ ልማትችን ምን ያህል ነዉ? ፩. የኢኮኖሚ እድገት አለ ካልን የኢኮኖሚ ልማትስ?
በኢኮኖሚክስ የኢኮኖሚ እድገት (economic growth) እና ኢኮኖሚ ልማት (economic development) የተለያዩ ነገሮች ናቸዉ:: የኢኮኖሚ እድገት ማለት ጠቅላላ ሃገራዊ ምርት (gross domestic Product- GDP) መጨመር ማለት ሲሆን የኢኮኖሚ ልማት ደግሞ የኢኮኖሚ እድገት እና ሌሎች ነገሮችን ያካትታል::
፪ የኢኮኖሚ እድገትና መሰረታዊ ፍላጎቶች
አንድ ሰዉ ለመኖር የሚያስፈልጉት መሰረታዊ ነገሮች ምግብ፣ መጠለያና ልብስ ናቸዉ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ ዉስጥ አብዛኛው ሰዉ የወር ገቢዉን እነዚህን መሰረታዊ ነገሮች ለመግዛት ወይም ለማሟላት ይጠቀምበታል:: ለምሳሌ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተዉ አዲስ አበባ ዉስጥ የሚኖረዉ ሕዝብ በአማካኝ የገቢዉን 51 ከመቶ ለምግብ መግዢአነት ያዉለዋል:: ከዚህ ቀጥሎ ትልቁ ወጭ የቤት ክራይ ነዉ:: ስለዚህ የምግብና የቤት ክራይ ከፍና ዝቅ ማለት የህብረተሰቡንም አኗኗር አብሮ ከፍና ዝቅ የሚያደርግ ነዉ:: ታዲያ 11 % የኢኮኖሚ እድገት አለ እየተባለ የምግብ ዋጋና የቤት ክራይ ለምንድን ነዉ ከቀን ወደቀን እየጨመረ ሕዝቡን ወደ ብልፅግና ሳይሆን ወደ ጉስቁልና የሚያመራዉ?
በሌላ በኩል ከ 15 እና 20 ዓመታት በፊት አነስተኛ ገቢ ያላቸዉ ሰወች ለምሳሌ የአንደኛ ደረጃ መምህራን በሚያገኙአት 400 እና 500 ብር ደሞዝ ከመንግስት ቦታ በነፃ እያገኙ በዚች ደሞዛቸዉ ቤት ሰርተዉ የቤት ባለቤት መሆን ብቻ ሳይሆን ዶርሞችን በመስራት እያከራዩ ተጠቃሚ ይሆኑ ነበር ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ እንኩአን የ አንደኛ ደረጃ መምህራን ባንፃሩ የተሻለ ገቢ ያላቸዉ የዩኒቨርሲቲ መምህራን እንኩአን የቤት ባለቤት ለመሆን ተስኗቸዋል፤ ኮንዶምንየምም እንድሚታወቀዉ ዋጋዉ የማይቀመስ ከምሆኑም በላይ ቤተሰብ ላለዉ ሰው አመች አይደለም::በተጨማሪም የኮንዶሚኒየም ቤቶችን በትልልቅ ከተሞች ማግኘት ከባድ ሁኖ ሳለ በተመሳሳይ ዲዛይንና ወጭ ባነስተኛ ከተሞች የተሰሩት የኮንዶሚኒየም ቤቶች ደግሞ ገዢ አጥተዉ ለ ዓመታት ተዘግተዉ የሚገኙት ምክንያቱም በአነስተኛ ከተሞች አንድ ባለ አንድ መኝታ ኮንዶሚኒየም ቤት ለመግዝት ከሚጠየቀዉ ባነሰ ዋጋ አንድ እራሱን የቻለ ግቢ ያለዉ ትልቅ ቤት ከግለሰብ መግዛት ስለሚቻል ነዉ :: ይህ በራሱ ትልቅ የፖሊሲ ዉድቀት ነዉ::
አሁን ያለዉ ወጣት በሕግ የተፈቀደለትን የመኖሪያ ቤት ባለቤት የመሆን ወይም ለመኖሪያ ቤት ግንባታ የሚሆን ቦታ የማግኘት መብቱን መንግስት ስለገደበዉ ወይም በተሳሳተ ፖሊሲ ስላከሸፈበት ለፍቶ የሚያገኘዉን ወርሓዊ ደሞዝ አብዛኛዉን ለቤት ክራይ እየከፈለ የተደላደለ ኑሮ ሳይኖር ትዳርን እየፈራ እንዲሁ ወጣትነቱ እያለፈበት ይገኛል:: ችግሩ በዚህ ከቀጠለ እነዚህ ወጣቶች ነገና ከነገ ወዲያ ወደ ጉልምስና እና ወደ እርጅና ሲገቡ ምን አይነት ችግር ሊያጋጥማቸዉ እንደሚችል ከወዲሁ ሲታሰብ ያስፈራል:: ከሁሉም የሚገርመዉ ለእኛ ለዜጎች ለአንገታችን ማስገቢያ ቤት ለመስራት የምትሆን አነስተኛ ቦታ ማግኘት ተከልክለን ከሕንድና አረብ ሃገራት ለመጡ ባለሀብቶች ግን በመቶ ሽ ሄክታር ቦታ በነፃ በሚያሰኝ ዋጋ ይታደላል ፤ ግን ለምን? በተጨማሪም 11 ፐርሰንት የሚያድገዉ ኢኮኖሚ የቤት አቅርቦትን በማሻሻል ሕዝቡን በተለይም ወጣቱን ላንገቱ ማስገቢያ ቤት እንዳያገኝ ማድረግ የተሳነዉ ለምንድን ነው?
፫ 11 % የኢኮኖሚ እድገት አለ ካልን የእድገቱን ፍሬ ማን በላዉ?
ከላይ እንደተገለፀዉ ሀገሪቱ 11 ፐርሰንት ማደግ ጀመረች መባል ከጀመረ አንስቶ አብዛኛዉ ሕዝብ ከቀን ወደ ቀን ኑሮ እንደ መርግ እየከበደዉ መጥቷል ታዲያ የዕድገቱን ፍሬ ማን በልቶት ነው ሕዝብ ኑሮ እንደዚህ የከበደዉ?
አንዳአንድ ሰወች ከላይ ለተጠየቁት ጥያቄወች ከተለያዩ ዌብ ሳይቶች ላይ ሪፖርቶችን በመዉሰድ እድገትም ልማትም አለ ብላችሁ እንደምትከራከሩ እገምታለሁ እኔ ግን የምለዉ ሌሎች ስለኛ የፅፉትን ሪፖርት ማስረጃ እያደረግን እንድንከራከር ሳይሆን ቀን ተቀን የምንኖረዉን ኑሮ በግልፅ እንድንወያይበትና ሃሳብ እንዲንሽራሸር ነዉ ከሃሳብ መንሸራሸር መፍትሄ ሊመጣ ይችላልና::
No comments:
Post a Comment