Friday, July 12, 2013

*** አገር ጠልቶ ወዴት? ****ኢትዮጵያዊ አይደለውም የሚያስብል ምን አለና!*

ደሃም ሆንን ሀፍታም አገርን አፍቅራት!እስከ መቼ ነው የኋሊት የምንሸራተተው ?
የሰው አገር እንደሆነ የሰው ነው።በሰው አገር ቢለብሱ፣መኪና ቢነዱ፣ቤት ቢገዙ ኧረ ምንም ቢያደርጉ እንኳን እንደናት አገር ማን አለና!!

ስለታላቅዋ ውድ ሀገራችን፤ ስለታታሪውና ስለሀገር ወዳዱ ድሀ ሕዝባችን የእርግማን ልጆች ባይቀበሉትም በታሪክም ሆነ በአፈ ታሪክ ተደጋግሞ የሚነገር አንድ እውነት አለ፡፡ በዘመናዊ የመንግሥት አስተዳደር፤ በዓለም አቀፍ የንግድ ግንኙነትና ዛሬም ድረስ የዓለም ሕዝብ በሚደነቅባቸው በልዩ የሀገር ቅርሳ ቅርስ ግንባታዎች መስክ በጥንታዊውሥልጣኔ ቀዳሚውን ሥፍራ ከያዙት የዓለማችን ሀገሮች ተርታ ነበርን፤ ነንም፡፡

አያቶቻችን፤ አባቶቻችንና እናቶቻችን ይህን እንዴት ማድረግ ቻሉ የሚለውን ለመመለስ እንደኛ የሆድ መሙያ ትምሕርት ሳይማሩ የተመራመሩ፤ ኅብረትና ፍቅር የነበራቸው፤ ግፍንና በደልን መሸከም የማይችሉ ነፃነት አፍቃሪዎች፤ሀገራቸውን፤ ሕዝባቸውንና መጪውን ትውልድ ጭምር ይወዱ ስለነበር አስደናቂ ታሪክ ለቀጣዩ ትውልድ አስተላልፈዋል።
ታዲያ በአሁን ሰዓት ትንሽ ፊደል ቆጠርን ያልን ሰዎች በአገር ፍቅር ማበድ ሲገባን የታሪክ አጥፊዎች ሆነን ሰው ማወናበድ ምን የሚሉት የበሽታ አቧዜ ነው ባካችሁ?

ይኽ ትውልድ የሰለጠነው ዓለም ሕዝብ ባለቤት ከሆነባቸው የዘመኑ የሥልጣኔ ግኝቶች መካከል አንድም የራሳችን አዲስ ነገር ሳንጨምርበት ቢጤአቸውን ያልተኩት አባቶቻችን የሠሩትን ድንቃ ድንቅ እስከ ዛሬም እንደ እንሰሳት እየበላን፤ እያወራን ስናነሳ፤ ስንጥል እየኮሰን ከአረጀንበት ታሪክ መላቀቅ አልቻልነም። ይህ ለምን ሆነ ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው።

መንግስት ሲበድለው ተነስቶ አገርን መጥላት ትክክለኛ አመለካከት አይደለም።ችግራችን ከገዥው ፓርቲ እንጂ ከአገር አይደለም።እንደዚ ያለ አመለካከት ያለው ሰው ፊደል መቁጠረ ለልማት ሳይሆን ለጥፋት ነው።አሁንም ቢሆን ልቦና ይስጥልን ከማለት ውጪ ምን ይባላል?

ይሁን እንጂ አሁን በምንኖርበት የሀያ አንደኛው ክፍለ ዘመን አንድን ሀገር የማጥፋትም የማልማትም ሥልጣንና መብት ያለው ሕዝብ ነው፡፡ ሕዝብ በሀገሩ ላይ ፈላጭ ቆራጭ ብቻም ሳይሆን የሚወክለውን መንግሥት በራሱ ፈቃድያለምንም ተፅዕኖ የሚመርጥ፤ የሚያዋቅር ባልፈለገ ጊዜም የሚሽር አድራጊፈጣሪ ነው፡፡ ይህ አባባል በሀገራችን በወረቀት ላይ ተፅፎ ዕለት በዕለትበመንግሥት የፕሮፖጋንዳ ማሰራጫዎች የጆሮአችን ታምቡር እስኪሸነተር ድረስ እየተነገረን ነው።ይኽን ለማጥፋት መታገል እንጂ
ኢትዮጵያዊ አይደለውም የሚያስብል ምንም ነገር የለም።
አሁንም በድጋሚ ልቦና ይስጥልን!!!

መከፋፈል የትም አያደርስም!!!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment