Sunday, July 14, 2013

ቤተ መንግስቱ በጩኸትም ይነቀነቃል!!

ይድረስ ለዳንኤል ብርሃኔ እና መሰሎቹ!
በመጀመሪያ የመፅሃፍ ምረቃ ላይ ለመገኘት አይደለም የሄድከው፡፡ ይህ ድብቅ ሴራህ ይታወቃል፡፡ እከሌ ይህን ተናገረ እከሌ እንዲህ አለ ለማለት ብለህ ለላኩህ ምድራዊ ጌቶች ሪፖርት ለማድረግ እንጂ፡፡ ‹‹ተመስገን ፓርላማ መግባት ብቻ ሳይሆን የቤተ መንግስቱን አጥር መነቅነቅ አለብን›› ላልከው እና ‹‹ግርማም እንዲህ ሲል ለማስተባበል ሞከረ አሁን ኢህአዴግ የተመስገንን አጣሞ ይጠቀምበታል፣ ተመስገን ግን ጥይት መተኮስ የሚችል አይመስለኝም በማለት ማብራሪያ አይሉት ማረሚያ ሰጠ›› ያልከው ሁሉንም ነገር አንተና የላኩህ ገዢዎችህ ጥቅም ጋር እያናኘህ እንጂ የተባለው እንደዛ አልነበረም፡፡ በቦታው ባልኖር ይገርመኝ ነበር፡፡ አንተና መሰሎችህ ግን እንዲህ ናችሁ፡፡ ቤተ መንግስቱን መነቅነቅ እንደሚቻል ተመስገን ሲገልፅ በሰላማዊ ትግል ውስጥ መሞት እንጂ መግደል እንደሌለ ለመሞት እንጂ ለመግደል እንደማንሄድ፣ ሊተኮስብን እንጂ ልንተኩስ እንደማንሄድ፣ ልንመታ እንጂ ልንመታ እንደማንሄድ በደምብ አድረጎ አስረድቷል፡፡ አንተ ግን ቤተ መንግስት መነቅነቅ የምትለዋን ብቻ ለይተህ ለሴራህ ተጠቀምካት፡፡ 
በርግጥ አይፈረድባችሁም አንተና መሰሎችህ ቤተ መንግስት መነቅነቅ ሲባል በጠመንጃ እንደሆነ ብቻ ነው የምታውቁት ፡፡ ያደረጋችሁት እንደዛ ነዋ፡፡ የኢያሪኮ ግንብ በምን እንደፈረሰ አታውቁም፡፡ አቶ ግርማም ገና ንግግር ሲጀምሩ እንዲህ ነበር ያሉት ‹‹ተመስገን ቤተ መንግስቱን መነቅነቅ ብሎ ስለተናገረ ብቻ እዚህ የፈራን ሰዎች እንኖራለን፡፡›› ነበር ያሉት ከዛም አስከትለው ቤተ መንግስት በጩኸትም እንደሚነቀነቅ ተናግረዋል፡፡ አየህ አንተ ሁሌም የምትወስደው የሚስማማህን እና ለምትፈልገው ሴራ እንዲጠቅምህ አድረገህ ነው፡፡ እናም እውነቱን ለማየት አይቻልህም፡፡ በጥቅም ታውረሃልና፡፡ አያለሁ ትላለህ እንጂ አታይም ታወረሃል፡፡

ተመስገን ስለ ምርጫ 2007 ሆነ ከዛ ወዲያ ስላለው ምርጫ የተናገረው በደንብ አልሰማኸውም እንዳልል በአዳራሹ ነበርኩኝ ብለኃል፡፡ለነገሩ እኛ እውነት ልሰማ አንተ ለሴራህ የሚሆኑ ነጥቦችን ነቅተህ ስትጠብቅ ስለነበር እውነቱን እደግምልሃለሁ፡፡ አንተ እንዳልከው ሳይሆን እሱ ሊል የፈለገው በሰላማዊ ትግል መስመር ውስጥ እስካለህ ድረስ 20072012 ብሎ መጠበቅ እንደማይቻል ነው፡፡ እንጂ ጉልበት ማባከን ነው አላለም፡፡ አየህ ነገሮችን የምትወስደው ለራስህ በሚመችህ መንገድ እና ሌሎችንም ለማሳሳት ሆን ብለህ እንደሆነ ያስታውቅብሃል፡፡ 
‹‹
እና ተመስገን በምርጫ ካልሆነ፣በጥይት ካልሆነ፣እንዴት ይሆን የቤ ተመንግስቱን አጥር የሚነቀነቀው ?›› ብለህ ጠይቀሃል መድገም ነው ሚሆንብኝ ሰላማዊ ትግል ማለት ለናንተ በምታዘጋጁት ድራማ አይሉት ምርጫ መወዳደር ይመስላችኋል፡፡ ሰላማዊ ትግል ምን እንደሆነ አታውቁም ምክንያቱም አላደጋችሁበትም እና ጦረኝነትና ሰላማዊ ትግል የሚገኛኙበት ነገር የለም፡፡ ላንተ ቤተ መንግስት የሚንቀጠቀጠው በጥይት ብቻ ነው፡፡ ለኛ ግን በጩኸት እንደሚነቀነቅ እናውቃለን፡፡ ይሄንንም የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ታየዋለሁ፡፡ አንባገነኖች ሁሌም እንዲህ ናቸው ፡፡ መማርን አያውቁም፡፡ ቢያንስ የመማሪያ ጊዜ እንዲኖራቸው አይፈልጉም፡፡ እናም ወድቀው መሳለቂ እስኪሆኑ ድረስ እንጂ እናም የአንተ ጌቶችም ይህ እጣ ፈንታ ነው የሚደርስባቸው፡፡ አትጠራጠር፡፡ የዛኔ አንተ መግቢያ ቀዳደ ይጠፍሃል፡፡

ሊገባህ የሚገባው ግን ይህ ትውልድ የናንተን ከፋፍለህ ግዛ የሚቀበል እንዳይመስልህ፡፡ የዚህ ትውልድ ወጣት ያንተን የሴራ እንደወረደ የሚቀበለል እነዳይመስልህ፡፡ እውነትን እንመረምራለን፡፡ እውነትን እንይዛለን፡፡ አትጠራጠር እውነትን ይዘን አናፍርም እና ባትለፋ ጥሩ ነው፡፡ ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል የሚለው ነገር የሚሰራ እንዳዬመስልህ ምክንያቱም እውነትን የሚመረምር፣ የሚፈልግ ትውልድ መጥቷልና፡፡ 

የነፃነት ናፍቆት! 

ትግሉ ይቀጥላል!!

No comments:

Post a Comment