ስለታላቅዋ ውድ ሀገራችን፤ ስለታታሪውና ስለሀገር ወዳዱ ድሀ ሕዝባችንየእርግማን ልጆች ባይቀበሉትም በታሪክም ሆነ በአፈ ታሪክ ተደጋግሞ የሚነገርአንድ እውነት አለ፡፡ በዘመናዊ የመንግሥት አስተዳደር፤ በዓለም አቀፍ የንግድግንኙነትና ዛሬም ድረስ የዓለም ሕዝብ በሚደነቅባቸው በልዩ የሀገር ቅርሳ ቅርስግንባታዎች መስክ በጥንታዊው ሥልጣኔ ቀዳሚውን ሥፍራ ከያዙት የዓለማችንሀገሮች ተርታ ነበርን፤ ነንም፡፡
አያቶቻችን፤ አባቶቻችንና እናቶቻችን ይህን እንዴት ማድረግ ቻሉ የሚለውን ለመመለስ እንደኛ የሆድ መሙያ ትምሕርት ሳይማሩ የተመራመሩ፤ ኅብረትናፍቅር የነበራቸው፤ ግፍንና በደልን መሸከም የማይችሉ ነፃነት አፍቃሪዎች፤ሀገራቸውን፤ ሕዝባቸውንና መጪውን ትውልድ ጭምር ይወዱ ስለነበር አስደናቂታሪክ ለቀጣዩ ትውልድ አስተላልፈዋል፡፡ ነገር ግን ይኽ ትውልድ የሰለጠነውዓለም ሕዝብ ባለቤት ከሆነባቸው የዘመኑ የሥልጣኔ ግኝቶች መካከል አንድምየራሳችን አዲስ ነገር ሳንጨምርበት ቢጤአቸውን ያልተኩት አባቶቻችን የሠሩትንድንቃ ድንቅ እስከ ዛሬም እንደ እንሰሳት እየበላን፤ እያወራን ስናነሳ፤ ስንጥልእየኮሰን ከአረጀንበት ታሪክ መላቀቅ አልቻልነም። ይህ ለምን ሆነ ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው።
ያለው መንግሥት በመሣሪያና በኢኮኖሚ ራሱን ማደራጀቱ አይታበልም። ይሁን እንጂ ሕዝብ ያልመረጠውና ያልደገፈው አገዛዝ በኃይል ሥልጣኑን ማስቀጠል እንደማይችል ካለፈ ታሪካችን መረዳት ይቻላል። ይኽን ጨቋኝ አገዛዝ ከስሩ ለመመንገል በመጀመሪያ ደረጃ ማነው ለትግሉ ፋና ወጊ ሆኖ ቀዳሚ መሆንያለበት የሚለውን ፖለቲከኞችም፤ ደጋፊዎችም በግልጽ ሊያውቁት ይገባል፡፡ከ1966 ዓ.ም. ሕዝባዊ አብዮት በፊት የነበረው የሀገራችን የትግል ተሞክሮ ታሪክወደ ኋላ ተስቦ መመርመር ተገቢ ይመስለኛል። የውጪ ጠላትን ለመከላከልምሆነ በውስጥ የመንግሥት ለውጥ ጉዳይ ግምባር ቀደም ታጋዮቹና የትግሉአንቀሳቃሽ መሪዎች በዋነኛነት ራሳቸው የሀገር መሪዎች፤ ወይም ወደፊት በተሻለሁኔታ ሀገር ልንመራ እንችላለን ብለው የተነሳሱ ግለሰቦች፤ በዕድሜና በዕውቀትየበሰሉ ቆራጦች እንደነበሩ ከኋላ ታሪካችን መረዳት ይቻላል፡፡
በዕድሜና በዕውቀት የበለፀጉ ታዋቂ ዜጎች በጦር ሜዳም ሆነ በሠላማዊው ትግልግምባር ቀደም ሆነው እስራቱን፤ እንግልቱን፤ ሞቱንም ሆነ፤ ከኑሮና ከሥራመፈናቀሉን ቀድመው እየቀመሱ አርአያ በመሆን ነው። ነገር ግን በተለያየ ጊዜ የተጀመሩ ትግሎች ግባቸውን ያልመቱበት ምክንያት መኖሩ ለሁሉም ግልጽ ይመስለኛል። እንደሚታወቀው ከሕዝባዊው አብዮት መፈንዳት ጋር ተያይዞ የተለያየ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸው በርካታ ቡድኖች ተፈጥረው ነበር። ይሁን እንጂ የንጉሠ ነገሥቱን የሥልጣን መንበር ቀድመው ለመቆጣጠርአሰፍስፈው ሲሽቀዳደሙ ለሀገር የሚበጀውን ጉዳይ ከግብ ለማድረስከመነጋገርና ከመተባበር ይልቅ መገፈታተርና መጠፋፋት ጀመሩ፡
የሥልጣን ጥማቱና ግድያው በተለያዩ ፓርቲዎች መካከል ብቻም ሳይገድብበአንድ ፓርቲ ውስጥ አንድ ዓይነት ዓላማ ኖሮአቸው የተለያየ የትግል ስልትእንከተል በሚሉ ግለሰቦች መካከልም በአሳዛኝ ሁኔታ ግድያዎች ተካሄዱ። ይኼንጊዜ ነው ሌሎችን ከኋላ ሆኖ ወደ እሳት እየማገዱ ራስን በሕይወት የማቆየትናወደ ሥልጣን እርካብ በቀላሉ የመውጣት ክፉ ወረርሽኝ በሽታ በአጭር ጊዜበአገራችን መሠራጨት የጀመረው፡፡ በተለይም በፖለቲካ አመለካከቱ ያልበሰለውን ወጣት በለብለብ የፖለቲካ ትምህርትና ውይይት፤ ወጣቱ ትኩስኃይል ነው፤ አይበገርም፤ ወጣት የነብር ጣት ነው፤ ሀገር የመገንባት የመለወጥ ኃላፊነት የወጣቱ ነው እየተባለ እስከዛሬም ድረስ የሀገራችን አምበገነንመንግሥታትም ሆኑ ተቀናቃኝ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወጣቱን ያለምንም የረባ ውጤት የእሳት እራት ሲያደርጉት ቆይተዋል፡፡
ከላይ በጠቃቀስኳቸው ምክንያቶች ይህ ትውልድ መሰረታዊ ለውጥ ሊያመጣ አለመቻሉ ግልጽ ይመስለኛል።ማንም ያሻውን ይበል እንጂ በእኔ አመለካከት፤ብሔራዊ የሀገርና የወገን ፍቅር ስሜታችንና እምነታችን ከዕውቀት ወለል በታችበማሽቆልቆሉ ለመጪው ትውልድ ደንታቢስ፤ ከመጠን በአለፈ ስግብግብነት ራስወዳዶችና ፈሪዎች ስለሆን ብቻ ነው ሀቁ።
አልፎ ተርፎ አባቶቻችን በደም ገንብተው የአቆዩልንን የሀገርና የሕዝብ አንድነትለማፍረስ ከሚሯሯጡ የውስጥና የውጪ ጠላቶች ጋር ዘላለም ላይኖርአንዳንዶቻችን ለጨቋኝ መንግሥት ተባባሪዎች ሆነን ነፃነት፤ ፍትህና እኩልነትበሌለበት ሀገር ላይ ተሙለጭልጮና አስመስሎ፤ አምታትቶና ዋሽቶ ሆድ አደርመሆን የመሰልጠን ያህል መታየ ከጀምረ ሰነባብቷል።
ይሁን እንጂ አሁን በምንኖርበት የሀያ አንደኛው ክፍለ ዘመን አንድን ሀገርየማጥፋትም የማልማትም ሥልጣንና መብት ያለው ሕዝብ ነው፡፡ ሕዝብ በሀገሩላይ ፈላጭ ቆራጭ ብቻም ሳይሆን የሚወክለውን መንግሥት በራሱ ፈቃድያለምንም ተፅዕኖ የሚመርጥ፤ የሚያዋቅር ባልፈለገ ጊዜም የሚሽር አድራጊፈጣሪ ነው፡፡ ይህ አባባል በሀገራችን በወረቀት ላይ ተፅፎ ዕለት በዕለትበመንግሥት የፕሮፖጋንዳ ማሰራጫዎች የጆሮአችን ታምቡር እስኪሸነተር ድረስእየተነገረን ነው። ይሁን እንጂ ተግባራዊነቱ እንደናፈቀን፤ በደመነፍስ ስንኖር ከአርባ ዓመታት በላይ ተቆጥሮብናል፡፡ለኢትዮጵያውያን ሌብነትና ልመና እጅግ አሳፋሪና ነውር መሆኑ ሃቅ ነው። ነገርግን በብልሹ አስተዳደር ምክንያት ሕዝቡ ልመና እንዲለምድ ተገደደ። ቢሆንም ወያኔ /ኢሕአዴግ ከድሀው ላይ የሰበሰበውን የሀገር ሀብትና የውጪ እርዳታበአደባባይ እየሞጨለፈው ነው። የወያኔ /ኢሕአዴግ መኪና መግዛት፤ ሕንፃመገንባትና የንግድ ድርጅት መክፈት ሌባ! ሌባ!!! ማስባሉ ቀርቶ ጀግንነትሆኖአል፡፡
እጅግ አስገራሚው ነገር ደግሞ “የሌባ ዐይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያድርቅ” እንዲሉመንግሥት ስለፍትህና የሕግ የበላይነት፤ ስለዴሞክራሲና የሕዝብ የሥልጣንባለቤትነት፤ ስለ ሀገር እድገትና ልማት የዜና ማሠራጫዎቻችንን እስከምንጠላቸውድረስ ይደሰኩራል። ተቀናቃኞችን ሁሉ ልዩ ልዩ ሥምና ክስ እየለጠፈባቸውያለፍርድ ዘብጥያ እያወረደ በማሰቃየት የሚፉልለው ከእራስ በላይ ነፋስ በሚልየማይም እውቀት፤ ከሥልጣኑ በቀር ለድሀው ሕዝብም ሆነ ለማንም ደንታየሌለው የሌባውና የዱርዬው ጥርቃሞ አምባገነኑ አገዛዝ መሆኑ ነው፡፡
ዛሬም የወያኔ መንግሥትም ሆነ የዘመኑ የፖለቲካ ተቀናቃኞች እነርሱ ከኋላበጭምብል ውስጥ ሆነው፤ በሚቆጣጠሩዋቸው የዜና ማሠራጫዎች ቀረርቶናፉከራ፤ ውዳሴና አጓጉል ቅስቀሳ እያሰሙ የፈረደበትን ልምድ አልባ ወጣት ወደ“የሚንቀለቀለው የሞት እሳት” ብቻውን ሊነዱት ይፈልጋሉ፡፡ የቀደሙትአባቶቻችን ልጅ የአቦካው ለእራት አይበቃም ይሉ ነበር፡፡ይህ አባባል አሁንባለንበት ዘመን ሙሉ ለሙሉ ያስኬዳል ባይባልም በዕድሜና በዕውቀትያልበለፀጉ ለጋ ወጣቶች እንደሚባለው ግምባር ቀደም ሆነው ሀገራዊ ኃላፊነትተሸክመው የትግልና የሀገር መሪ መሆን እንደማይችሉ ያለፈውን ታሪካችንንከማየት ውጪ ሌላ ነጋሪ አያሻም።
የጋራ ራዕይና የሩቅ ዓላማ ላይኖረን፤ ላንፋቀር፤ ላንግባባና አንድ ልብ ኖሮንላንወያይ የተረገምንና ለውድቀት የታተምን ያህል የጥቅማ ጥቅምና የሆድ አዳሪባርነት ተጭኖን እርስ በርስ እየተጠፋፋንና ከኋላ በሾኬ እየተጠላለፍን በአንድቦታ ደርቀን ቆመናል፡፡ የዚህ ዓይነት የእንስሳት ሕይወት ማብቂያው መቼ ይሆን?
ሀገርና ለወገን ፍቅር መስዋዕት መሆን፤ ጉስቁልናና ድህነት ስላጎበጠው ወገናችንመብት መታገል፤ ለመጪው ትውልድ ወይም ለራሳችን ስሜት ስንልያለፈቃዳቸው ለወለድናቸው ልጆቻችን የተሻለ ነገር ስለማቆየት ማሰብእንደቂልነት መታየት ጀምሯል፡፡ በዚህ ባለንበት አስቸጋሪ ወቅት ላይ የሀገራችንፖለቲከኞች ያልተገነዘቡትና ተረድተውትም ከሆነ መፍትሄ የአላበጁለት ጉዳይበአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመንግሥት የዕለት ተዕለት ክንዋኔዎች ይልቅለሃይማኖታዊ መሪዎችና ክንዋኔዎች ትልቁን ዋጋ ስለሚሰጥ፤ መሪዎች ሁሉከፈጣሪ የተሰጡን ምድራዊ አድራጊ ፈጣሪዎች በመሆናቸው ልንገዛላቸውእንደሚገባና ከዕኩይ ሥራዎቻቸው ይልቅ ለህልውናቸው ሲሉ በግድ አምጠውለሚሠሩአቸው ጥቃቅን ጥገናዊ ለውጦች አድናቆቱን እየቸረ የግፍ ፅዋው ጢምብሎ እስከሚሞላ በተስፋ የሚጠብቅ እንጂ በየአንዳንዱ የውስጥ ጉዳይና የበደልዓይነት መብትና ግዴታውን በውል ተረድቶ፤ ጉልበቱን አስተባብሮ፤ በሕዝባዊኃይሉ ተጠቅሞ የተነጠቀውንና የጎደለበትን ከማስመለስ ይልቅ፤ እንዴት ለምንብለው የሚጠይቁ ልጆቹን በግፍ ለሚገድሉና አስረው ለሚያሰቃዩ፤ እሱንምወደ ድህነት መቀመቅ ለከተቱት ግፈኛ መሪዎች አፋሽ፤ አጎንባሽ ሆኖ የመኖሩንዐብይ ጉዳይ ነው፡፡
የቀለም ትምህርት የተማረው የሕብረተሰብ ክፍል ይኸን የተዛባ አገዛዝ በዐይኑእያየ አንድ የሀገራችን ጎምቱ እንዳሉት የፍርሃት ቆፈን ጨምድዶት በትግሉ ጎዳናላይ ደንቃራ ሆኖ አላሳልፍ በማለቱ የሥልጣን ባለቤት የሆነው ሕዝብ ግፍናበደልን ተሸክሞ እህህ!!! እያለ በሰቀቀን ተሸማቅቆ እንዲኖር ምክንያት ሆኖአል።
በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ ሀገር የሚገኙ የሀገራችን ፖለቲከኞች በርካታ ትኩስመልዕክቶቻቸውን በመፃሕፍት፤ በመፅሔት፤ በጋዜጦችና ስፍር ቁጥር በሌላቸውየኢንተርኔት መስመሮች ያለዕረፍት ያሰራጫሉ። ለመሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብከሠማንያ በመቶ በላይ ማንበብና መፃፍ የማይችል መሆኑን ዘንግተውት ይሆንን?የተማረውስ ቢሆን ከመቶ በእጅ ጣት የሚቆጠረው አይደለም እንዴ፤ አንባቢናየኢንተርኔት ተጠቃሚ? ከዚህ መሀልስ ምን ያህሉ ነው ከፍርሃት ጭምብልተላቅቆ ለትግሉ የበኩሉን አስተዋፅዖ ለማድረግ እራሱን የሚያዘጋጀው? ወይስእንዲያው በደፈናው ማድረግ የምንችለው ይኼንን ብቻ ነው ለማለት ከሆነ ሃቁን ለሕዝብ ሊነግሩ ይገባል፡፡
ዥውን የወያኔ ፓርቲ ጨምሮ፤ ሁሉም ወይም የተወሰኑት ከማራኪ የፖለቲካፕሮግራሞቻቸው በስተጀርባ በየመሪዎቻቸው የህሊና ጉዋዳ ውስጥ መስፈሪያየማይገኝለት ድብቅ የሥልጣን፤ የገንዘብና የዝና ጥማት አለ። ፍላጎታቸውብቻቸውን ገናና ሆነው በአሸናፊነት በመውጣት ተረኛ አምባገነን ሆነው በሌላው ላይ የቋጠሩትን ቂም ለመተግበር እንጂ ዘላቂ ሀገራዊ መፍትሄ ለመፈለግከማንም ጋር መወያየት፤ መግባባት፤ መተባበር ወይም በሌላ መመራትአይፈልጉም፡፡ የዚህ ዓይነት አካሄድ ደግሞ ለአገርና ለሕዝብ የሚጠቅም አይደለም።
በሕዝባችንና በአገራችን ላይ እየደረሰ ያለው የመከራ ግፍ በግልጽ እየታየ ገዥውየወያኔ ፓርቲ ስለመልካም አስተዳደ፤ የኢኮኖሚ እድገት ስለማስመዝገቡናዴሞክራሲያዊ እንደሆነ አድርጐ በየጊዜው ጧት ማታ መናገሩ የተለመደ ከሆነአመታት ማስቆጠሩን ከፍል ሲል ለማውሳት ተሞክሯል። ነገር ግን መንግሥት እንደሚለው ሳይሆን ሕዝብ በአገሩ እንደ ሕዝብ መኖር አለመቻሉ የአደባባይ ምስጢር ነው። በጣም የሚያሳዝነው መንግሥት ከሚሰጠው ፕሮፖጋንዳ ባልተናነሰ መልክ ሁሉም ወይም አብዛኛዎች የሀገራችን የፖለቲካ ፓርቲዎችስለሕግ የበላይነት፤ ስለፍትሕ፤ ስለዴሞክራሲ፤ ስለሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነትናሀገራዊ አንድነት አዘውትረው በጥብቅ ይወተውታሉ፡፡ ሆኖም እውነቱ ሲመረመርፓርቲዎቻቸው ከተመሠረቱ ጀምሮ ቢያንስ ለአንድ ጊዜ እንኳን በመካከላቸውንፁህ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በጭራሽ አድርገው አያውቁም፡፡ ስለዚህ በራሳቸውመካከል ያልተለማመዱትንና ያልተዋሃዳቸውን ዴሞክራሲና ፍትሕ እንዴትአድርገው ነው በሀገር ደረጃ ማስፈን የሚችሉት ብሎ መጠየቅ ተገቢ ይመስለኛል።
ገዥው ፓርቲም ሆነ ተቃዋሚዎች ልብ ሊሉት የሚገባ ነገር አለ። ዛሬ ሕዝባችንበመንግሥት የሥለላ መዋቅር እጅ ቶርች ቢያዝም ሕዝብ በቃኝ ጭቆና ካለበትደረጃ ላይ ደርሷል። ይህ ሁኔታ ባለበት ለጥቂት ጊዜ ካልሆነ በስተቀር በኢትዮጵያ ምድር በዘላቂነት ማንንም ማታለል አይቻልም፡፡ በየትኛውም የትግል ስልትናአቅጣጫ የተሰለፉ ቢሆንም፤ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል ብለው የተደራጁ በርካታየፖለቲካ ፓርቲዎች በውጪና በሀገር ውስጥ መኖራቸው የሚታይ እውነት ነው፡፡በወጣቱ ደም ላይ የኋሊት እየተንሸራተትን በሰው ሕይወት መጫወት እስከመቼ ነው የዚህ አስተሳሰብ ማብቂያው? ይህ ጥያቄ ዘርፈ ብዙ አስተያየትና መልሶችንእንደሚሻ ይገመታል። ነገር ግን ሀቀኛ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ለውጥእንፈልጋለን ወይ? ምን ዓይነት ለውጥስ ነው የምንፈልገው የሚለው በጥብቅሊታሰብበት የሚገባ ዐቢይና ሀገራዊ አጀንዳ ይዘው ሲነሱ ነው፡፡
ነገር ግን ፍርሃትን ያላስወገደ ትግል፤ ለሕዝብ በማይታይና በማይዳሰስ፤ የትምበማያደርስ የትግል ስልት እየፎከርንና እያቅራራን፤ የወያኔንና የአጫፋሪዎቹንዕድሜ ከማራዘም ውጭ ወደፊት ለመገስገስ ብዙ እንቅፋቶች እየተስተዋሉ ነው።ስለሆነም አሁን የተያዘው የተናጥልና የተድበሰበሰ ጉዞ የኋሊት መንሸራተታችንንያባብሰዋል እንጂ በፍፁም አይቀንሰውም፡፡
አገርና ሕዝብን ለመታደግ መጀመሪያ በመሀል ያሉ ውስብስብ ችግሮች ዘላቂእንዳይሆኑ በተገኘው ቀዳዳ ሁሉ በመጠቀም፤ በሕዝቡ መሀል ሆኖ እያደራጁናለትግል እያበቁ ትግሉን ማቀጣጠል ግድ ይላል። ነገር ግን ማንኛውም የፖለቲካሰው ከከባድ መስዋዕትነት በፊት ድልን የሚያስብ ከሆነ ትግሉ እዚያውአብቅቶአል ማለት ይቻላል።
መፍትሄው በሕዝብ የሚደገፍ ሠላማዊ የፖለቲካ ትግል አካሂዶ ለድል ለመብቃት፤ዕልፍ አዕላፎች ሊታሠሩ፤ ሊሞቱ፤ ሊገረፉ፤ ከኑሮና ከሥራ ሊፈናቀሉ የግድ ነው፡፡ ምክንያቱም ያለመስዋዕትነት ድል የለምና !!!!!! አገራችንና ለሕዝባችንለመታደግ ዛሬም እንደትላንቱ ፖለቲከኞች ወጣቱን ፊት ለፊት ማጋፈጥ ሳይሆንከኋላቸው በማሰለፍ ወጣቱ ትውልድ በቀላሉ የማይናወጥ ልምድ እንዲቀስምየማድረግ ኃላፊነት እንዳለባቸው የሚያጠያይቅና የሚያነጋግር ጉዳይ አይደለም፤በዚህ መንገድ ከተጓዝን ከሚፈለገው ግብ መድረስ ይቻላል።
ከድል ማግስት ጀምሮ ለይስሙላ በመንግሥት የተሰሩ ትናንሽና ትላልቅ ኩሽኔትየተገጠመላቸውን የአረጁ የኋሊት መንሸራተቻ መንኮራኩሮቻችንን ሁላችንምሰባብረን አዲስና እጅግ ፈጣን በሆነ በሕዝባዊ አመፅ የትግል ስልት እጅ ለእጅተያይዘን ከኋሊት ጉዞ ብንላቀቅ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ በርካታኢትዮጵያውያን የተሰውለትን፤ በሕይወት የተረፍነውም የምንናፍቀው ሕዝባዊመንግሥት ተቋቁሞ የሕግ የበላይነት የተከበረባት፤ ዜጎች ሳይሸማቀቁ በወደዱትሥፍራና የሥራ መስክ ተሰማርተው በነፃነት እየተዘዋወሩ የሚኖሩባትን አዲስ ሀገር በእርግጠኝነት መገንባት እንችላለን፡፡
ከተክሉ ተሾመ
No comments:
Post a Comment