Monday, July 22, 2013

ለምን በአማራነት መደራጀት አስፈለገን?

እንደሚታወቀው የአማራው ነገድ በኢትዮጵያ ታሪክ ዉስጥ ደሙንና አጥንቱን ሲገቢር የኖረና እኛም ሁሌም የምንኮራበት ኣኩሪ ታሪካችን ሆኖ ዘረኛው ወያኔ የሚስጠው የተዛባ ስያሜ መቸም ሊያዳፍነው የማይችል ሊያኮራን የሚገባ የሁልጊዜም የጥንካሬያችን እና የህዝብ ኣለኝታነታችን አርማ ሆኖ ከትውልድ ትውልድ ይቀጥላል። የአማራው ወጣት ሁሌም የኢትዮጵያን ህዝቦች እድገት ብልጽግና፣ ነጻነት፣ እና አንድነት ለማስከበር በጣልያን ወረራ፣ኣንድ በ፩፱፷ የተማሪዎች አንቅስቃሴ ጀምሮ የደርግን አምባገነናዊ ስርዓት በመቃዎም የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን በመጀመርና በመታገል ዛሬ ወያኔ ከፈልኩት እያለ በየቀኑ ሲደነፋበት ከሚውለው ዋጋ በብዙ እጥፍ ህይዎቱን የገበረ ነገድ መሆኑን ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሊያስታዉስው የሚገባ ሃቅ ነው። በተማሪዎች እንቅስቃሴ እና ተከትሎ በመጣው የስርዓት ለውጥ የመጀመሪያ ሰለባ የሆኑት የኛ ወንድሞች እና አባቶች ነበሩ፤ቀጥሎም የደርግን አገዛዝ በመቃዎም ከማንም በላይ የተዋደቁና የቀይ ሽብር ሰለባ የሆኑት ወያነዎች ሳይሆኑ የኣማራው ወጣቶች ነበሩ።
ዛሬም በግፍ የምንገደለው፣የምንታሰረው፣የምንሰደደው፣ ይህም አልበካ ብሎ በራሳችን ሚድያ ሳይቀር ሃገራችን አንድ ኢትዮጵያ ናት ስላልን ብቻ ነፍጠኞች፣የደርግ እርዝራዦች፣ የድሮ ስርዓት ናፋቂዎች፣ እና ወራሪዎች እየተባልን በተገኘው ኣጋጣሚ በሙሉ ለሰነልቦና እና አካላዊ ትንኮሳ ሰለባ የሆነው እኛ የኣማራው ወጣቶች መሆናችን ማንም ማየት እና መስማት የሚችል ሰው ሊገነዘበው የሚችል አውነታ ነው።

ይህ ሁሉ ግፍ እና መከራ እየደረሰብን ባለበት በአሁኑ ሰዐት እንኩአ ( አማራው ወጣቶች) አባቶቻችን እና ወንድሞቻችን ስንት መስዋትነት የከፈሉበትን ኢትዮጵያዊነት እንደ ቲሸርት አውልቀን የምንጥል ሳንሆን እንደቀደሙት አባቶቻችን እና ወንድሞቻችን ደማችንን የምንለግስለት የምንጊዘም የማንነት መገለጫችንና የኩራታችን ምንጭ መሆኑን ለወያኔና አማራውን ወጣት መደራጀት ለማይፈልግ ማንኛውም አካል አስረግጠን ማሳወቅ አንፈልጋለን።ለኢትዮጵያዊነት ከሁሉም በላይ ደም ከፍለናል፤ ኣሁንም እየከፈልን ነው፤ ፤እንዳስፈላጊነቱ ወደፊትም እንከፍላለን። የወያኔ አላማ (የሙኣቹም ሆነ የቀሩት መሪዎቹ ራዕይ) ይህን ኢትዮጵያዊነት ኩራቱና ክብሩ የሆነን ወጣት ኢትዮጵያን ታሪክ ዐመት ታሪክ ብቻ በማድረግ፣ የኢትዮጵያን ታሪክ ከጭቆና ታሪክ ጋር ብቻ በማያያዝ፣ በኢትዮጵያ

ውስጥ ያለውንና የነበረውን ችግር ምክንያት ወደ አማራው ህዝብ በማላከክና፣ የኣማራውን ህዝብ ባህል አና ወግ በማንቁአሸሽ ስነልቦናውን ጎድቶ በክብር ሲሞትለት ከነበረውና ዛሬም ከሚሞትለት ኢትዮጵያዊነት መነጣጠል ነው። ቢሆንም ግን ጠንካራው የኣማራ ወጣት በዚህ ፪፪ ዐመታት ዉስጥ በቴለቭዥን፣ በሬድዮ፣ በጋዜጣና በመጽሃፍት ሲደረግበት የነበረውን ኢትዮጵያዊነቱን የመንጠቅ ራዕይ(ዠመችሃ) ተቁአቁሞ ዛሬም ከኢትዮጵያዊነቱ ዝንፍ ያላለላቸው ወያኔዎች ፪፪ አመታት ሲጨፈጭፉትና ሲያስጨፈጭፉት የነበረውን ወገናችን በየገባበት በመግባት ደሙን በከፈለባት እናት ሃገሩ በግፍ ነብረቱን በመቀማት፣ በዱላ በመደብደብ፣ ዘሩን በማንቁአሸሽና በመስደብ ያለምንም ርህራሄ ከነልጆቹ እንዲፈናቀል በማድረግ ኢትዮጵያዊነቱን እንዲጠራጠርና እንዲጠላ የማድረግ ስራቸውን ከማንኛውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ እየተገበሩ ይገኛል። እስካሁን ይህ ግፍና ጭቆና የሆነ ጊዜ ላይ ይቆማል በሚል አማራው ወጣት ፪፪ አመታት እራሱን እንደሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች በዘር አና በቁኣንቁኣ ከማደራጀት ይልቅ በተለያዩ ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች በመሳተፍ የሚደርስበትን ስቃይ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ሲታገል ቆይቱኣል።ይሁን እንጅ እስካሁን የተደረገው ትግልና እንቅስቃሴ፣ የአማራውን ስቃይ መቀነስ ይቅርና እራሱ እንኩኣ እንደ ድርጅት መንቀሳቀስ የማይችልበት ደረጃ እየደረሰ መሆኑን በሃገር ዉስጥና ዉጭ ያለውን የተቃዉሞ እንቅስቃሴ ማየት ብቻ በቂ ነው።ይህንም ወቅታዊ ችግር በመረዳት የአማራው ወጣት በራሱ አና በወገኑ ላይ እየደረሰ ያለውን አስከፊ ግፍና ጭቆና ለማስቆም ያዋጣኛል በሚለው መንገድ መደራጀት የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን ወቅታዊ ግዳጁ መሆኑን ተረድቶ በመደራጀት ላይ ይገኛል።ይሁንና ኣማራው ነገድ አለፉት ሁለት አስርት አመታት በደርሰበት የመገለልና የስነ ልቦና ጫና የተጠያቂነት ስሜት ኣዳብሮ ተቀባዪነት አላገኝም በማለት በተቃዉሞው እንቅስቃሴ ዉስጥ የመሪነትን ሳይሆን የተከታይነትን ባህል ሲያራምድ ቆይቱኣል። ይህም በመሆኑ አማራው ነገድ ባለበት የስነ ልቦና ደረጃ በኢትዮጵያዊነት ተደራጅቶ ወያኔን ለማስወገድ የሚያስችለው አቅም መኖሩ አጠራጣሪ ስለሆነ ለጊዘውም ቢሆን ዝቅ ተብሎ ማንነቱን፣ ባህሉንና ወጉን የማስታአስ አና የማዳበር ስራ መሰራት እንዳለበት ድምዳሜ ላይ ደርሰናል። ስለሆነም ሞረሽ አማራ ወጣቶች ንቅናቄ በቀዳሚነት ከሚሰራቸው ስራዎች መካከል አማራውን ነገድ ባህሉን ወጉንና ጀግንነቱን እንደገና በመገንባት እንደ አንድ ቤተሰብ ተደራጅቶ ፍላጎቱንና ጥያቄውንን ያለምንም ዪሉኝታና ፍርሃት ከሌሎች ኢትዮጵያን ዎንድሞቹ ጋር በነጻነት፣በእኩልነት እና በመከባበር እንዲያስተጋባ ከለላ በመመስረት በኢትዮጵያ ዉስጥ እና ዉጭ ያሉ አማራውን ነገድ እንቅስቃሴዎች አንድ ላይ በማምጣት እንዳለፈው ታሪኩ በሃገሩ ጉዳይ ግንባር ቀደም ተሳታፊ ማድረግ ነው። ይህንንም ለማድረግ በምናደርገው እንቅስቃሴ የናንተ አማራው ልጆች ምክር፣ ድጋፍ አና ተሳትፎ አጅግ ዎሳኝ በመሆኑ እጅ ለእጅ ተያዪዘን ወገናችንን እየደረሰበት ካለው ሰቆቃና ዉርደት እንድንታደገው በሞርሽ አማራ ዎጣቶች ንቅናቄ ስም አክብሮት እጠይቃለሁ። አምላክ ሃገራችንና ህዝባችን ከማንኛውም ጥፋት ይታደግ። ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።አሜን።

ሞርሽ የአማራው ወጣቶች ንቅናቄ

No comments:

Post a Comment