***ለወገኖቻችንን ጥሪ ምላሽ የምንሰጥበት ግዜ***ሐይማኖት እና ፆታ አይጠይቅም!!!
***አምባገነን መብትህን ካልጠየከውና ከእጁ ካልነጠከው በፍፁም አይሰጥህም***
ከውሸት መራቅ፣ከሀሜት መራቅ፣ነገር ከማዛመት መቆጠብ ፣በውሸት ከመመስከር መቆጠብ፣ሰዎች ከማታለል መቆጠብ፣ለእውነት መቆም
ዋና ዋና መሰረታዊ ጥያቄዎችን ለማንሳት መዘጋጀት፡፡ በአሸባሪነት ተፈርጀው የታሰሩ ለማስፈታት መታገል!
መሪ ቃል ሊሆን የሚገባ ጥያቄ!!!!!!!
በጣም አንገብጋቢና የወቅቱ የህዝብ ብሶት የሆኑ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ መታገል፡፡ አንደኛ ሙያዊ ግዴታቸውን ስለተወጡና የመንግሥትን ፖሊሲ ስለተቹ ብቻ በአሸባሪነት ተፈርጀው የታሰሩ እንደ እስክንድር፣ ውብሸት፣ ርእዮትና ሌሎች ጋዜጠኞች አሉ፡፡ እነዚህ ጋዜጠኞች ያደረጉት ምንም ወንጀል የለም ብሎ ህዝብ ያምናል፡፡ ህዝብ ብቻ ሳንሆን በዚህ ጉዳይ ላይ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶችም ተመሳሳይ አቋም ነው ያላቸው ሰዎቹ የህሊና እስረኞች ናቸው ብለው ያምናሉ፡፡ ስለዚህ ግለሰቦቹ በሽብርተኝነት መታሰራቸው አግባብነት ስለሌለው እንዲፈቱ ጥያቄ ማቅረብ።

የፖለቲካ ሰዎች እስርም ቢሆን እንደ በቀለ ገርባ፣ ኦልባና ሌሊሳ እና እንደነ አንዷለም አራጌ የመሳሰሉ ፖለቲከኞች በሀገሪቱ በህግ ሰላማዊ የትግል መስመር እንደሚከተሉ የተረጋገጠላቸው የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ናቸው፡፡ እናም ሃሳባቸውን በነፃ በመግለፃቸው፣ ህዝብን በማደራጀታቸው እና ፖለቲከኛ ሊወጣ የሚገባውን ተግባር ስለተወጡ ወይም ከመንግሥት የተለየ ሀሳብ ስላራመዱ ነው የታሰሩት ስለሆነም እነሱም እንዲለቁ ጥያቄ ማቅረብ።
መንግሥት ህገ-መንግሥታዊ የዜጎች መብትን በመጣስ በሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ ገብቶ ሙስሊሙን ማህበረሰብ የማይፈልጉትን አስተምህሮት እንዲቀበሉና አመራሮችም በኛ ሳይሆን በሱ ፈቃድ እንድንመርጥ ተገደናል ሲሉ ለሁለት ዓመት ሙስሊሞች ጠይቀዋል፡፡ ጉዳዩ መጀመሪያ ላይ ሲነሳ ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ተወካዮች ተመርጠው መንግሥት ራሱ እውቅና ሰቶ ለሰባት ወራት ሲደራደሩ እንደነበር ይታወቃል፡ ፡ ሆኖም ግን በኋላ ላይ ራሱ መንግሥት እነኚህኑ ሰዎች መልሶ አሸባሪ ናቸው ብሎ ዘብጥያ ወርውሯቸዋል፡፡ ይህ ትክክል አይደለም መብትን መጠየቅ አሸባሪነት አይደለም፡፡ የሃይማኖት ነፃንት በህገመንግሥት ዋስትና ያገኘ መብት ነው መንግሥት እዛ ውስጥ ገብቶ መፈትፈት የለበትም፡ ፡ እኛ እነዚህ ሰዎች እንደተባለው አሸባሪዎች ናቸው ብለን አናምንም በዚህ ምክንያት እንዲፈቱ ጥያቄ ማቅረብ።
እነዚህን ሁሉ ድምር ጥያቄዎች ይዘን ነው እንግዲህ ዝም ያነው፡፡ ላለፉት 22 አመታት ህዝቡ በፍርሀት ተሸብቦ ነው የኖረው፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ የዜጎች መሰረታዊ መብት ቢሆንም ይህን ሳይጠቀምበት ቆይቷል፡፡ ይህን በተለይ በአዋጅ እንደተደነገገው ሰዎች ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አላማቸውን፣ ቀኑንና ቦታውን ጠቅሰው ሰልፍ ለማድረግ እስከጠየቁ ድረስ በ48 ሰዓት ይፈቀዳል ነው የሚለው፡፡ የፀጥታ ስጋት ወይ ቀድሞ ቦታው ለሌላ ፕሮግራም ከተያዘና በመሳሰሉት ሁኔታዎች ካልሆነ በቀር ይህን የመፍቀድ ግዴታ አለበት፡፡
ይህ ህግ በሀገሪቱ ቢኖርም ህዝባችን ይህን መብት ሳይጠቀም ነው የቆየው፡፡ በተለይ ከ1997 በኋላ በጊዜው ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስቴር ፓርቲያቸው መደናበር ውስጥ ሲገባ ህጉ ያልሰጣቸውን ስልጣን ተጠቅመው ከዛሬ ጀምሮ ሰልፍ የሚባል በጥብቅ ተከልክሏል ሲሉ ያወጁበት ህገወጥ እርምጃን ተከትሎ ህዝብ በፍፁም ፍርሀት ስር ወድቋል፡ ፡ ያ የጠቅላይ ሚኒሰትሩ አዋጅ እስከዛሬ ህግ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ተቃዋሚዎችም ይህን መብት እስከመጨረሻው ሄደው አይጠይቁም ነበር፡ ፡
***አምባገነን መብትህን ካልጠየከውና ከእጁ ካልነጠከው በፍፁም አይሰጥህም፡፡***
የትግሉ ጥያቄ እውን የሚሆንበት አሁንና አሁን ብቻ ነው።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
ከሰብኣዊ
No comments:
Post a Comment