ፍትሕ ከሌለህ ሰላም ሊኖርህ አይችልም፡፡ አንተም ተው አንቺም ተይ ተብሎ ወንጀል ሊቀር አይችልም፡፡ ቅጣቱ እኮ ሊዘለልም ይችላል፡፡ ማኅበረሰቡም ይቅርታ ሊያደርግለት ይችላል፡፡ ዋናው ቅጣቱ ሳይሆን ተጠያቂነቱ ነው፡፡ በአካባቢው እርቅና ሰላም እንዲወርድ ከተፈለገ ቅጣቱን መዝለል ወይም በይቅርታ ማለፍ ይቻላል፡፡ ተጠያቂነትን ግን በምንም ዓይነት መንገድ መዝለል አይገባም፡፡ አንዳንድ ሰዎች ለአፍሪካ የተለየ ዓይነት ፍትሕ አስፈላጊ እንደሆነ አድርገው ያቀርባሉ፡፡ አፍሪካ ከአውሮፓና ከአሜሪካ የተለየ እሴት እንዳለውም ይከራከራሉ፡፡ የፍትሕ አሰጣጡ ሒደት ከአፍሪካ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ሊስተካከል ይገባል በማለት ያስረዳሉ፡፡ አውሮፓም፣ አሜሪካም ሆነ አፍሪካም ያለው ሰው ነው፡፡ የሰው ልጅ ፍትሕ ይፈልጋል፡፡ ፍትሕ ደግሞ ሁሌም አንድ ዓይነት ነው፡፡ ፍትሕ ሁሉን አቀፍ የሆነ መብት ነው፡፡ አፍሪካ የተለየ ፍትሕ የለውም፡፡ የሰው ልጅ ፍላጎት ተመሳሳይ ነው፡፡
ከሰብኣዊ
ከሰብኣዊ
No comments:
Post a Comment