Saturday, July 13, 2013

የኢትዮጲያኖች ህይወት በአረብ አገር

ሴት ለሴት ወንድ ለወንድ የሚደረግ ጋብቻ በሰለጠነው ማህበረሰብ እንደህጋዊ በሚቆጠርበት ዘመን ላይ ደርሰናል ደጉ ዘመን
  • በተለያዩ የማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ እንዳነበብኩት ባገራችንም ስር እየሰደደና ያለው ሁኔታ አስከፊ መሆኑን ሳነበብ ነገሩ ወዴት ወዴት እየሄደ ነው በሚል ግርምት ድንጋጤ ውስጥ እገባለው ዛሬ እንኳን ከዚህ በበለጠ ሁኔታ ያስደነገጠኛና ያሳሳበኝን ነገር ልንገራቹ።
    ልጅቷ የምትሰራው ሰው ቤት ነው።ከዚህ በፌት አሰሪዋ ሲያስቸግራት ስለነብር ቤት ቀይራ አሁን ያለችበት ቤት ከመጣች 8ኛ ወሯ ነው እንደነገረችኝ ከሆነ ቤቱ በጣም ተስማምቷትና ስራም እንደማይበዛበት ከበፊቱን የተሻለ እንደሆነ አጫውታኝ ነበር ከዚህ በፊት የዛሪው የስልክ ጥሪ ግን ንግግሯ ሁሉ ተለወጠብኝ እንደማልቀስም እንደማዘንም ያደላል ምን ሆነሻል???
    ከዛሬ 5 እና 6 ቀን የትልቋ ልጅ ሁኔታ ግራ አጋባኝ በምሄድበት ትሄዳለች በምቆምበት ትቆማለች እንቅስቃሴዋን እንደዛሪው በገሃድ ገፍታ ባታሳየኝም ይህ ሁኔታዋ ግን እኔን በመፈለግ ነው ብዬ አልተጠራጠርኩም ዛሬ ግን ሁለንተነዋ ግልጽ ሆነልኝ 
    ወቅቱ የጾም ስለሆነ አርፍጄ ነው የምነሳው የመኝታዬ በር በቀስታ ሲከፈት ሰማሁና ልጅቷ መሆኗን ሳይ የምትፈልገው አለ በማለት ጠይቄታ ተመልሼ መተኛት ስለፈለኩ ምን ፈልገሽ ነው ከማለቴ በሩ ዘጋችውና አጠገቤ መታ ተኛች ምን ልትነግረኝ ነው ብዬ ልቤ ፈራ ከዛም ከንፈሯን ከከንፈሬ እጆቿን ወደ ጡቴ በመላክ ልክ ሴትና ወንድ እንደሚያደርጉት እንቅስቃሴ ልትፈጽምኝ ስትል ካልጋዬ እንዴት እንደወረድኩ አላውቀውም ልታባብለኝ ሞከረች ድምጼን ከፍ አድርጌ ልጮህ ብሞክር በጇ ግጥም አድርጋ በመያዝ ማማ ብትሰማ እገልሻለው በማለት ተመናቅራ ወጣች 
    ከዛ በኋላ ያለውን ጊዜ እንዴት እንዳሳለፍኩት አላውቀውም ሰዎቹ ጾመኛ ስለሆኑ በመደናበር የሚበሉት ሰርቼ ከቀልቤም ሳልሆን ዋልኩ አሁን ሴትየዋ ልጆቿን ይዛ ወታለች እናም በዚህ አጋጣሚ ደወልኩ ምን ላድርግ ብላ ያለችበትን ሁኔታ አሁን በምጽፍበት ወቅት አማከረችኝ።

    ይህን መልህክት ስሟን በመደበቅ ወደናተ አመጣሁት ገንቢ አስተያየት ካላችሁ ለግሷት

No comments:

Post a Comment