Friday, July 12, 2013

***ነፃ-ፕሬስ የሌለው መንግስት ኩራዝ በሌለው ጨለማ ቤት ውስጥ የሚኖር ግለሰብ እንደማለት ነው፡፡***

የተሳካ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት የነፃ ፕሬስ አስፈላጊነት ትልቅ ቦታ እንዳለው ከልብ አምናለሁ፡፡ ያለነፃ ፕሬስ ዴሞክራሲ አለ ብሎ መናገር ማወናበድ እንጅ እውነት ሊሆንም አይችልም፡፡
የነፃ ፕሬስ መኖር በራሱ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት መኖር መገለጫ ነውና፡፡ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ሲኖርም ነፃ ፕሬስ ይኖራል፡፡ ወደ እኛ ሃገር ስንመለስ ግን ነገሮች ሁሉ የተገላቢጦሽ ሆነው
እናገኛቸዋለን፡፡ ወያኔ/ህውሃት መንግስት ሆኖ ለባለፉት 22 ዓመታት ሃገሪቱን ሲያስተዳድር ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን በወረቀትና በቃል እንጂ ከዚያ በዘለለ ተግባር ሲፈፅም አላሳየንም፡፡ ለመተግበር የሞከራቸውንም እንደቀንዳ ውጣ ቀንድ መልሶ ሸሽጎታል፡፡ ስለዚህ በዴሞክራሲያዊ ስርዓት የማያምን ገዢ ፓርቲ ስለሆነ ለነፃው ፕሬስ ተገቢውን ጥበቃና እንክብካቤ በመስጠት ፈንታ አጥፊና ደምጣጭ ሆኖ እየሰራ ነው፡፡ 
በኢትዮጵያ ሃሳብን በነፃነት መግለፅ ህገ-መንግስታዊ ከለላ ቢሰጠውም፤ ሳንሱር መነሳቱ በህግ ቢደነገግም፣ በገቢር ግን ሃሳብን በነፃነት መግለፅ የሚያሳስር፣ የሚያሰድድና የመንግስት ጠላት
የሚያሰኝ ሆኗል፡፡


ፕሬስ ፍፁም ነፃነት የሚያስፈልገውና መንግስት ጣልቃ የማይገባበት ህዝብን የሚያገለግል የማህበረሰብ ተቋም ነው፡፡ እንደዚህ የምለው ነፃ-ፕሬስ የሚሰጠውን ዘርፈ ብዙ ጥቅም ከግምት በማስገባት ነው፡፡ ነፃ-ፕሬስ የሌለው መንግስት ኩራዝ በሌለው ጨለማ ቤት ውስጥ የሚኖር ግለሰብ እንደማለት ነው፡፡ ነፃ-ፕሬስ የሌለው ህዝብ በሃገሩ ላይ ምን እየተካሄደ እንደሆነ እንዳያውቅ የተፈረደበት ህዝብ ነው፡፡ ነፃ-ፕሬስ ለነፃነት፣ ለፍትሕና ለእኩልነት የሚያደርገውን አስተዋፅኦ የሚገነዘቡ ገዥዎች ፕሬሱ
ለአምባገነንነት አገዛዛቸው የሚመች ስለማይሆን ይፈሩታል፤ይጠሉታል፤ ያጠፉታል፡፡ ወያኔ/ህውሃት እያደረገ ያለው ይሄንኑ ነው፡፡ነፃው ፕሬስ ለህዝቡ የፖለቲካ ንቃተ ህሊና መዳበር የሚያደርገውን
አስተዋጽኦ፣ ህዝቡ ባሪያ ከሚያደርግ አስተሳሰብ እንዲላቀቅ፤ከአምባገነኖች የሚደርስበትን ጫና አልቀበልም እንዲልና የኑሮው ሁኔታ እንዲሻሻል የሚያደርገውን አስተዋጽኦ እንደ ወያኔ/ህውሃ አይነቱ ዴሞክራሲያዊ ያልሆነ መንግስት አይፈልገውም፡፡ ስለዚህ የማጥፋት ዘመቻ ያካሂዱበታል፡

ገዢ ፓርቲ የሆነው ኢህአዴግ 9 ሚሊዬን ህዝብ የሚመጥን ነፃ ፕሬስ እንዲኖር ባለማድረጉ አገዛዙ ያልተሳካለት እንደሆነ አመላካች ነው፡፡ፕሬስ ለዴሞክራሲ ዘብ ይቆማልየሚለው የሰለጠነ አባባልም
የሚገባው አይደለም፡፡ ለፕሬሱ ዘብ መቆሙ ቀርቶ ማጥፋቱን በተወ።
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment