ለአባይ ግድብ ሲባል የመንግስት ድርጅቶች ሁሉ ለጨረታ ሊቀርቡ ነው? ገዢዎች ግን እንደሌሉም በጥናት ተረጋግጧል::ወያኔ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መግባቱን እየሰማን ነው እገድባለሁ ብሎ የጀመረው ግድብ በኢትዮጵያውያን ኩርፊያ እንዳይስተጓጎል በጣም ሰግቷል:: የሚያደርገው ቢያጣ ገዚ ያጡትን የመንግስት ድርጅቶች የሚደልለውን የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ የሚያመጣውን ገቢ ለግድቡ እንዲውል ከጭንቀት በመነጨ ወስኗል:: ይህ ደላላዊ ኤጀንሲ ደሞ መሸጥ የሚፈልገውን ሁሉ የሚገዛው አጥቶ አፉን ከፍቶ እንደዋለ ነው:: ከዚህ በፊት ያቀረበውን ጨረታ 65% ማንም ገዢ አጥቶ እንደተኮላሸ ይታወቃል::
የነፃ ኢኮኖሚ ሥርዓት ግንባታ እውን በማድረግ ስም በሟቹ መለስ ዜናዊ በሳምንት ሁለት ጊዜ መመሪያ እየተሰጠው የነበረ እና ለሙስና ታላቁን ሚና የሚጫወተው ይሀው ድርጅት ለአባይ ግድብ የሚሆን ትርፍራፊ ገንዘብ ሸጦ እና ለውጦ ያመጣል ማለት ዘበት ነው :: ለፖለቲካ እና ለሚዲያ ግብኣት ፍጆታ ቃላቶችን ለማዋል ወያኔ ተጠቀመበት እንጂ ውጤት የለውም::
ሃይለማርያም ደሳለኝ የሚባሉት ሰውዬ በምክር ቤት ከዚህ ቀደም ግድቡ በገንዘብ እጥረት ይቆማል ተብለው ሲጠየቁ አይቆምም በቂ ገንዘብ አለ ብለው በዋሹበት አንደበት ግድቡን ስራው እየተስተጓጎለ ስለሆነ ብለው የመንግስት ድርጅቶች እየተሸጡ ገንዘቡ ለግድቡ ፈሰስ እንዲደረግ አዘዋል::ድርጅቶቹ ገዢ የላቸውም እንጂ::
የግድቡን ወጪ በህዝብ ትከሻ ላይ የጣለው ወያኔ የህዝቡ ማጉረምረምን እና የኑሮ ውድነትን ተከትሎ እንዲሁም የሰብኣዊ መብቶች መደፍረስን አካቶ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል::የወያኔ አጣብቂኝ ሊወጣው በሚችልበት ነገር ሁሉ ቢሞክርም አልተቻለውን :: አባይን ለመገደብ ወያኔ ከማናለብኝነት እና ከእልህ ወጥቶ ከህዝብ ጋር መታረቅ አለበት::የማይመስል ስሌት እያቀረቡ ህዝብን ማደናገር አያዛልቅም::
በኢትዮጵያ ያለውን የሰብኣዊ መብት ጥሰት የህዝቦች በሰላም እና በነጻነት የመኖር መብት መገፈፍ አፈና ግድያ ማፍያዊ ድርጊቶች መንግስታዊ ሽብርተኝነት ማናለብኝነት እና እብሪት እስካልተወገዱ ድረስ ወያኔ አፉን የሚከፍትለን ግድብ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ይቆማል::
በየእስር ቤቱ ከላምንም ማስረጃ እና ፍትህ በየፍርድ ቤቱ እየተመላለስኡ የሚገኙት የፖለቲካ እስረኞሽ የሃይማኖት መሪዎች ጋዜጠኛኦ እስካልተፈቱ ድረስ በሃገር በት እና በውጪው አለም ያለው ኢትዮጵያዊ በሃገሩ ጉዳይ እንዴት ይሳተፍ:: ወያኔ ማነቆዎችን ማንሳት አለበት::

No comments:
Post a Comment