Wednesday, July 3, 2013

*** ሕዝብ አመኔታ ያልሰጠው መንግስት በምንም መመዘኛ ታማኝ ሊሆን አይቻልም።


*** በዜጎች ድምፅና ፈቃድ ሳይሆን በጦር መሳሪያና በማጭበርበር ስልጣኑ እንደተቆጣጠረ ስለሚያውቀው እንደ መንግስትለሚያስተዳድረው ሕዝብ እምነትና ፈቃድ አይጨነቅም በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ እና በማሕበራዊ ዘርፍ የሚከተላቸው ፖሊሲዎችየሚያፀድቃቸው አዋጅና ህጎች የሚያወጣቸው ደንቦችና መመሪያዎች የሚሰይማቸው አስፈጻሚ አካላትበህዝብ ፈቃድ ላይ የተመረኮዘና ለህዝብ ዘለቄታ ጥቅም እንዲአበረክቱ የሚታሰብላቸው አይደሉም።
አምባገነኖች ከስልጣን ወንበራቸው ውጭ አርቀው መመልከትም ሆነ ማየትም አይሹም አንድም ከስህተቶቻቸው ሁለትም ከቀደም ቢጤዎቻቸው ውድቀትና ውርደት በመማር እራሳቸው ለመለወጥ ከህዝባቸውና ከፖለቲካ ተጠቃሚዎቻቸው ጋር እርቅ ለመፍጠር ቅንነትና ፍላጎት የላቸውም::
የዛሬውን እንዴት እንደተቆናጠጡት ስለሚያውቁት ነገ የእነሱ ስለመሆኑ እርግጠኛ አይደሉም ወደዱም ጠሉም ትተውት በሚያልፉት ስርዓት ዉስጥ የፈጸሟቸው እኩይ ተግባራት ሊያስከትሉ የሚችሏቸው አገራዊ ቀውሶች በግልም ሆነ በጋራ ተጠያቂነት ሊያስከትሉ እንደሚችሉ ግን አያጡትም። ዋጋም መክፈላቸው የት ይቀርና !!

ነገ በታሰባቸው መጠን ዘወትር ዉስጣቸው ይረበሻል። የዛሬው ማን አለብኝነት ሕገ ወጥነትና የበላይነት ከነገው ተጠያቂነት ውርደትና ቅሌት አንፃር በፍርርቅ እየታየ ሠላም ይነሳቸዋል፣ ይረብሻቸዋል፣ ያሻብራቸዋል በመሆኑም ዘወትር ሕዝቡን ሰላም ይነሳሉ ያሸብራሉ በየጊዜው እየበረገጉ እንደሚኖሩ ሁሉ ሕዝብን በፍርሃት ለማስበርገግ እንቅልፍ ያጣሉ::
ይህ የአምባገነኖች የጋራ ባህሪ ነው ነገ የነሱ እንዳልሆነ ተስፋ በቆረጡ መጠን ለነገ ብሩህ ተስፋ የሰነቀ ሁሉ ሰላም የሚያሳጣቸው የሚረብሻቸው ፀረ ሰላም አሸባሪ ጠላት የሆነ ኃይል ነው መስሎ የሚታያቸው። በመንግስት ላይ የሚንፀባረቀው የተስፋ መቁረጥ ባህርይ ከኢትዮጵያ
አልፎ ጎረቤት ሐገሮችን ተሸብረው እንዲያሸብሩ ምክንያት መሆኑን ለመገንዘብ አያዳግትም። አይቀሬው ውድቀትና ውርደት የሚያባንነው አገዛዝን ሕዝብን በፍርሃት እያሽማቀቀ ቀን ከመግፋት ባሻገር አርቆ ማየት አልቻለም ስለ ውድቀታቸውና በምትኩ ነገ ሊኖር ስለሚገባው የህግ የበላይነት ግልፅነት ተጠያቂነት በስውርም ይሁን በግልጽ የሚያስቡ የሚናገሩ የሚጽፉ ሁሉ የስርአቱ ጠላቶች ናቸው። ስለሆነም የስርዓቱ ጠላት እና ሽብርተኞች ወይንም አሽባሪዎች ተደርገው ሊከሰሱ የሚችሉበት ጭፍን ህግ ተረቅቆና በመለስ አሻንጉሊት ፓርላማ ጸድቆ የስርዓቱ ዘብ በመሆን ያገለግላል።

ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment