Thursday, July 4, 2013

ወደ ራሳችን እንመለስ::

የሰሜን አፍሪካዋን ግብጥ የውስጥ ነውጥ ተከትሎ የተለዩዩ የቃላት ቂሪላዎች ሲለጉ እያየን ነው:: እኔ የምለው የራሳችንን ጉዳይ በወጉ ያልደፈንን በተገኘበት የምንዋትት ሃሳባችን እየተሰረቀ የምንዘናጋ ሰዎች ስለግብጥ ነውጥ ለመናገር ሞራላችን ምን ያህል እንደሆነ አይገባኝም ::እስኪ የራሳችንን ከወያኔ ጋር የገጠምነውን እንካሰላምታያ በድል ለመወጣት እንሩጥ::
ሌላው ከግብጥ ህዝብ የምንማረው ምናምን እየተባለ የሚዘባረቀው ነገር ምንም የምንማረው ነገር የለም :: ግብጦች የሙባረክን መንግስት ለመጣል ያደረጉትን አብዮት ህዝባዊ መንግስት ይመስረትልን ብለው ያሰሙትን ድምጽ አይተናል ሰምታናል ኬነዚህ እንቅስቃሴዎች ያልተማረ ህዝብ ዛሬ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ ስልጣን ይዞ ህገመንግስታዊ ስልጣኑን የጠቀለለው እና አሜሪካ እና እስራኤል የሰጉበት ህዝቡም አጉረምርሞ አደባባይ የፈሰሰበት ሙርሲ ምን ያስተምረናል ማለት የዋህነት ነው::

የወደቀ ዛፍ ምሳር እንደሚበዛበት ኢትዮጵያውያን ያልገባን የግብጻውያኑ ጥያቄ እና የሙርሲ አተካሮ ብሎም ውድቀት በሃገሪቱ መንሰራፋት የሚፈልጉ አይሁዶች እና የኮፕቲክ መሪዎች ሴራ መሆኑን ለራሳቸው ትተንላቸው እኛ ሳንዘናጋ ስለራሳችን ጉድ እናስብ :; ወደ ትግላችን እንመለስ:: የራሳችን የትግል ስልት ይኑረን ካለፉት የሙባረክ እና የወታደራዊው ውድቀት አብዮት ያልተማርን ሰዎች ከዚህ የምንማረው ነገር የለም:: ወደ ራሳችን እንመለስ ሁሌ የሰው እንዳወራን አንኑር የወያኔ መንጋት አንድ ህግ ሲያረቅ ከዚህ አገር ያመጣሁት ነው ይለናል ተቃዋሚ ነን ባዮችን የአንድ ሃገር አብዮት ስናይ ከዚህ መማር እንላለን ..ሁሌ የሰው አንይ :: ካልሆነ ትግሉም ይከስማል:: ድሉም የወያኔ ይሆናል:: ስለዚህ ከትግላችን አንዘናጋ ተመለሱ::

ከሚሊኒክ ሳልሳዊ

No comments:

Post a Comment