አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የስራ ሀላፊዎችን መርቁልኝ በማለት ለፓርላማው አቅርበዋል፡፡መመረቅ ልማዱ የሆነበት ፓርላማም ሹመትና ሽረት ያዳብር ያለ መሰለኝ፡፡ግን ትምህርት ሚኒስትር አሳዘነኝ፡፡በየሹመት ሴርሞኒው ወጪና ወራጅ አያጣውም፡፡አሁን አቶ ደመቀ መኮንን ቁጭ ከማለታቸው እንዲነሱ ተደርገዋል፡፡ሽፈራው ከደቡብ እንዲመጡ የተደረጉትም ምናልባት ከሃይሌ ጋር በቅርበት ስለሚተዋወቁ ይሆናል፡፡ሽፈራው ለቦታው የሚመጥኑ ሰው ስለመሆናቸው ግን መጨነቅ አይኖርብንም ነፍሳቸውን ይማርና መሌ አንድ ወቅት‹‹የእኛ ይሁን እንጂ ሌላው አያስጨንቀንም››ብለውን አልነበር?፡፡ለማንኛውም የበረከትን ቦታ የኢህአዴግን ጽ/ቤት ይመሩ የነበሩት ካድሬው አቶ ሬድዋን ሁሴን ተረክበውታል፡፡የበረከት ስምኦን ዕጣ ፈንታ ከጠበቅኩት ውጪ ሆኖብኛል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሁለት ምርጫዎችን ወግ ደራሲ እንዲህ ውሽቅ ያደርጓቸዋል የሚል እምነት አልነበረኝም፡፡ ሬድዋንና አቶ ሽመልስ ከማል (ሁለቱም ካድሬዎች ናቸው)አብረው በተለይም ሽመልስ የሬድዋን የበታች ሆነው መስራት ስለ መቻላቸው ጊዜ ከሰጣቸው የምናየው ይሆናል፡፡በ1997 ቀውጢ ሰዓት የፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ቀውጢ ሁኔታ ውስጥ የሚገኘውን የትራንስፖርት ሚኒስትርን ተረክበዋል፡፡ምናልባት የትራንስፖርት ችግራችንን በፖሊሳዊ መመሪያ ስርዓት ያስይዙት ይሆን? ለማንኛውም ሹመኞቹ እነዚህ ናቸው፡፡አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የትምህርት ሚኒስትር
አቶ ሬድዋን ሑሴን የመንግስት ኮሚኒኬሽን
ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር
አቶ አህመድ አብተው የኢንዲስትሪ ሚኒስትር
አቶ ወርቅነህ ገበየሁ የትራንስፖርት ሚኒስትር
ወ/ሮ ሮማን ገብረስላሴ በህዝብ ተወካዮች
ምክርቤት የመንግስት ጉዳዮች ተጠሪ ሚኒስትር
ወ/ሮ ደሚቱ ሃምዴሳ የሳይንስና ቴክኖሎጂ
ሚኒስትር
አቶ ጌታቸው አምባዬ የፍትህ ሚኒስትር
አቶ በክሪ ሻሌ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና
ዳይሬክተር
አቶ በለጠ ታፈረ የአከባቢ ጥበቃና ደን ሚኒስትር
አቶ መኮንን ማንያዘዋል የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን
ኮሚሽነር ሆነው ተሽመዋል፡፡
No comments:
Post a Comment