Friday, July 5, 2013

***የየራሳችንን አሻራ ለማሳረፍ ከወሬ በዘለለ ለተግባራዊ ትግል እንትጋ***

በአሁኑ ወቅት አዛዥና ታዛዥ የሌለበት የወያኔ ስርዓት ዘመኑ እያከተመ መሆኑን ከሚሰራቸው ስራዎች መገንዘብ አይከብድም።
ህግ ማሰከበር ያለበት መንግስት ላወጣው ህግ መገዛት የማይችልበት ደረጃ ከደረሰ ህልውናው አደጋ ውስጥ ለመሆኑ ማሳያ ነው።
ለዚህም መብቱን በወያኔ የተነጠቀው ህዝብ የህገ-መንግስቱን አንቀፅ እያሳየ የህግ ያለህ ሲል መደመጡ፡ በግምት የሚመራን ስርዓት የመጨረሻው ጠርዝ ላይ መቆሙን አመላካች ነው፡፡
ህውሃት/ የወያኔ ገዢ ቡድን በኢትዮጵያ ታሪክ ከነበሩት አገዛዝ ሁሉ እጅግ በከፋና በባሰ መልኩ የአገሪቱን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ የጣለ፤ ሕዝብን ከቦታውና ከቀየው እያፈናቀለ ለከፍተኛ ሥቃይና መከራ በመዳረግ ለይ ይገኛል።እንዲሁም በኃይማኖት እምነት ጣልቃ እየገባ፤ የአገሪቷን ድንግል መሬት ለባዕዳን በመሸጥ ወገኖቻችንን በማንነታቸው እንዲያፍሩና አገር አልባ እንዲሆኑ በማድረግ፤ ለእርስ በርስ ግጭትና ለከፋ ችግር ዳርጓቸዋል።
ከዚህም ባሻገር ይህ ጠባብ አረመኔ ቡድንና ጭፍሮቹ በሙስና የአገሪቱን አንጡራ ሀብት እየዘረፉ በማራቆትና ይባስ ብሎም በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ከተሞች ለሆዳቸው ባደሩ ካድሬዎች አማካኝነት ስደተኛውን በመደለል ለማስበዝበዝ ከሚሞክሯቸው ስልቶች በመቃወም ለህዝባችን አለንልህ ንንለው ወቅቱ አሁን ነው። 
ስለሆነም ኢትዮጵያንና ህዝቧን ለመታደግ በየትኛውም የትግል መስክ ተሳትፎ በማረግ ለነፃነት በሚደረገው ትግል ውስጥ የየራሳችንን አሻራ ለማሳረፍ ከወሬ በዘለለ ለተግባራዊ ትግል እንትጋ፡፡
ውድቀት ለአንባገነን ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment