Friday, July 5, 2013

ፕሬዝዳንት ሙርሲን ከስልጣን ማስወገዶ በኋላ የሚሰጡ አስተያየቶች

የግብጽ ጦር ኃይል ፕሬዝዳንት ሙርሲን ከስልጣን ማስወገዶ ጊዚያዊ ፕሬዝደንት ይፋ ማድረጉን ተከትሎ የተለያዩ ሃገራት መሪዎች እሰተያየታቸውን እየሰጡ ነው፡፡
በዴሞክራሲያዊ መንገድ ተመርጠው ወደ ስልጣን የመጡት ሙርሲ በሃገሪቱ የመከላከያ ኃይል ከስልጣን መነሳታቸው የተለያየ አይነት አስተሳሰበ እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል፡፡
የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ፣ካትሪን አሽተን በግብጽ ሁሉም ወገኖች ወደ ዴሞክራሲያዊ መንገድ በመመለስ ነጻና ግልጽ ምርጫ እንዲያካሂዱ ጠይቀዋል፡፡ የጸጥታ ኃይሉም ሁሉንም አማራጭ በመጠቀም የህዝቡን ደህንነት መጠበቅ አለባቸው ሲሉ ነው አስተያየታቸውን የሰጡት፡፡
የፈረንሳይ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ላውረንት ፋቢየስ ሃገራቸው በግብጽ ሰላማዊ ሁኔታ እንዲፈጥር ትፈልጋለች ብለዋል፡፡ህዝቡ በነጻነት መሪውንና የወደፊት እጣ ፈንታውን የሚመርጥብትን አማራጭ ማቅረብ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ እንዳልሆነም ተናግረዋል፡፡

ኳታርም በበኩሏ በአሚሯ ሸክ ታሚም ቢን ሃሚድ በኩል የእነኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፋለች፡፡ኳታር የግብፅን ህዝብ ፍላጎት ታከብራለች ብለዋል፡፡
ሳኡዲ ዓረቢያ በበኩሏ አዲስ ለተመረጡት ጊዚያው የሽግግር ፕሬዝዳንት የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክቷን ለመላክ ማንም የቀደማት አልነበረም፡ንጉስ አብደላህ ቃለመሃላ የፈጸሙትን አድሊ መንሱርን እንኳን ደስ አለዎት በማለት በዚህ ታሪካዊ ወቅት ለግብጽ ህዝብ መልካሙን ሁሉ እንመኛለን ብለዋል፡፡
ወትሮም ቢሆን ከፕሬዝዳንተ ሙርሲ ስምምነት ያልነበራቸው የሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አል አሳድ ፣የግብጽ ጦር ኃይል በፕሬዝዳንት ሙርሲ ላይ የወሰደው እርምጃ እስላማዊ ፖለቲካ ያበቃለት እንደሆነ ያመላከተ ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ በግብጽ የመጣውን ለውጥ በመልካም ጎኑ እንደምታየው ገልጻለች፡፡የሃሪቱ ወጭ ጉዳይ ሚንስትር አብዱላሂ ቢን ዛይድ አል ናሃያን ፕሬዝዳንት ሙርሲን ከስልጣን ያወረደው የመከላከያ ኃይሉ የደረሰበትን ከፍተኛ ደረጃ የሚያሳይ እንደሆነ ድርጊቱን በማሞካሸት ገልጸዋል፡፡
በዴሞክራሲያዊ ሂደት ግጭቶችን ለማስወገድ የጦር ኃይል ጣልቃ ገብነትን እንደማትደግፍ የገለጸችው እንግሊዝ ፣በውጭ ጉዳይሚንስትሯ ዊልያም ሄግ በኩል የግብጽን ዴሞክራሲ እንደገና ለማደስ ሁሉም ወገኖቸ በጋራ መስራት እንዳለባቸው አሳስባለች፡፡
ዊልያም ሄግ እንደዚህ አይንቱ ጉዳይ እጅግ አደገኛ በመሆኑ ሁከትን በማስወገድ ሃገሪቱ ለተያያዘችው የኢኮኖሚ እድገት ፈጣን የፖለቲካ ለውጥን ማምጣቱ ለግብጽ ህዝብ እንደሚበጅ ነው በአጽንኦት የገለጹት፡በግብጽ የተከሰተው አለመረጋጋት ያሳሰባት አሜሪካ ቅድሚያ በግብጽ የሚገኘው ኢንባሲዎን ደህንነት በማስጠበቅ እነደ እንግሊዝ ሁሉ የመከላከያውን ጣልቃ ገብነት እንደማትደግፍ ነው የገለጸችው፡፡
ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በግብጽና አሜሪካ መካከል ያለው የጠነከረ ወዳጀነት በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ መሆኑን በመጠቆም የመከላከያ ኃይሉ የወሰደውን እርምጃ በተመለከተ ግን እንደምታጤነው ግልጸዋል፡ይህም በመንግስት ላይ ጣልቃ የሚገባ የመከላከያ ኃይል ያለው ሃገር ከአሜሪካ ምንም አይንት እርዳታ እንዳያገኝ ከልካይ ህግ ያላት አሜሪካ በግብጽ ጦር ኃይል ላይ ጥርጣሬዋን እያሳየች ነው፡፡
ያም ሆነ ይህ ግን የሀገሪቱ ጦር ኃይል የግበፅ ከፍተኛው ህገምንግስታዊ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት የነበሩትን አድሊ ሞሃሙድ መንሱርን በሙርሲ ምትክ በጊዜያዊነት ሀገሪቱን እንዲያስተዳድሩ አስቀምጧቸዋል፡፡ አድሊ ሞሃሙድ መንሱር ከአራት ቀናት በፊት ነበር የግብፅ ከፍተኛ የህገ መንግስት ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነው በፕሬዝዳንት ሙርሲ የተሾሙት
ከሰብኣዊ



No comments:

Post a Comment