Saturday, July 13, 2013

ማሰብ ስንጀምር ሁሉ ነገር ይገባናል::

Minilik Salsawi

በሃገሪቱ የጨለማ ድባብ ውስጥ ሆነው የራሳቸውን የግል ጥቅም ለማስጠበቅ የሚራወጡ የፕሬስ ሰዎችን አንድ ማለት የዜግነት ግዴታችን ነው::ጊዜ የሰጠው ቅል... እንደሚባለው የፕሬስ ሰዎች ነን የሚሉ ሰዎች የጊዜ ጀግና ከመሆን አለፈው የመንግስት እሹሩሩ ሞግዚቶች በመሆን ብዙሃኑን ህዝብ በአደባባይ እየዘለፉት ነው::
እንደፕሬስ ባለሙያ የፕሬስ አንደበት እና አደብ ያሌላቸው ሰዎች ህዝብን መግፋት ከጀመሩ ቆይተዋል ይህ ደሞ የህዝብ ድካም ውቴት እንጂ የአዮህ ባይ ባለስልጣናት ግፊት አይደለም :: ህዝብ በአንድነት መብቱን ለማስከበር ቢነሳ ሆዳም ጋዜጠኛ ነን የሚሉትን ሊበላቸው ይችላል::
እንደነ ሚሚ ስብሃቱ ያሉ የስርኣቱ ሹምባሾች እና በሷ ዙሪያ የተኮለኮሉ የወያኔ ማፊያዊ ጠረጴዛ አባላት የህዝብን ስቃዮች ሆነ መመለስ ያለባቸው ህዝባዊ ጥያቀዎችን አንድ ቀን ሲያስተጋቡ አላየንም :: የነሱ ስራ መሳደብ ስለሆነ ማሰብ እንዲጀምሩ ብንነግራቸው መልካም ነው::
ወደ ወያኔያዊ የዜና ማሰራጫዎች ስንመጣ እንዲሁ ባልተፈጠሩ ባልተደረጉ እንዲሁም በተፈበረኩ ነገሮች ዙሪያ የሚቀመመውና ሊያጎርሱን የሚፈልጉት እሬት እየመረረን እየተፋነው መሆኑን እንዲያውቁት ልንነግራቸው ይገባል::

ጋዜጠኞቻቸው የባለስልታናቱን ትርፍራፊ ለመብላት እየተሻሙ ብሚያደርጉት ግብግብ ህዝብን እየረገጡ መሆኑን ልብ ሊሉ ይገባል:: ስለዚህ እኛም እንደነሱ ወሬ ሳናበዛ ማሰብ እንዲጀምሩ ልንነግራቸው ይገባል::
በነጻ ፕሬስ ስም የሚነግዱ እና አስመሳይ አክቲቭስት የፖለቲካ ተንታኝ እንዲሁም የጋዜጣ አውራ ለመሆን የሚፈልጉ ጋዜጠኞች ሳያውቁት የሚተነፍሱት ነገር ጌታዋን የተማመነች..... ያስብላል :: በባለስልጣናት ደጋፊነት ህዝብን ለማጋደል የተቃዋሚ ደጋፊ መስለው መርዛቸውን እየረጩ የሚገኙት እነዚህ የፕሬስ ሰዎች ሃይ ልንላቸው ይገባል:: ተመሳስለው ገብተው ሊያደፈርሱ የሚፈልጉት እና በመንግስት የደህነነት ጉያ ስር ተወሽቀው የሚያወናብዱ ጥቅመኞችን ማሰብ እንዲጀምሩ ልንነግራቸው ይገባል::
በዲያስፖራው በኩልም ያሉ ስሜታዊ ደርጋዊ የሰው አራማጅ የሆኑ ተናግሮ አናጋሪ ተመሳስለው ሰላይ ሰርጎ ገብ መሃል ሰፋሪዎችም በቃችሁ ሚናችሁን ለዩ ማሰብ ጀምሩ ብለን እናስደምጣቸው::
በእኛ በኩልም እነሱን በቃችሁ ብለን ስንነግራቸው እኛም መደባበቅ ሊበቃን ይገባል የወያኔን የግፍ ቀንበር ተሸክመን እስከመቼ ልንዘልቅ ነው:: ዝምታችንን ሰብረን ለነጻነታችን መነሳት ማሰብንም መጀመር አለብን::የዛን ሰኣት ማሰብ ስንጀምር ሁሉ ነገር ይገባናል::

No comments:

Post a Comment