ከጃዋር እና አልጀዚራ የተማርኩአቸው ቁም ነገሮች
ሰሞኑን በአልጀዚራ በተላለፈው ዝግጅት ላይ ጃዋር የሰጣቸው አስተያየቶች የብዙወቻችን መነጋገሪያ ሁነው ሰንብተዋል፤ እስኪ እኔም ትንሽ ልበል:: በመጀመሪያ ለጃዋር ከፍተኛ ክብር እንዳለኝ ለመግለፅ እወዳለሁ ፤ብዙ ጊዜ የሚሰጣቸው ትንተናወችም ጥሩ ናቸው ነገር ግን ሰሞኑን አልጀዚራ የሰጣቸው ትንተናወች ላይ አንዳንድ ጥያቄወች እና አስተያየቶች አሉኝ::
ጃዋር እንደፖለቲካ ሳይንቲስትነቱ የአልጀዚራዋ ጋዜጠኛ “are you first Ethiopia or first oromo?” ማለትም “አንተ ቅድሚያ ኦሮሞ ነህ ወይስ ቅድሚያ ኢትዮጵያ”ብላ ስትጠይቀው ጉዳይ ስሱ (sensitive) ከመሆኑ አንፃር ወጥመድ ዉስጥ እያስገባችዉ ስለነበር መጠንቀቅ ነበረበት :: እሱ እሷ እንዲሰጣት የፈለገችዉን መልስ በቀጥታ ሰጣት ፤ “እኔ ቅድሚያ ኦሮሞ ነኝ ፣ኢትዮጵያዊነት በግድ የተጫነብኝ ነው” ከማለት ይልቅ እኔ ቅድሚያ ሰው ነኝ ብሎ ማብራርያወቹን ቢያሰማ ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያዉያንም ይህን ያህል በጥርጣሬ እንዲያዩት እና እንዲያወግዙት አያደርግም ነበር :: ጃዋር ትክክል ነው የመሰለዉን ተናግሯል የምትሉ ካላችሁ ግን እኔም ለጃዋር የሚከተሉት ጥያቄወች አሉኝ::

ጃዋር “ቅድሚያ ኦሮሞ” ከሆነ ስልጣን በእጁ ቢገባስ ቅድሚያ ኦሮሞ የሚል መርህ ይከተላል ወይስ ሁሉም ኢትዮጵያዉያን እኩል ናቸው ብሎ ነው የሚያምነው ? ቅድሚያ ኦሮሞ ብሎ ካመነ አሁን ህወሃትን ከምንተችበት ቅድሚያ ትግራይ በምን ይለያል ?
ጃዋር በሙስሊሞች ትግልም ግንባር ቀደም ተዋናይ ነው ስለዚህ ጃዋር “ቅድሚያ ሙስሊም ኦሮሞ” ነው ወይስ ወይስ “ቅድሚያ ኦሮሞ” ነው ?
በሁለተኛ ደረጃ ጃዋር ኦሮሞወች ላይ የሚደርሰው ግፍ በሌሎች ኢትዮጵያዉያን ላይ ከሚደርሰው ግፍ እንደሚበልጥ ለማሳየት ያደረገው ጥረት ላይም አልስማማም:: ለዚህ ማስርጃ ያቀረበው አንዱ ማስረጃ በአደን ባህረሰላጤ የሚያቁአርጡት ስደትኞች አብዛኛዉን ኦሮሞወች ናቸዉ የሚል ነው ነገር ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ በአሁኑ ወቅት በአራቱም ማዕዘን በስደት ላይ ነው ለምሳሌ በኬንያ እና ታንዛኒያ ወደ ደቡብ አፍሪካ በጭነት መኪና በኮንቴነር እየታጎሩ የሚፈልሱትን ሲከፋም ታፍነው የሚሞቱት በአብዛኝዉ ከደቡብ ክልል የሀዲያ እና ከንባታ ወጣቶች ናቸው:: በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ዉስጥ ከአማራ እስከ ጋንቤላ፣ ከኦሮሞ እስከ ሶማሌ፣ ከሲዳማ እስከ አፋር እና ሌሎችም በህወሓት/ ኢህአዴግ እየተበድሉ እንደሆነ በደንብ ያውቃል ስለዚህ የሌሎችን ግፍና መከራም በግልፅ በመናገር ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያዉያንንም ግፍ ማስረዳት ነበረበት ምክንያቱም የሌሎች ኢትዮጵያዉያን ችግር ሳይፈታ የኦሮም ችግርም ብቻዉን አይፈታም፤ ችግሮቹ እርሥ በእርስ የተያያዙ ናቸው::
በመጨረሻም አንድ ነገር ልበል ግን ኦነግ በዓለምአቀፍ ሚዲያ የሚቀርብ ከዛ የተሻለ ተወካይ የለውም?
ማጠቃለያ
አሁንም ቢሆን የኒኮሎ ማካቬሌ ከፋፍለህ ግዛን ለዓለም ያስተማረችዉ “ዘ ፕሪንስ” ተፅፋ ለሕዝብ መድረስ ከጀመረች ይሄዉ ልክ አምስት መቶ አመቷ ቢሆንም ዛሬም በደንብ እንደምትሰራ ተገንዝብያለሁ:: ህዝብን የከፋፈለ መንግስት ምንም ግፈኛ ቢሆን ረጅም ዓመት መግዛት የሚችለው ለካ እንደዚህ ነው !
No comments:
Post a Comment