Monday, July 1, 2013

" ዘረኝነት "

ዘረያቆብ

" ዘረኝነት "
የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ,....logical or racism ?!?! 
ዘረኝነት ከጥንት ጀምሮ የነበረ ሰዉ ልጆችን የሚያሰቃይ {ቫይረስ} ነዉ
ዘረኝነት በሁለት ይከፈላል
1. በተፈጥሮ ዘረኛ የሆኑ ሰዎች አሉ ሌላዉን የሰዉ ልጅ የሚንቁ የሚያቋሽሹ እንዲሁም የሚያገሉ እራሳቸዉን ልዩ ዘር አርገዉ የሚያዩ {እነዚህን የያዘዉ የዘረኝነት ቫይረስ በቀላሉ የሚፈወስ አይደለም}

2.
ሌላዉ ደግሞ በተለያየ ምክኒያ ዘረኛ ለመሆን የተገደዱ ሰዎች ናቸዉ እነዚህ ለዘረኝነታቸዉ ምክኒያት ነዉ ብለዉ የሚያነሱት ከሌላዉ ዘር በደረሰባቸዉ ግፍ በደለ የዘር አድሎ ጭቆና እና ማጥላላት ዋነኛ ምክኒያት ነዉ
 
የአብዛኛዉ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ የመገንጠል ጥያቄ የሚያነሱ ይህን እንደ ምክኒያት ያስቀምጣሉ
ለእንደዚህ አይነት ዘረኝነት ብዙ በአለማችን የተከሰቱ እንደ ምሳሌ ማቅረብ ይቻላል 
_
የጉስላቪያዉ መሪ ሚሎሶቪች በፈፀመዉ የዘር ማጥላላት እና ጭፍጨፋ ለዩጎስላቪ መበታተን እና ወደ 7 ሃገራት መከፋፈል ዋነኛ ምክኒያት ነዉ
_
በኢስፓኒያ የጄኔራል ፍራንኮ ጦር የፈፀመዉ የዘር አድሎ እና ግፍ የባስክ እና የካታሎኒያ ተወላጆችን እስካሁን ከስፔን የመገንጠል ጥያቄ እንዳነሱ ነዉ
.......
ሌሎችም ማአት ተመሳሳይ አሉ

በአሁን ሰአት የዘር ፖለቲካ የሚከተሉ ኦሮሞዎች ዋነኛ ምክኒያት ምንድን ነዉ ??
በኢትዮጵያዊነት እኩልነት እና ፍትህ አጥተናል 
ሃሳብን በነፃነት በቋንቋችን እንግለፅ,.. ባህላችን በሚገባ የመጠቀም መብታችን ይከበር
በሃገራችን ሀብት ፍትሀዊ ተጠቃሚ እንሁን .... ወዘተ
እነዚህ ጥያቄዎች የኔም ጥያቄዎች ናቸዉ ግን መገንጠል የሚለዉን እኔም ሆንኩ ዘመዶቼ አንቀበለዉም {ኦሮሞ ያለ ኢትዮጵያ,.... ኢትዮጵያ ያለ ኦሮሞ የማይታሰብ ነገር ነዉ} 
How can we put down fire with fire

No comments:

Post a Comment