Monday, July 1, 2013

***በታሪክ አንቀልባ ታዝሎ መኖር ለማንም አልጠቀመም***

***በአሁኑ ወቅት ከየትኛውም የትምህርት ተቋም የሚመረቅ ወጣት ሀገርህ የት ነው ተብሎ ቢጠየቅኦሮምያ፣ ትግራይ፣ደቡብ፣ ሶማሌ፣አፋር…› ከማለት ውጪኢትዮጵያ ናትየሚል ለማግኘት በጣም የምንቸገርበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡***
መብላት መጠጣት፣ መልበስና ማማር ሊቀር የሚችል ተራ ነገር ነው፡፡ ማጣትና ማግኘት ተፈራራቂ በመሆናቸው ዛሬን ያጣ ነገ ያገኛል ተብሎ ይገመታልና ይህም ምንም ማለት አይደለም፡፡ አሁን እያስፈራኝ የሚገኘው ትልቁ መርዶ ግን አንድ ሕዝብ በዜግነት ማንነቱ፣ በባህሉ፣ በሃይማኖቱ፣ በትምህርት አቋሙ፣ በማኅበራዊ ሥነ ልቦናው፣ በአጠቃላይ የግንዛቤና ዓለምን የመረዳት የአስተሳሰብና የአመለካከት አድማሱበነዚህና በመሳሰለው አእምሮኣዊና መንፈሣዊ ኅልውናው ላይ አሁን የተጋረጠበት አደጋ ሊያስከትለው የሚችለው የትውልድ ምክነትና የኅልውና ቀጣይነት ችግር ነው፡፡ ይህ ዓይቱ ችግር ነው ብዙዎቻችንን እንቅልፍ እየነሳን የሚገኘው፡፡ ይህ ዓይነቱ በሰው አምሳል የሚንቀሳቀስ ሞራለቢስና በሀገሩ ላይ ሀገር አልባ የሆነ ትውልድ በብዛት የሚያመርት ሀገራዊ ችግር ነው ጥቂት የማንባል የቀደመው ትውልድ አባላትን የኅሊና ዕረፍት እያሳጣን የሚገኘው፡፡ ይህ ዓይነቱ ሀገር ያለች እየመሰለች ነገር ግን ሁለመናዋ የጠፋና እንደፀጉራም ውሻ አለች ሲሏት የሞተች ሀገር ውስጥ የመኖር አደጋ ነው እየተንሰራፋ ያለው፡፡ 
ከቁሣዊው ሕይወት አንጻር ዛሬ ቢርበንና ቢጠማን ምንም አይደለም፡፡

ዛሬን ብንታረዝ ምንም ማለት አይደለም፡፡ ዛሬን ብንከሳና ብንጠቁር፣ ብንኮስስና ብንገረጣ ብንታመምም ምንም አይደለም፡፡
ጦርነትና ርሀብ ተከስቶ የተመሰቃቀለ ችግር ቢፈጠርም አላፊ ነውና ምንም ማለት አይደለም፡፡
በጥቅሉ ዛሬን ተፈጥሯዊ ችግርን ብንቸገር በኛ ብቻ ስላልሆነ ምንም አይደለም፡፡
ይህ እንግዲህ በሥጋዊ አስተሳሰብ ነው፡፡ ብዙ የዓለም ሀገሮችም በዚህ ሂደት አልፈዋል፤ ዛሬ የሥልጣኔና የቅንጦተኛ ኑሮ ቁንጮ የሆኑት እነአሜሪካና (ቻይና?) እነጃፓንና ከሞላ ጎደል ሁሉም የአውሮፓ ሀገሮች በጠኔና የርስ በርስ ጦርነትን ጨምሮ በአሰቃቂ ችግሮች ውስጥ አልፈው ነው (በአንጻራዊ ሁኔታ የአሁኑ) ምድራዊ ገነት ውስጥ ሊገቡ የቻሉት፡፡ በታሪክ አንቀልባ ታዝሎ መኖር ለማንም አልጠቀመም እንጂ ኢትዮጵያም አንድ ወቅት ለተቸገሩ ሀገሮችና ሕዝቦች የምትረዳ ርህሩሂት ሀገር እንደነበረች የቅርብ ጊዜው ታሪካችን የሚዘክረውና ፈረንጆችና ሌሎች የውጪዎች ሊያምኑት የሚቸግራቸው ተኣምር ነው፡፡ ለጃፓን፣ ለኮርያ፣ ለካናዳና ለብዙ የአፍሪካ ሀገሮች ፍጡነ ረድኤት የነበረች ሀገራችን ዛሬ ሌሎችን መርዳት ይቅርና ቅን አሳቢ ሰው የማይወጣባት፣ መጭና ወበሎ የሚበቅልባት፣ ጅቦችና ዓሣማዎች የሚራቡባት (የሚፈለፈሉባት ለማለት እንጂ ርሀቡስ ሲያልፍም አይነካቸው!) እጅግ አሳዛኝ ሀገር ሆናለች፡፡ ጤናማ ዜጎቿ እግር ባወጣ እየተሰደዱ፣ በሀገር ቤት ያሉትም በፍርሀት ተሸብበው አንገታቸውን እየደፉ፣ ብዙዎችምሁራኗወያኔ የቀደዳለቸውን ቦይ በመከተል በዘርና በጎሣ ተከፋፍለውና በአጥፊና ጠፊ አማሳኝ ጎራዎች ተቧድነው ኃይላቸውን በልማትና በችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ሥራዎች ላይ ሳይሆን በጉንጭአልፋ ንትርክ የሚያባክኑ፣ በውጤቱ ደግሞ ታሪካዊ ጠላቶቿ ያሰማሯቸው የውስጥ የጠላት ቅጥረኞችና ሸማቂዎች ያገኙትን ወርቃማ ዕድል ተጠቅመው ሀገሪቱ ዳግም እንዳታንሰራራ የሚቀጠቅጡበት ሁኔታ ተመቻችቶላቸው ሳንወድ በግዳችን በታሪክ ጠማማ ፍርድ እየተንገፈገፍን እንገኛለን፡፡ ቅጥቀጣው ቁሣዊ ብቻ ቢሆን እንደገለጽኩላችሁ ብዙም ባልከፋ፡፡ የቅጥቀጣው መሠሪነትና አሰቃቂነት ግዘፍ ነስቶ የሚታየው ነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ እንዳይኖር ሆን ተብሎ ታቅዶ በሚደረገው ሁልአቀፍ ጥረት አማካይነት እየታዘብነው በምንገኘው ወደርየለሽ ጭካኔ የተሞላት ዕኩይ ድርጊት አማካይነት ነው፡፡ ለአብነት በአሁኑ ወቅት ከየትኛውም የትምህርት ተቋም የሚመረቅ ወጣት - አብዛኛው ማለት በሚቻል ሁኔታ - ስሙን በእንግሊዝኛ አስተካክሎ የሚጽፍ ስለመሆኑ በርግጠኛነት መናገር አይቻልም፤ ይህ የተደረገውና እየተደረገ ያለውም ሆን ተብሎ በተጫነ ትውልድ ገዳይ የመማር ማስተማር ሂደት ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ከየትኛውም የትምህርት ተቋም የሚመረቅ ወጣት ሀገርህ የት ነው ተብሎ ቢጠየቅኦሮምያ፣ ትግራይ፣ደቡብ፣ ሶማሌ፣አፋር…› ከማለት ውጪኢትዮጵያ ናትየሚል ለማግኘት በጣም የምንቸገርበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡ ይህ ዓይነቱ ወያኔያዊ ከፋፍሎ የመግዛት ዘዴ ሀገራችንን እያጠፋት ነው - የፈጣሪ ሥራ ካልተጨመረበት በስተቀር በቀላሉ ልታገግም በማትችልበት ሁኔታ እየወደመች ናት፡፡

ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment