ሀገራችን ኢትዮጵያ እጅግ ሰፊ እና ጥልቅ ታሪክ ያላት ሀገር ስትሆን ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ ግን የምናስተዉለው ነገር አሁን ያለው ትዉልድ ታሪክ እና የጊዜአችን ፖለቲካ እየተቀላቀሉበት ታሪክን በዘመኑ ሸዉራራ የፖለቲካ መነፅር እየተመለከተ ወይም እንዲያይ እየተገደደ እራሱ ግራ ገብቶት ሌላዉን ግራ ሲያጋባ ነው:: ነገሩን አሳሳቢ የሚያደርገው ደግሞ ታሪክን የማንሸዋረሩን ሥራ ከመንግስት እስከ ሙህራን፣ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ እስከ ግል ጋዜጦች ሲተገብሩት ማየቱ ነው::
የመጀመሪያ ዓመት የዩንቨርሲቲ ተማሪ በነበርኩበት ወቅት የ“Ethiopian History” የተባለ ‘ኮርስ’ የሰጠኝንመምህር ችሎታዉንና የማስተማር ስልቱን የማደንቅለት የነበረ ቢሆንም አንዳንዴ ታሪክን በራሱ ፖለቲካዊ አመለካከት በርዞ ሊግተን ሲሞክር በልቤ እታዘበው ነበር፤ ምክንያቱም ትምህርቱን ባብዛኛዉ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴ የተማርኩት ስለነበረና ለታሪክ ትምህርት ከነበርኝ ጥልቅ ፍቅር የተነሳ የተለያዩ የታሪክ መፃህፍትን በግሌ አንብቤ ቀደም ብዬ ኮርሱን ባብዛኛዉ አዉቀው ስለነበር እሱ እንደገና በአዲስ መልክ ዘመነኛ ፖለቲካዊ ይዘት አስይዞ ሲያቀርበው ይገርመኝ ነበር :: በአሁኑ ጊዜ እንደዚህ አይነት አንሸዋራሪ ሙህራን ቁጥር ቀላል አይደለም::
የመጀመሪያ ዓመት የዩንቨርሲቲ ተማሪ በነበርኩበት ወቅት የ“Ethiopian History” የተባለ ‘ኮርስ’ የሰጠኝንመምህር ችሎታዉንና የማስተማር ስልቱን የማደንቅለት የነበረ ቢሆንም አንዳንዴ ታሪክን በራሱ ፖለቲካዊ አመለካከት በርዞ ሊግተን ሲሞክር በልቤ እታዘበው ነበር፤ ምክንያቱም ትምህርቱን ባብዛኛዉ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴ የተማርኩት ስለነበረና ለታሪክ ትምህርት ከነበርኝ ጥልቅ ፍቅር የተነሳ የተለያዩ የታሪክ መፃህፍትን በግሌ አንብቤ ቀደም ብዬ ኮርሱን ባብዛኛዉ አዉቀው ስለነበር እሱ እንደገና በአዲስ መልክ ዘመነኛ ፖለቲካዊ ይዘት አስይዞ ሲያቀርበው ይገርመኝ ነበር :: በአሁኑ ጊዜ እንደዚህ አይነት አንሸዋራሪ ሙህራን ቁጥር ቀላል አይደለም::
በሌላ በኩል ምርጫ ፱፯ (97)ን ተከትሎ የተነሳበትን ተቃዉሞ ለማብረድ መንግስት በመላ ሀገሪቱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪወችን ክረምት ላይ ሰብስቦ ሲሰጠን የነበረዉ ትምህርት ታሪክን የሚያዛባ ብቻ ሳይሆን አንዱ ብሔር በሌላዉ፣ አንዱ ሃይማኖት በሌላዉ ላይ ጥላቻ እንዲያዳብር የሚቀሰቅስ ነበር፤ በወቅቱ የዩንቨርሲቲ ተማሪ የነብራቹና በዚህ ስልጠና ላይ የተሳተፋችሁ ሰወች ወደሁአላ ተመለሱና ሟች ጠቅላይ ሚንስትር መለስን ጨምሮ እነ በረከት ስምዖን በፕላዝማ ቴሌቪዥን ብቅ እያሉ ምን ይሉን እንደነበር አስታዉሱ:: ለስልጠና ተዘጋጅቶ የነበረዉ ሰማያዊዉ መፅሀፍም እንዴት ታሪክን አዛብቶ ወይም ጎደሎ አድርጎ ጥላቻን ይሰብክ እንደነበር ልብ በሉ ፤ መፅሐፉን ያስቀመጣችሁት ካላችሁም እስኪ ገለጥ ገለጥ አድርጋችሁ እንደገና እዩት:: አንዳንዴ ሟች ጠቅላይ ሚኒስትር በትግራይ አካባቢ ሰወች ዘንድ ባብዛኛዉ ጀግና ተደርገው ሲቆጠሩ በሌላዉ ኢትዮጵያዊ ደግሞ ባብዛኛዉ አምባገነንነታቸው የሚነገረዉ እሳቸዉ እና መሰሎቻቸዉ የዘሩት ዘር ፍሬ ይሆን ብዬ አስባለሁ :: በሌላ በኩል ታሪክን ማንሸዋረሩን ሀገራችን ዉስጥ ይታተሙ የነበሩ የተቃዋሚ ፓርቲ ጋዜጦች ላይም ያነበብኩበት ወቅት ትዝ ይለኛል::
ከዚህ ላይ ታሪክን ማንሸዋረር ማለት እራሱ ምን ማለት ነው?ታሪኩ የተንሸዋረረው በማን እይታ ነው? ታሪክ ተንሸዋሮ ቀረበ የሚባለዉ የትኞቹን መስፈርቶች ሳያሟላ ሲቀር ነው ? ብላችሁ ልትጠይቁ ትችላላችሁ:: እነዚህን ነገሮች በንድፈ ሃሳብ ከማስረዳት ይልቅ በእዉነታዉ ከምናዉቃቸዉን ነገሮች በማሳየት ላስረዳ:: ለምሳሌ በፌስ ቡክ እና በሌሎች መገናኛ ዘዴወች የሚደረጉ የታሪክ ዉይይቶችን ስንመልከት የጎሰኝነትና የጎጠኝነት መንፈስ በግልፅ ይታይባቸዋል:: እሱ ከተወለደበት አካባቢና ብሔር የተገኙትን ታሪካዊ መሪወችና ታሪካዊ ሰወች እያሞጋገሱ እና እየካቡ ከሱ አካባቢና ብሔር ዉጭ የሆኑትን መሪወችና ታሪካዊ ጀግኖች ታሪክ ጥላ እሸት እየቀቡ ማራከስ የተለመደ አሳዛኝ ተግባር ነው:: ለኔ ይህ እና መሰል ተግባራት ታሪክን ማንሸዋረር ነው ::
አንድ ሰው የአፄ ቴወድሮስን ታሪካዊ ጀግንነትና ራዕይ ለመዘከር የግድ ጎንደር መወለድ የለበትም፥ አፄ ዮሐንስ ለሀገራቸዉ የከፈሉትን መስዋትነት ለማመን የግድ ትግራይ መወለድ የለበትም ፣የአፄ ምንሊክን የአድዋ ጀግነነት ለመመስከር ሽዋ መወለድ የግድ አይልም፣ የአብዲሳ አጋን ከኢትዮጵያ እስከ አዉሮጳ የዘለቀ አርበኝነት ለመቀበል ወለጋ መወለድ ወይም ኦሮሞ መሆን አያሻም:: የነበላይ ዘለቀ፣ አሉላ አባነጋ እና የሌሎችን ኢትዮጵያዉያን ጀግኖችን ታሪክ ለመቀበል የግድ እነሱ ከተገኙበት አካባቢ መወለድ አያስፈልግም ኢትዮጵያዊ መሆን በቂ ነው፤ ምክንያቱም እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ እና ያልተጠቀሱ ጀግኖች መስዋትነት የከፈሉት እና የተዋጉት ለሀገራቸው እንጂ ለአካባብያቸዉ እና ለብሄራቸዉ ነው የሚል የታሪክ ድርሳን እስካሁን አላየሁም ነገር ግን በዘመናችን የተንሸዋረረ የፖለቲካ መነፅር እያዩ እንደዚህ የሚያወሩና የሚያስቡ ሠወች ቁጥር ቀላል የሚባል አይደለም:: ከዚህ ላይ ታሪካዊ ሰወች በተለይ መሪወች ሰዉ እንደመሆናቸው መጠን በዘመናቸው የሰሩት ጥፋት ይኖራል ስለዚህ ጥንካሬአቸውን ማድነቅና መውሰድ ከድክመታቸውም መማር እንጅ በጎጠኝነት አስተሳሰብ ታጥሮ የጎጣችን እና የብሄራችን የሆነዉን ፍፁም እንደሆነ አድርጎ ማሞገስ የሌላዉን ምንም ቁም ነገር እንዳልሰራ ጥፋቱን እያጋነኑ ማራከስ እኛን ቢያስገምተን እንጂ እነሱ የሰሩትን ታሪክ አይቀይረዉም ::
ከማስታዋል
No comments:
Post a Comment