Wednesday, August 28, 2013

አንድነት በሮቤ ከተማው ሰላማዊ ሰልፍ እንግልት ገጠመኝ አለ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) በባሌ ሮቤ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ባቀደው ፕሮግራም ላይ ከፍተኛ እንግልት እንደገጠመው ገለፁ።
ፓርቲው ባወጣው መግለጫ ነሐሴ 13/2005ቱ ሰላማዊ ሰልፍ ቀስቃሾች ፖስተር እና በራሪ ወረቀት በሚለጥፉበት ወቅት መታገዳቸውን ገልጿል። እንደ መግለጫው ከሆነ ቀስቃሾቹ ነሐሴ 18 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 19 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ከነመኪናቸው ከቆሙበት እንዳይንቀሳቀሱ ተደርጓል። ከዚህ በተጨማሪም የሀገር ሽማግሌዎች እኛን ሳታነጋግሩና ሳንፈቅድላችሁ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ የለባችሁም እንዳሏቸው ገልፀዋል።
ፓርቲው ሰላማዊ ሰልፉን ለማድረግ በሚሞክርበት ወቅት በፌዴራል እና በክልሉ መንግስት እንዲሁም  በአካባቢው ሽማግሌዎች በተለያየ አቅጣጫ ከፍተኛ ጫና እንደተደረገበት እና የቻለውን አማራጭ ሁሉ መጠቀሙንም ገልጿል። (የፓርቲውን መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው አቅርበነዋል።) 

***        ***        ***


የኢህአዴግ ስውር ሴራ በሮቤ ከተማ ተጋለጠ!!!
ሐገሪቷን የሚያስተዳድራት ማነውየባሌ ሮቤ ሰላማዊ ሰልፍ ለምን ተደናቀፈ?
ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነትየተሰጠ ማብራሪያ

የሚሊየኖች ድምፅ ለነፃነት ንቅናቄ በአራቱም የኢትዮጵያ ማዕዘናት የነፃነት ድምፅ ማስተጋባት ከጀመረ እንሆ ዛሬ ስልሳሰባተኛ(67) ቀኑን ይዟል። ፓርቲያችን በእዚህ ታላቅ ሕዝባዊ የነፃነት ንቅናቄ መሪር የሆነ ውድ ዋጋ እየከፈለ ድምፅ አልባ ለሆኑትሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን ድምፅ በመሆኑ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል።
ላለፋት ስምንት ዓመታት ሰቆቃ እና ግፍ በገዢዎቻችን ሲፈፀምበት የኖረው የገጠሩም ሆነ የከተማው ታላቁ ህዝባችንአንድነት ፓርቲአችን አስትንፋሳችን’ በማለት  አንድነት ፓርቲ ባመቻቸለት ህዝባዊ ስብሰባዎች እና ሠላማዊ ሠልፎች በነቂስበመውጣት የታፈነ ብሶቱን በግልፅ በአደባባይ ላይ በማሰማቱ ኢህአዴግ እና ህዝቡ ዛሬም ድረስ ተለያይተው እንዳሉ አንድነት ፓርቲበማያወላዳ ሁኔታ በሚሊዮኖች ድምፅ ንቅናቄ በህዝባችን መሀል በመገኘት አረጋግጧል።
ኢህአዴግ የቀረው በውሸት እና በሴራ የተሞላ የቅጥፈት ፕሮፖጋንዳ ብቻ መሆኑን ይበልጥ ያረጋገጠልን የባሌ ዞንአስተዳደር እና የሮቤ ከተማ አስተዳደር ያዘጋጁት በሀገር ሽማግሌዎች ስም የተቀነባበረው የእናደራድራችሁ አሳፋሪ ድራማለኦህዴድም ሆነ ለኢህአዴግ ታላቅ ውድቀት ነው።
አንድነት ፓርቲ በባሌ ሮቤ ከተማ ሠላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ህጉ በሚያዘው መሰረት ነሐሴ 13/2005 የሰላማዊ ሰልፍማሳወቂያ ደብዳቤ ለከተማዋ አስተዳደር አስገባ። ጉዳዩን የሚከታተሉት የፓርቲው ተወካዮች ደብዳቤው ከገባ 48 ሠዓት በኋላ ወደመደበኛ ቅስቀሳቸው መግባት እንደሚችሉ ህጉ እንደሚፈቅድላቸው የተረዱት የፓርቲያችን ትንታግ ታጋዮች ጊዜ ሳያባክኑየተዘጋጀውን የቅስቀሳ በራሪ ወረቀት በከተማ ውስጥ ማሰራጨት ጀመሩ።
ሁኔታውን በቅርብ ሲከታተሉት የነበሩት የፌደራል መንግስት እና የክልሉ መንግስት ከሮቤ ከተማ አስተዳደር ጋርበመቀናጀት አንድነት ፓርቲ ላይ ያጠመዱት ሴራ ለመተግበር የከተማው ከንቲባ አቶ አብዱል ላጥፍ ነሓሴ 13/2005 ለገባላቸውየፓርቲው ደብዳቤ መልስ ያሉትን ነሓሴ 13/2005 ቀን እንደ ተፃፈ ተደርጎ ፓርቲው አላማ ያሉትን ዘርዝረው ነሓሴ 17/2005 .ደብዳቤ ለፓርቲው ተወካዮች ሰጡ። የተባሉትን ሰበቦች እና ምክንያቶችን በሙሉ አሟልቶ ፓርቲው የእዚያኑ ዕለት በደብዳቤ ምላሽቢሰጥም የከተማው አስተዳደር ባለስልጣኖች ከንቲባውም ጭምር ቢሮአቸውን ዘግተው ጠፉ። መዝገብቤትም ለማስገባትየተደረገው ጥረት በመዝገብ ቤት ሰራተኞች እምቢ ባይነት ሳይሳካ ቀረ። የአምባ ገነኑን የኢህአድግ ባለስልጣኖችን ነውረኛ ስራቀድሞ የሚያውቀው የአንድነት ፓርቲ የተዘጋጀውን ደብዳቤ በሪኮማንዴ በፓስታ ቤት በኩል አንዲደርሳቸው በማድረግ ምንምመፈናፈኛ ሰበብ እንዳያገኙ አደረገ።      
ግራ የገባቸው የከተማው አስተዳዳሪዎች ተሰባስበው ከላይ በተሰጣቸው ትእዛዝ መሰረት አንድነትን የማጥቅያ ሌላ ሴራተጠቅመው መጥታችሁ የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያውን ቅፅ ሙሉ በማለት ለተወካዮቻችን ጥሪ አደረጉ። የፓርቲው ተወካዮችስራቸውን እየሰሩ ቅፁን የሚሞሉ እና የሚፈርሙ አባላትን በመመደብ ተወካይ ብቻ ወደ ወስተዳድሩ /ቤት ላኩ። የጠበቃቸው ግንየተቀናጀ ሴራ ነው። አንድነት ፓርቲን በህግ የሚያስጠይቅ እንዲሁም ያዘጋጁትን የሀይል ርምጃ ህጋዊ የሚያደርግ፤ ደብዳቤ ካስገባን48 ሰዓታት ባነሰ ጊዜ ሰልፍ እወጣለሁ ብሎ ፓርቲው ነሓሴ 17/2005 ደብዳቤ እንዳስገባ ተደርጎ ይህንኑ ቀን የጠቀሰ ቅፅአዘጋጅተው የአንድነትን ተወካዮች አንዲፈርሙ ተጠየቁ። ቀድሞውኑ ሴራው የገባው የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር በሰጠውመመርያ መሰረት ቅፁ ላይ የምንፈርመው ደብዳቤአችንን ያስገባንበትን ነሐሴ 13/2005 ቀን ከጠቀሰ ብቻ ነው በማለት የአንድነትተወካዮች አንፈርምም አሉ።
አንድነት ፓርቲን በጉልበትም በህግም ለማኮላሸት ኢህአድግ ያዘጋጀውን ሴራ በጥበብ ማክሸፍ ተቻለ። ኢህአዴግ ለሌላሴራ ማቀንቀኑን ወድያውኑ ተያያዘው።
የፓርቲው ቀስቃሽ ቡድን 50‚000 የሚገመት በራሪ ወረቀት መበተኑን እና 5‚000 በላይ ፖስተር በእለቱ በመለጠፍየፓርቲውን መልእክት ለታፈነው የሮቤ ከተማ ህዝብ አደረሰ። በሁለት መኪና መጠነኛ ቅስቀሳ ካደረገ  100 ሰዓት በኋላመኪናዎቹ ከነቀስቃሽ ቡድኑ ከነሀሴ 18/2005 እስከ እሁድ ነሀሴ 19/2005 ድረስ በታጣቂዎች ከቆሙበት አንዳይንቀሳቀሱ ታገቱ።የትራፊክ ፖሊሶችም መኪናዎቻችንን በማገት ያለቆቻቸውን ትዕዛዝ ተግባራዊ አደረጉ። በዚህ መሀል ነው በሽማግሌ ስምያደራጃቸውን 15 የሚሆኑ የኦህዴድ ካድሬዎች “ነገ የሚከሰተው ደም መፋሰስ አሳስቦን ነው የመጣነው እናወያያችሁ” በማለትከምሽቱ 130 ባረፍንበተ ሆቴል ተሰባስበው የመጡት። ለሀገር ሽማግሌ ክብር የሚሰጠው አንድነት ፓርቲ ሽማግሌዎች የተላኩበትንዝርዝር መልእክት ካዳመጠ በኋላ የእሁዱን ሰላማዊ ሰልፍ በምንም ተአምር እንደማንሰርዘው፤ ይልቁንም የከተማው መስተዳድርለፖሊስ የሀይል እርምጃ ውሰዱ ብሎ ያስተላለፈውን መመሪያ እንዲስብና ህገመንግስቱን እንዲያከብር ሽማግሌዎቹ ምክራቸውንለገዢው ፓርቲ ባለ ስልጣኖች እንዲለግሱ መልእክት በመንገር ውይይቱ ከምሽቱ 300 ሰዓት ተጠናቀቀ። በኢህአድግ የተለመደቀመር የቅስቀሳ ጊዜያችንን በጉልበት እና በማስመሰል ለመስረቅ የተደረገውን የተለመደ ቅንብር አንድነት ፓርቲ ቀድሞ የሚያውቀውጉዳይ በመሆኑ ሁለት ተደራዳሪዎችን ብቻ በመመደቡ ሌላው ግብረኃይል ሳይዘናጋ የቅስቀሳ ወረቀቱን በማሰራጨቱ ኢህአዴግያሰበውን አንድነትን የመነጠል ሴራ ሳይሳካለት ቀርቷል።
እነዚያው የሀገር ሽማግሌዎች የተባሉ ግለሰቦች “መስተዳድሩ አሁን ሊያነጋግራችሁ ዝግጁ ነው። ቢሮ ድረስ  እናተወያዩ” በማለት በሰላማዊ ሰልፉ ቀን እሁድ ከጥዋቱ 100 ሰዓት እኛን ቀጥረውን በሰዓቱ ስንደርስ የኦሆዴድ ባለስልጣኖች ግንየጠዋቱ የቅስቀሳ ስዓታችንን ለመስረቅ ከጠዋቱ 140 በሁለት ኮብራ መኪና እና ታርጋ በሌላት በአንድ መኪና በደህንነት ባለስልጣኖች ታጅበው መጡ።
ውይይቱ በዞኑ /አስተዳዳሪ አቶ ሰሎሞን አወያይነት የከተማው ከንቲባ፣ የኦሆዴድ ተጠሪ የኮምኒኬሽን ኃላፊ ሌሎችም15 ያላነሱ ባለ ስልጣኖች እንዲሁም በርካታ የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት ሦስት የመንግስት ካሜራዎች ተጠምደው ውይይቱተጀመረ።
የሽማግሌ ካባ የለበሱት የኦሆዴድ ካድሬ የሆኑት የሀገር ሽማግሌዎች ተወካይ ነኝ ያሉት ግለሰብ ውይይቱን በንግግርሲጀምሩ “እናንተ የነፍጠኛን ስርዓት ልታመጡብን ነው። እኛን ሳታነጋግሩ ሳንፈቅድላችሁ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንዴትአሰባችሁአሁንም ይህንን ሰላማዊ ሰልፍ አታደርጓትም። የሮቤ ህዝብ እኛን ዎክሎናል መንግስት እንኳን ቢፈቅድላችሁ እኛሽማግሌዎች አይደረግም ብለናል አቁሙ” በማለት የተጫኑትን ዉሳኔ በሚደንቅ ሁኔታ አስተላለፉ። በእዚያው መድረክ የኢህአዴግ/ኦህዴድ ማንነት እና ጭንብል ለዓለም ህዝብ ተጋለጠ። አንድነት ፓርቲም ይህንን ከላይ እስከታች ባሉ ባለስልጣኖች የተቀነባበረውንድራማ በካሜራ ቀርፆ ያስቀረ በመሆኑ በእጃችን የሚገኘውን የውይይቱን ይዘት የያዘውን ቨድዮ እንድትመለከቱ በአክብሮት እየጋበዝን አንድነት ፓርቲ የኢህአዴግን እውነተኛ ገፅታ በመረጃ ማጋለጡን  አጠናክሮ ዛሬም ነገም ይቀጥላል።
በሮቤ ከተማ ለቅስቀሳ የተላከው ቡድን በመስተዳድሩ ባለስልጣናት ትእዛዝ ከምሽቱ 400 ስዓት አልጋ ከያዙበትታይታኒክ ሆቴል በግፍ ተባረው፤ የያዙትን ቦርሳ እንኳን ከመኝታ ክፍላችው ሳያወጡ በግፍ አውላላ ሜዳ ላይ ወንጀልእንዲፈፀምባቻው የከተማው መስተዳድር የፍፀመውን መንግስታዊ ውንብድና ፓርቲአችን በዝምታ የሚያልፈው ጉዳይ አይደለም።የመኪና ሹፊሮቻችንን በውድቅት ሌሊት ጭንብል ባጠለቁ  20 በላይ ታጣቂዎችን በማሰማራት በማስወረር በጉልበት ክፍላቸውውስጥ በመግባት ስለተፈፀመው ወንጀል አንድነት ፓርቲ በህግ የሚጠይቅ ሲሆን ታላቁ የሮቤ ከተማ ነዋሪ ህዝብ መብቱንለማስከበር ያደረገውን ትንቅንቅ አንድነት ፓርቲ ከልብ ያደንቃል። ምስጋናውንም በእዚህ አጋጣሚ ያቀርባል። 
ድል ለታፈነው የኢትዮጵያ ህዝብ!!!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ
ነሐሴ 21 ቀን 2005 .
አዲስ አባባ

No comments:

Post a Comment