ሙት ዓመትና ተዝካር የሚያወጣ መንግሰት ያየሁት የኛው ጉዴ የሆነው በስሌጣን ሊይ ያሇው ፓርቲ መሆኑን መጠራጠር ያሇብን አይመስሇኝም፡፡ ፋውንዳሽኑ እንጂ የመንግሰት አይዯሇም የሚሌ ማምታቻ እንዯማይሰራ ከዚሁ ማሰጨበጥ ያስፈሌጋሌ፡፡ ሌክ ነው የአንዯኛ ዓመት መታሰቢያ በአንዴ አዲራሽ ቢታሰብ ክፋቱ አይታየኝም፡፡ ነገር ግን ሁለም የመንግስት መዋቅር የ”ሕዝብ” ተወካዮች ምክር ቤቱን ሰራተኞቹን ጨምሮ የሙት ዓመት ሇማክበር የመንግሰት ሰራ አቋርጠው ችግኝ ተከሊ ወይም የሻማ ማብራት ሰነ ስርዓት ሊይ መገኘት ተገቢም ትክክሌም አይመስሇኝም፡፡
ከሁለም የሚገርመው በሙት ዓመት ሊይ ሇመገኘት ወዯ ሀገራችን የመጡት መሪ ተብዬዎች እና ተወካዮች ናቸው፡፡ እርግጥ ነው የሱዲኑ ፕሬዝዲንት ከሸሪክ አንባገነን ሀገሮች ውጭ መሄዴ ስሇማይችለ የእርሳቸው ጉዞ በእውነቱ አጋጣሚውን ተጠቅሞ ወጣ ሇማሇት ብሇን በቅንነት ሌንወስዯው እንችሊሇን፡፡ የሚያሳዝነው ይህን ጉዲይ ብሇው የመጡ መሪዎችን ሇመቀበሌና ሇመሸኘት በሚዯረግ ሸብ-እረብ ዜጋው የገጠመው ሰቃይ ነው፡፡ ሁለም እንዯሚረዲው የአዱሰ አበባ ከተማ በአጭሩ ሉቃሇሌ በማይችሌ የትራንስፖርት አገሌግልት ቅርቃር ውስጥ ትገኛሇች፣ በዚህም ሊይ በተሇያየ የመንገዴና የባቡር ግንባታ ምክንያት ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት ችግር አሇ፡፡ እዚህ ሊይ ነው እንግዱህ ሰራ ፈት መሪዎች ሙት ዓመት ብሇው መጥተው ከተማዋ ሊይ ጫና ፈጥረው በእንቅርት ሊይ ጆሮ ዯግፍ ያሰኙን፡፡
No comments:
Post a Comment