በአንድነት ሆነን የምንጮኸው ድምጽ ተመሳሳይ ቃና ሊኖረው ይገባል። ለአንድ ወገን ብቻ መጮኻችን በቂ አይደለም።ሁላችንም በደም ተዋህደናል ማንም ሊበታትነን አይገባም!
አሁን ላይ ሆነን ያለፈውን ታሪክ የምናነሳው፤ ያለፈ ጥፋታችንን እንዳንደግም ነው። ካለፈው ጥፋታችን የምንማረው አንድ ቁም ነገር ቢኖር… ኢትዮጵያ ውስጥ ህንጻን በማቃጠል፤ ማንም የማንንም ሃይማኖት አለማጥፋቱን ነው።
የማንኛውም ሐይማኖት በአንዱ እምነት ላይ አደጋ ማድረስ አይገባም።
ሊሆን፣ሊታሰብ፣ሊደረግ፣ሊፈፀም የማይደረግ ተግባር!!!
ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ያለ እውነታ ይኽ ነው ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ተንስሁ ለፀሎት ስትል ጎንን ለጎን ያለው አንዋር መስጂድም አላዋክበር የሚባልበት ስፍራ ነው ይህ በአለም ላይ የሌለ አንዱ መገለጫጭን ነው።
ከዚህ መሰረታዊ እውነታ በመነሳት ወደፊት በፍቅር እንጂ፤ በጸብ የማንኖርባትን ኢትዮጵያ፤ በመከባበር መገንባት ይኖርብናል። ከአንድ አመት በላይ የቆየው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የሚያነሱት ጥያቄም የመብት ጥያቄ መሆኑን አብላጫው ህዝብ ያምንበታል። በእስር ቤት ከሚገኙት የኮሚቴ አባላት መካከል አንደኛው ሲናገር፤ “እኛ እኮ በምርጫውም ጊዜ ኢህአዴግን እንጂ ቅንጅትን አልመረጥንም” ቢልም እንኳን የቅንጅት ደጋፊ የነበሩ ሰዎች አላዘኑበትም፤ “የኢህአዴግ ደጋፊ ነኝ” ስላለም ኢህአዴግ አላዘነለትም – ትላንት ቅንጅቶች እና ጋዜጠኞች የታሰሩበት ቃሊቲ በሩን ከፍቶ ሁሉንም አስተናግዷል። ነገ ማን እንደሚስተናገድበት የሚያውቀው ግን አንድ አምላክ ነው። እናም እንዲህ ጊዜ እና ሁኔታ በሚፈራረቁበት ዘመን ላይ ሆነን፤ ከነልዩነታችንም ቢሆን፤ ቢያንስ ለሰው ልጆች መብት በእኩል መንፈስ ልንቆም ይገባል።አሁን ላይ ሆነን ያለፈውን ታሪክ የምናነሳው፤ ያለፈ ጥፋታችንን እንዳንደግም ነው። ካለፈው ጥፋታችን የምንማረው አንድ ቁም ነገር ቢኖር… ኢትዮጵያ ውስጥ ህንጻን በማቃጠል፤ ማንም የማንንም ሃይማኖት አለማጥፋቱን ነው።
የማንኛውም ሐይማኖት በአንዱ እምነት ላይ አደጋ ማድረስ አይገባም።
ሊሆን፣ሊታሰብ፣ሊደረግ፣ሊፈፀም የማይደረግ ተግባር!!!
ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ያለ እውነታ ይኽ ነው ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ተንስሁ ለፀሎት ስትል ጎንን ለጎን ያለው አንዋር መስጂድም አላዋክበር የሚባልበት ስፍራ ነው ይህ በአለም ላይ የሌለ አንዱ መገለጫጭን ነው።
የሃሳብ እና የሃይማኖት ልዩነት ሊኖር ይችላል። ነገር ግን የሰው ልጅ መብት ሲረገጥ “እሰይ ደግ አደረገ!” የሚል ሰይጣናዊ መንፈስ በውስጣችን ሊኖር አይገባም። ለዚህም ነው… ሙስሊም ወገኖች ሲታሰሩ እና ሲደበደቡ ሌላው ክርስቲያን ወገናቸው ድምጹን ደግሞ ደጋግሞ ሲያሰማ የነበረው። አንዳንዴ የክርስቲያኑም ሆነ፤ የፖለቲካ ድርጅቶች ጩኸት የሚሰማ እስከማይመስል ደረጃ ላይ ቢደረስም እንኳን፤ ህውሃት/ኢህአዴግ እያደረሰ ያለውን የግፍ ተግባር ሁሉም ወገን እያወገዘው ይገኛል። የሰብአዊ መብት ረገጣን ማውገዝ ደግሞ ከአንድ የሰለጠነ ህዝብ የሚጠበቅ ተግባር በመሆኑ፤ በኢትዮጵያ እየደረሰ ያለውን ግፍ የምናወግዘው ውለታ ለመቆጣጠር ሳይሆን፤ የሰለጠነ ህሊናችን ስለሚያስገድደን ነው።
ከሰብኣዊ
No comments:
Post a Comment