Saturday, August 31, 2013

የሰማይዊ ፓርቲ አመራሮች በስብሰባ ላይ እንዳሉ የወያኔ ፌደራል ፖሊስ ቢሮውን በመክበብ ሁሉንም የአመራር አባላትን በመኪና ጭኖ ወደ እስር ወስደዋቸዋል።



ከምሽቱ 1:00 ላይ የሰማይዊ ፓርቲ አመራሮች አራት ኪሎ 

አካባቢ በሚገኘው ጽ/ቤታቸው በስብሰባ ላይ እንዳሉ የወያኔ 

ፌደራል ፖሊስ ቢሮውን በመክበብ ሊቀ-መንበሩን ጨምሮ 

ሁሉንም የአመራር አባላትን በመኪና ጭኖ ወደ እስር 

ወስደዋቸዋል።በውጭም በውስጥም የሚኖረው መላው 

የኢትዮጵያ ህዝብ ድርጊቱን እንዲያወግዝና ለአለም-አቀፍ 

ተቁማትም ሁኔታውን እንዲያሳውቅ ጥሪ ቀርቧል። ሞት ለወያኔ 

ትግሉ ይቀጥላል።
                   
                  የሰማያዊ ፓርቲ መግለጫ፤

ትግላችን የህግ የበላይነትን ወደ ማስከበር ተሸጋግሯል!

ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም. ባካሄደው ታላቅ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለመንግሥት 

ያቀረብናቸው ጥያቄዎች መልስ ባለማግኘታቸው ለሕዝብ ቃል በገባነው መሠረት በድጋሚ ተቃውሞ ሰልፍ አቅዶ 

አስፈላጊውንእንቅስቃሴ እያደረገ ነው፡፡ ለዚህም ሥራ መሳካት ለሚመለከተው የመንግሥት አካል ነሐሴ 13 ቀን

2005ዓ.ም. በደብዳቤ ያሳወቀ ሲሆን፣ መጀመሪያ ባቀረብነው ደብዳቤ ላይ ያልተካተቱ ጉዳዮችን
እንድናካትት ነሐሴ 15 ቀን 2005 ዓ.ም. በተፃፈልን ደብዳቤ ተጠይቀን አስፈላጊውን መልስ አሟልተን ነሐሴ 17 

ቀን 2005 ዓ.ም. በተፃፈ ደብዳቤ አሳውቀናል፡፡

በአዋጁ በግልፅ እንደተደነገገው ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ህገ መንግሥታዊ መብት እንደሆነና ማንም ሊከለክለን 

እንደማይችል በማያሻማ መንገድ ተገልጿል፡፡ ሰልፉን የማሳወቁ ዓላማ የጥበቃ አገልግሎትና አንዳንድ አስተዳደራዊ 

ድጋፎችን ለማግኘት ነው፡፡ በዚህ አሰራር ውስጥ መንግሥት የጥበቃና የቦታ ችግር ካለ ሰልፉን ለሌላ ጊዜና ቦታ 

እንዲያደርግ ለሚመለከተው አካል ደብዳቤ በደረሰው በ24 ሰዓት ውስጥ በፅሑፍ መልስይሰጣል የሚል ድንጋጌ 

አለ፡፡ ነገር ግን በመንግሥትበኩል ላቀረብነው የመብት ጥያቄ ምላሽ መሰጠት ሲገባው እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ 

የመንግሥት መዋቅር ሙሉ በሙሉ በመጠቀምና ዜጐችን አስገድዶ ሰልፍ እንዲወጡ በማስፈረም ሰማያዊ ፓርቲ 

ሰልፍ በጠራበት ቀንና ቦታ ሌላ ሰልፍ በተደራቢ በሃይማኖት መቻቻል ስም ህገ መንግሥቱን በመጣስ የሃይማኖት 

ተቋማትን ለራሱ የድርጅት ፖለቲካ መጠቀሚያና የሰማያዊ ፓርቲን ህጋዊ እንቅስቃሴ ለመግታት እየተጠቀመበት 

ነው፡፡

No comments:

Post a Comment