Sunday, August 25, 2013

የደህንነትና የፖሊስ ሀላፊዎች የሙስሊሙን ህብረተሰብ የመብት ጥያቄ ለማዳፈን እንደሚሰሩ ገለጹ!

‹‹መንግስት መስጂዶችን ከአክራሪዎች ቀምቶ ለእኛ ሊሰጠን ይገባል›› የመንግስታዊው ሃይማኖት አቀንቃኝ ግለሰብ
የደህንነትና የፖሊስ ሀላፊዎች የሙስሊሙን ህብረተሰብ የመብት ይከበር ጥያቄ ለማኮላሸት መስራታቸውን እንደሚቀጥሉ አስታወቁ፡፡ ሀላፊዎቹ ይህን የገለጹት ለሁለት ቀናት በተካሄደ ስብሰባ ላይ ነው፡፡ ረቡእና ሐሙስ በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የስብሰባ ማእከል በተደረገው በዚህ ስብሰባ ህዝብ ያወረዳቸው የመጅሊስ ሹመኞች፣ የመስጂድ ኮሚቴዎች፣ በአዲስ አበባ የሚገኙ ኢማሞች፣ ሙአዚኖች እና የመንግስታዊው ሃይማኖት አቀንቃኞች የተገኙ ሲሆን ዋነኛ አጀንዳውን ያደረገውም ‹‹አክራሪነት በመከላከልና ጸጥታን በማስፈን›› ርእሰ ጉዳይ መሆኑ ታውቋል፡፡
መድረኩን ይመሩ የነበሩትም ከፍተኛ የደህነት ሹሞች መሆናቸው ተመልክቷል፡፡ በዚሁ ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉ ቀድመው የተመረጡና መናገሪያ አጀንዳ የተያዘላቸው ግለሰቦች ‹‹አክራሪዎችን ልንታገስ አይገባም፣ ድምጻችን ይሰማ የሚሉት የአክራሪዎችን ድምጽ ነው›› የሚሉና መሰል ዘላፋዎችና ዛቻዎችን ሰንዝረዋል፡፡
መንግስት ትእግስቱ በዝቷል፣ አክራሪዎችን ልንታገሳቸው አይገባም በሚል ሀሳባቸውን የገለጹትና በተሰብሳቢዎች መካከል ተሰግስገበው እንዲገቡ የተደረጉት ግለሰቦች አንንዶቹ የፖለቲካ ስራ የሚያከናውኑና የእስልምና እምነት ተከታይ ያልሆኑ ጭምር መሆናቸው ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ በመድረኩ ንግግር ሲያደርጉ የታዩት አንዳንዶቹም በየእለቱ በኢቴቪ የአዲስ አበባ ሙስሊም ነዋሪ እየተባሉ ለዜና ግብአትነት የሚውሉ ናቸው፡፡ የመንግስታዊው ሃይማኖት አቀንቃኝ ግለሰብ በበኩሉ ‹‹መንግስት መስጂዶችን ከአክራሪዎች ቀምቶ ለእኛ ሊሰጠን ይገባል›› በማለት የጠየቀ ሲሆን የመንግስት ሀላፊዎቹም ተቃውሞውን ለማፈንና በየሰፈሩ ያሉ ሙስሊሞችን ተቃውሞ ለመግታት ማሰራቸውን እንደሚቀጥሉ አሳስበዋል፡፡ በስብሰባው የተሳተታተፉ ብዙዎቹ ኢማሞች ሀሳባቸውን ከመግለጽ በመቆጠብ ስብሰባውን በፍርሃት ተካፍለው የጨረሱ ሲሆን በዚህ ስብሰባ ያልተገኙ ኢማሞችንም መንግስት በትእግስት እንደማይመለከታቸው ከመድረኩ የነበሩት የደህንነት ሃለፊዎች ተናግረዋል፡፡
ድምፃችን ይሰማ

No comments:

Post a Comment