Thursday, August 29, 2013

ስለ አርከበ እቁባይ! – አብርሃ ደስታ

7c196-1001168_485348238212789_1719160956_n
አብርሃ ደስታ
አቶ አርከበ ከህወሓት ጉባኤ በኋላ ከሌሎች የህወሓት አመራር አባላት ጋራ አብሮ ለመስራት ፍቃደኛ አለመሆኑንና በ አሁኑ ሰዓት ስልጣኑንና ሀገሩ ለቆ መውጣቱ ስንፅፍ እነሱ ደግሞ አቶ አርከበ የሦስተኛ ዲግሪ ትምህርቱን በለንደን እየተከታተለ መሆኑ ነገሩን።
አቶ አርከበ ትምህርት የጀመረው ከሦስት ዓመት በፊት ነበር (ከመለስ ሞት በፊት)። ይህ ሁኖ በሀገሩ እየኖረ የሚኒስተር ዲኤታ ሐላፊነቱ በአግባቡ እየተወጣ ነበር። ስለዚህ ትምህርት መጀመሩ አዲስ ነገር አይደለም።

አዲስ ነገር የሆነው በህወሓት ጉባኤ አለመግባባት ከተፈጠረ ወዲህ ስራው በፈቃዱ መተውና …በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ከሀገር መውጣቱ ነው። (ከዚህ በፊት ለትምህርትም ይሁን ለሌላ ስራ ከሀገር ወጥቶ አያውቅም አላልኩም፤ የአሁኑ መውጣት ሁሉም ትቶ መሆኑ ነው።)
ስለዚህ የአቶ አርከበ በለንደን ትምህርት መጀመር ስራውና ሀገሩ ለቆ አለመውጣቱ ማረጋገጫ አይሆንም። ሀገር ለቋል የምንለው ወደ ለንደን ስለሄደ አይደለም። (ብዙ የህወሓት ባለስልጣናት ኮ ወደ አሜሪካና አውሮፓ ተጉዘው ነበር፣ ሀገር ለቀው ሄዱ ግን አላልንም፣ ምክንያቱም አልለቀቁም።)
ስለዚህ ህወሓቶች ሆይ! ሌላ ምክንያት ፈልጉ።
It is so!!!

No comments:

Post a Comment